Saturday, 05 November 2022 11:46

“ኢትዮጵያ ምን አጥታ ተቸገረች” መጽሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

    በደራሲ አስፋ አደፍርስ  የተጻፈውና በኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የታሪክና ፖለቲካውንና  ስርዓተ መንግስቱን ተከትሎ አሁን የደረደንበትን ምስቅል የሚያመለክተው “ኢትዮጵያ ምን አጥታ ተቸገረች” የተሰኘው መጽሐፍ ዛሬ ህዳር 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ጀምሮ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል በተለያዩ መርሃ ግብሮች ይመረቃል። ደራሲው በተለይም በነጋና በመሸ ቁጥር  የሚያንገበግባቸውን አገራዊ ችግሮቻችንን ለመቀነስ በእርጅና ዕድሜያቸው ያለማንም አጋዥ የጀመሯቸው ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶቻቸው በሙሰኞች እንዴት እንደወደሙባቸው ለታሪክ የተቀመጠበት እንደሆነም ታውቋል።
በመጽሐፉ ምረቃ ላይ መጽሀፍ ዳሰሳና ውይይት የሚደረግ ሲሆን፣ ደጃዝማች ወልደሰመያት ገ/ወልድ፣ ብ/ጄ ካሳዬ ጨመዳ፣ ረ/ፕ አበባው አያሌው ደራሲና ጋዜጠኛ በኩረ ትጉሃን ጥበቡ በለጠ በመጸሐፉ ላይ ሙያዊ ገለጻ ያደርጋሉም ተብቧል። በዕለቱ ገጣሚና፣ ጸሐፌ ተውኔት  አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ጸሀይ መላኩና ሌሎችም ትልልቅ ደራሲያን በክብር እንግድነት ይገኛሉ ተብሏል። መጽሐፉ በ295 ገጽ ተቀንብቦ በ350 ብር ለገበያ የቀረበ ሲሆን በዋናነት ጃዕፈር መጽሀፍት መደብር ያከፋፍለዋል። ደራሲው ከዚህ ቀደም “ከባቹማ እስከ ቨርጂኒያ” የተሰኘ መጽሐፍ ለንባብ ማብቃታቸው አይዘነጋም።

Read 11169 times