Saturday, 05 November 2022 11:43

“አፍሪካ ለአፍሪካዊያን” አህጉራዊ ሁነት ተከፈተ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 አቢሲኒያ ቢዝነስ ኔትወርክ ከአጋሮቹ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር ያዘጋጀው “አፍሪካዊያን ለአፍሪካውያን” የተሰኘው አህጉራዊ ዝግጅት ትናንትና ጥቅምት 25 ቀን 2015 በወዳጅነት አደባባይ ተከፈተ። ይህ አህጉራዊ ዝግጅት የአፍሪካን ባህል፣ ምርቶች፣ የቱሪዝም ሀብቶች፣ የኪነጥበብ ውጤቶች፣ የኢንቨስትመንት አማራጮችና የንግድ እሴቶችን እርስ በእርስ በማስተዋወቅና በማጉላት የሚከወን ትልቅ ዝግጅት ስመሆኑም የአቢሲኒያ ቢዝነስ ኔትወርክ ኩባንያ ባለቤትና ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ጥሩነህ ተናግረዋል።
የዝግጅቱ ዋና አላማም በመላው አፍሪካ የሚገኙ ማህበረሰቦችን በማቀራረብና ያሏቸውን የባህል፣ የኪነ-ትበብ፣ የንግድና ኢንቨስትመንት ልዩነቶች ወደ አንድ በማምጣት የአፍካን ሀብት በጋራ መጠቀም ሚቻልበትን ሁኔታ ለማመቻቸት ነው ብለዋል አቶ ዳንኤል። በዚህ ልዩና ዓመታዊ ዝግጅት የተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚከወኑ ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራት አንዳንዳቸው ባህሎቻቸውንና እሴቶቻቸውን የሚያሳዩበት አውደርዕይ፣ የፋሽን ትርኢት፣ የዳንስና የሙዚቃ ኮንሰርትን ጨምሮ በርካታ መዝናኛዎች ይኖሩታል ተብሏል።

Read 10907 times