Print this page
Saturday, 05 November 2022 12:44

የሌባው የመጨረሻ ምሳ

Written by  መሐመድ ኢድሪስ
Rate this item
(7 votes)

 ትንሳኤ በጠዋቱ ተነስቶ ፊቱን ታጠበና ቁርስ አደረገ። የሚኖረው ብቻውን ሲሆን ዛሬ ለእረፍት ያህል ይመስላል፣ ከሴተኛ አዳሪ ጋር አላደረም። ለነገሩ ምክንያት ነበረው፡፡ ምንም ሳይሸቅል ነበር ያደረው። ዛሬ ግን ቆርጦ ተነስቷል፡፡ የጀበና ጫት ከጠይብ በዱቤ ወስዶ ከነከሰ በኋላ አይኑ ተከፈተ፡፡ ቀይ “ነፍስ ይማር” ጃኬቱን (በሃምሳ ብር ያስያዘው ሰው ሳይሞት አይቀርም) ደረበና ዞር ዞር ማለት ያዘ፡፡ መጀመሪያ ወደ ማዘር ቤት ነበር የገባው፡፡ ማዘር ከሱቁ ባንኮኒ ፊት ለፊት ሳይሆን ጓዳ ውስጥ ሆነው ለመሿለኪያ ልጆች ለምሳ የሚደርስ ሽሮና በየአይነት መወጥወጥ ልማዳቸው እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን ትንሳኤ የተለመደ ስራውን ጀመረ፡፡
ፊቱ ፓፓያ ይመስላል፡፡ ከንፈሩ በጣም ወፍራም ሆኖ በሲጋራ አርሮ የተለበለበ ግንድ ነው የሚመስለው፡፡ ሴተኛ አዳሪዎቹን ሲስም አፉ እንዳይሸት ጫቱን ተፍቶ ማስቲካ ማኘክ ልማዱ ነው፡፡ ማዘር ወጡን ሲወጠዉጡ ማስቲካውን ከአፉ አወጣና የያዘው የጫት እንጨት ላይ አጣብቆ፤ “ማዘር ሲጋራ ይስጡኝ ወልፎኛል፤ ነገ እከፍላለሁ፡፡” አለና ባንኮኒውን ደገፍ ብሎ ሁኔታውን አጠና፡፡ ማዘር በትልቅ ቁልፍ መሳቢያውን ዘግተው ቁልፉን መቀነታቸው ላይ ማንጠልጠል ልማዳቸው ሲሆን፤ ይህንን ሲያደርጉ መሳብያው አናት ላይ ያለው ሳንቲምና ገንዘብ የሚያስገቡበት ቀዳዳ፣ የትንሳኤን የጫት እንጨት ማስገባት እንደማይችል ግን እንዴት ያውቃሉ?!
“ዱቤ የለም! ያለፈውን ሳትከፍል ዱቤ ስትል አታፍርም!”
ትንሳኤ እንጨቱን ሰዶ በማስቲካው አንዱን ብር አጣብቆ ያዘና መዞ ሲያወጣ በለስ ቀናው። ድፍን መቶ ብር!
“እርሶ ደግሞ ሰው አያምኑም፤ የሰው ሙድ ይጨርባሉ፡፡” ብሎ እየተነጫነጨ ባንኮኒውን መታ፡፡
“ምናችሁ ይታመናል፤ ነፍስ በላዎች! አሁን ሂድልኝ!” እየሳቀ ወጣና ሌላ ሩብ ገለምሶ በሃያ ብር ከጠይብ ገዝቶ፣ ሲጋራውን እያጨሰ፣ ዞር ዞር ማለት ጀመረ፡፡ ከአለም አንደኛ ላቦሮ መሆኑን ለማስመስከርና ዛሬ ጆፌ የጣለባትን ያቺን ግድንግዷን ቡና የምታፈላውን አዲሷን ኮረዳ ይዞ ሊፎልል ቋምጧል፡፡ ጫቱን እየጨመቀ ሲጋራውን ሲምግ፣ የሴቷ አረግራጊ ዳሌ ልቡን ሰወረው፡፡
ሌላ በለስ ቀናው። አንድ ካሜራ የያዘ ፈረንጅ የባቡር ጣቢያውን የመሿለኪያ ድልድይ በቪድዮ ካሜራ ከቀረፀ በኋላ ወደ መኪናው ገብቶ ካሜራውን የመኪናው ጋቢና ላይ አስቀምጦ ሚስቱን ይጠብቃል፡፡ ሚስቱ ፊት ለፊቱ ካለው ሱፐር ማርኬት እንደገባች ያጠናው ጮሌው ትንሳኤ፤ ድንጋይ ላይ ቁጭ ብሎ ጠፍሾት የሚያዛጋውን አባው በፉጨት ጠራው። አባው እንደመጣ አንድ ሲጋራ ሰጠውና፤
“ያን ዜጋ ታየዋለህ”
“ባለማርሴዲሱ”
“አዎ፤ የፊት ፍሬቻው ላይ ሲጋራውን የምትለኩስ አስመስለህ ሸውድልኝ፡፡ ካሜራውን እነጨዋለሁ፤ ደህና አድርጌ ነው የምለቅልህ”
“ስታይል!”
አባው እድሜው ምን ያህል እንደሆነ ባይታወቅም፣ ቁመቱ ግን ሜትር ከሰላሳ ነው ከተባለ ማጋነን ይሆናል፡፡
ፍሬቻው ላይ ሲጋራውን ሰክቶ የሚለኩስ እየመሰለ ሲደናበር፣ ፈረንጁ ተገርሞ አባውን እያየ እሱም ሲደናበር ሶስት ደቂቃ ፈጅቷል። አጅሬ ግን ካሜራውን ይዞ የተቀየሰው ገና በአንደኛው ደቂቃ ነበር፡፡ ካሜራውን ወስዶ ለጆቢራ ሲሰጠው፣ “አንድ ትልቁን” አሻረው። ከማዘር መቶ ብር ጋር አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር መሆኑ ነው፡፡ አባው እካፈላለሁ ብሎ አስቦ ከሆነ አፍንጫውን ይላስ፡፡ ትንሳኤ ሞት እንጂ ምንም አያካፍልም፡፡ ለዚህም ይሆናል አባቱ ትንሳኤ ብለው የሰየሙት፡፡
አባቱ የቅኔ ፀሐፊ ነበሩ። ነፍሳቸውን በገነት ያኑራቸውና፡፡ የአለም አንደኛ ላቦሮ መሆኑን አባው ስለሚነግርለት የዛሬው ገድሉ ይበቃዋል። እንደ እድል ሆነና ሌላ የአለም አንደኛ ላቦሮ የሚያሰኘው አጋጣሚ ተፈጠረ። አንዲት ሸንቃጣ ወጣት ሽንጧን እየሰበቀች፣ አስር ሺህ ብር በካኪ ወረቀት ውስጥ እየከተተች፣ ከመኪናዋ ወርዳ ወደ ባንክ ልትገባ ፈጠን ፈጠን እያለች ስትራመድ ትንሳኤ ፊቷን ለየው። አንድ ቀን ሊጠብሳት ሞክሮ ተከትሎ ለስንት ሰዓት እንደሆነ ባይታወቅም፣ ሲጀነጅን ውሎ ፊቷ ላይ ያለውን ንቀት በውሸት ፈገግታ ሸፍና ስልክ ሰጥታው ሰላም ሲባባሉ (ኮሮና ያኔ አልነበረም) እጁ ላይ የቀረው ውድ ሽቶዋ ራሱን አዙሮት ሊወድቅ ተንገዳግዶ ነው የተረፈው፡፡ እንደለመደው ቺኮች የሰጡትን ስልክ የእውነት ይሁን የውሸት ለማረጋገጥ የህዝብ ስልክ ላይ አራት ሳንቲሞች አስገብቶ የደወለበትን ጊዜ አስታወሰ፡፡ ምኑ ሞኝ ነው የማያገኛትን ሴት እያለመ ጊዜ የሚያጠፋው፡፡
ጎርናና የወንድ ድምፅ፤ “ሂድና ሶሲህን የምትፈልግበት ፈልግ፣ ነሆለል!” እንዳለው አይረሳም፡፡ እግረ መንገዱንም የስልኩን እጀታ በሃይል ስልኩ ላይ አሳርፎ፣ ስልኩን አራግፎ ብዙ ሳንቲሞችን መመንተፉን አይረሳም፡፡
ትንሳኤ ሴትዋ በመላው መሿለኪያ ጦጣ እንዳደረገችውና አባው አረቄያቸውን እየጠጡ ሙድ ሲይዙ ራሱ አባው ወሬ ነጋሪ እንዲሆን ስለፈለገ፣ ትንሳኤ የት እንደገባ ግራ ገብቶት የሚቅበዘበዘውን አባው በፉጨት ጠራና፤ “ምን ትቆዝማለህ እንካ አመድ” ብሎት “ሂድና ከጠይብ ሱቅ ቢጫ ፓስታ ይዘህ ና፤ እንካ ዴች ያቺን ቄንጠኛ ታያታለህ፤ ማን መሆኔን አሳያታለሁ፡፡” አባው ሲጋራውን በስታይል ለኮሰና “እናትዋን አውቂያታለሁ፡፡ ያኔ ጦጣ አርጋህ ነበር፡፡” አለ፤ ከትንሳኤ መቶ ብር መገኘቱ የእየሱስ መነሳት መድረሱን የሚያበስር ጥሩ ምልክት መሆኑን በልቡ እያሰላሰለ፡፡
“ጦጣ---ማን ጦጣ እንደሆነ ዛሬ ታያለህ!”
አባው ፓስታውን ይዞ ሲመጣ ሴትዋ ባንኩ በር ላይ ቆማ እየተንጎራደደች ስልክ ታወራለች። ትንሳኤ በአጠገቧ አለፈና ጋዜጣ የተከተተበት ቢጫ ፖስታ ይዞ ወደ ባንኩ ገባ። ትንሽ ወረፋ ብቻ ነበር ያለው። እንደጠበቀው ገባችና ካኪውን ባንኮኒው ላይ አስቀምጣ የፎርም ወረቀት ላይ መፃፍ ስትጀምር፣ አጅሬ የወጪ ወረቀት ላይ የሌላ ሰው ስም መቸክቸክ ያዘ። ከፋይዋ ብር እየቆጠረች መሆንዋን አየና የሱን ፖስታ ከሴትየዋ ፖስታ ጋር ቀስ ብሎ ለዋወጠው፡፡ ፊቱን አዙሮ ወደ በሩ ሲያመራ እሷም ቄንጠኛ ፊርማዋን ፈርማ ጨረሰች። ሴትየዋም የዋዛ አልነበረችም፡፡ ፖስታው ሙሉ ለሙሉ አዲስና የእርሷ ድርጅት አርማ የሌለበት መሆኑን አስተውላ ዞር ስትል ቀይ ጃኬት የለበሰ ሰው፣ ቢጫ ካኪ ፖስታ ይዞ ፈጠን ፈጠን እያለ ሲራመድ ተመለከተች፡፡
ፖስታውን ብትንትን ስታደርገው፤ “አብዮታዊ ፖሊስ” የሚል የድሮ ጋዜጣ!
“ፖሊስ! ፖሊስ!” እያለች ስትሮጥ፤ ሁለት ፖሊሶች እየሮጡ ከተፍ አሉ፡፡ የቆሙት ባንኩ አጠገብ ነበር።
“ያውና ቀይ ጃኬት የለበሰው---ብሬን ይዞ ሄዷል፡፡ ቢጫ ካኪ ውስጥ አስር ሺህ ብር!”
ትንሳኤ ሩጫውን አስነካው። አባው ይሄን ጉድ ለሰፈር ልጆች ለማውራት እየሮጠ ሊያ አረቄ ቤት ዘው ብሎ ገባና፣ አንድ ደብል አዝዞ ሲጋራ ለኮሰ፡፡
ትንሳኤ ፖሊሶቹን የሸወደው በሴንት ጆሴፍ አጥር ዘሎ ትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ በመግባት ነበር። አልለቀቁትም። እነሱም ዘለው ሲገቡ ቀይ ጃኬቱን አውጥቶ ጣለና ወደ ተማሪዎች ድሮወር ክፍል ሲገባ፣ መሽቁቁ ፖሊስ የተጣለውን ጃኬት ዘሎ ሳይረግጠው አለፈና በአቅራቢያው ከዚያ ክፍል ውጭ የትም ሊገባ እንደማይችል አረጋግጦ “አንተ እዚህ ቆይና በሩን ያዝ፤ ማንም እንዳይወጣ፤ እያንዳንዳቸውን እፈትሻለሁ፤ አለቀውም” አለ ለባልደረባው፡፡
እንዳለውም መፈተሽ ጀመረ። ወደ አስር ያህል ተማሪዎች ነበሩ። ትንሳኤ “ዛሬ ተበላሁ” አለና ወደ አንዱ ድሮወር / ሳጥን ሲመለከት፣ ሳጥኑ ቢቆለፍም፣ ከላይ ግን አስር ሺህ ብር ማስገባት የሚችል ሽንቁር እንዳለ አስተዋለ። ቀስ ብሎ ብሩን በዚያ አሾለከው፡፡ ፍተሻው ሲያልቅ ተመልሶ መጥቶ በሆነ ዘዴ ከምሳ በፊት ያወጣዋል፡፡ የምሳ ማስቀመጫ እንደሆነ ስለሚያውቅ፡፡ ተፈትሾ ወጣ፡፡
የማዘር ልጅ ብስራት፣ እናቱ በየአይነትና ሽሮ እየሸጡ በመቀናታቸው የቋጠሯትን ብር ቆጥበው ልጆቻውን ውድ ትምህርት ቤት ሲያስተምሩ “ባለመማራችን ነው እንዲህ የሆነው፡፡ የተማረ ይግደለኝ፤ ከእንግዲህ ለየትኛው እድሜ፤ ጊዜው የነሱ ነው” ብለው ይመልሱ ነበር፤ ለሰፈር ሰው። ያን ቀን ብስራት በጣም ስለራበው አራት ሰዓት ላይ የምሳ እቃውን አውጥቶ ግማሽ ያህሉን በልቶ፣ ግማሽ ያህሉን ለምሳ ሊያስቀምጥ አስቦ ሳጥኑን ከፈተ፡፡
ማዘር ልጃቸው በዚህ ሰዓት ይመጣል ብለው አላሰቡም፡፡
“ምን ሆነህ ነው? አሞህ ነው?” ብለው ሲጠይቁ ጩሉሌው ብስራት፣ ሁለት ሺህ ብር ለእናቱ ሰጥቶ፤ ስምንቱን የኋላ ኪሱ ውስጥ ቀርቅሯል፡፡
“ኬት አመጣህ ከዚያ ትንሳኤ ጋር ገጥመህ ምንተፋ ጀምረሃል መሰለኝ… ጉድ ጉድ ገና አስራ ሁለት አመቱ እኮ ነው፡፡” አሉ፤ የባንኮኒውን ሽንቁር እንዳይከፈት አድርጎ በጣውላና በረጅም ምስማሮች በመዶሻ ለሚደበድበው የሰፈሩ ሁለገብ ሰራተኛ ኢሳያስ ሲያስረዱ፡፡
 “ከዚህ ቀዳዳ እንኳን የሚመነትፍ አበስክ ገበርኩ!”
“መሬት ላይ አግኝቼ ነው፡፡”
“አይ እውነቱን ታወጣለህ፤ ማነው በአሁኑ ዘመን ሁለት ሺህ ብር መሬት ላይ የሚጥል፤ ገና በበርበሬ ትታጠናለህ፡፡”
ብስራት እቺ የበርበሬ ማጤን ፉከራ ከንቱ እንደሆነች ስለሚያውቅ “ካላመንሽ ተይው” አለና እየተነጫነጨ ወጣ፡፡
“ትመጣለህ እዚህ ቤት አንተ እርኩስ” ካሉ በኋላ ብሩን በደስታ እያዩ፤ “ነገሩ አንድ ፍሬ ልጅ እኮ ነው፤ ተንኮል አያውቅም፤ ወድቆ ቢያገኘው ነው” አሉና ብሩን መቁጠር ሲጀምሩ “አይ ትንሳኤ”  ማለታቸውን አልረሱም። “ትንሳኤማ አስር ሚስማር ቂጡ ላይ ቀርቅሬበታለሁ፤ ይኸው ማዘር ጨረስኩኝ” አለ ኢሳያስ፤ ትንሳኤ ስልኩን መንትፎ የሮጠበትን ቀን እያስታወሰ። “አንቺም አራዳ እኔም አራዳ ምን አሽዋወደን  በሰው በረንዳ” እያለ በልቡ፤ “አንድ ሺህ ብር ይከፍላሉ” አለ ፍርጥም ብሎ። ብስራት ሁለት ሺህ ብሩን ለማዘሩ ሲያስረከብ ያየው እሱ ብቻ ነው፡፡
“ኧረ ነው፡፡ ደህና ብር ጠፊ ነው፤ ሰው ይሻላል” አሉና ቆጥረው ሰጡትና ወደ ቤት ገቡ።
ትንሳኤ ከምሳ በፊት ተመልሶ ወደ ሴንት ጆሴፍ  ግቢ ዘሎ ገባና የሳጥኑን ቁልፍ በሽቦ መጎርጎር ጀመረ፡፡ እሱ መላ አያጣ፤ በርግዶ ሲከፍተው እላዩ ላይ “ብስራት በለጠ” የሚል ፅሑፍ ያለበት የምሳ እቃ ብቻ! ደሙ ፈልቶ የምሳ እቃውን ያዘና ወጣ። ብስራትን እንዴት አድርጎ ብሩን እንደሚቀበል ሲያስብ ምንም መላ አልታይ አለው፡፡ ወደ ሱቁ ገባ። ዞር ዞር ብሎ ብስራትን ፈለገ፡፡ የለም። አንድ አዲስ ነገር አስተዋለ። የማዘር የባንኮኒ ሽንቁር በጣውላ ተቀርቅሯል፡፡ ሚስማሮቹን አያቸው። ባልወለደ አንጀቱ እንዲህ ጉሮሮውን የዘጋበት ከኢሳያስ ውጭ ማንም ሊሆን እንደማይችል እርግጠኛ ነው፡፡ ኬት መጀመር እንዳለበት አሰበ፡፡ የብስራትን ምሳ እቃ ከፈተ። አንደ አጋጣሚ ፓስታል ፉርኖ ነበር፡፡ ምሳውን እየበላ “አይ ማዘር! ለልጆችዎ ምርጥ ምርጡን ነው የሚሰሩት” እያለ የካሜራውን ሽያጭ አንድ ሺህ ብር ይዞ ምን ማድረግ እንዳለበት ሲያስብ፣ ብስራት አንድ እሽግ ፒዛ ይዞ ከጓደኞቹ ጋር ሲበላ አይን ለአይን ተገጣጠሙ፡፡
የአባታችን ልጆች ስለለሆንን ነው ሁሉም አባቶችን ለካ ልጆች ወልደናል ብለው ስለሚኮሩብን ነው፡፡ ፀሀፊ ትዛዝ ወለደጊዮርጊስ ለያፈትሄ ንጉስ ከፃፉት ደብዳቤ፡
ታመህ ሳልጠይቅህ መቅረቴን አትውቀስ  
ባውቀው ነው ከመጣው እንደማልመለስ
ያሉት ወደው አይመስለንም ኢትዮጵያ በድሮ ፖለቲከኞች ቋንቋ የብሄር ብሄረሰቦች እስር ቤት ናት ተብሎ ከተነገረ ሰንብቷል ብዙዎች እንደሚያስቡት ብሄር ብሄረሰቦች ዛሬ የመጡና የተፈጠሩ አይደሉም የመንግስት ፖሊሲም ይህን ያውቅ ዘንድ ግድ ይለዋል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ እናት እንጂ እንጀራ እናት አይደለችም ማንም የመጣ መሪ አንድ ማስተዋል ያለበት ነገር “አዲስ እረኛ ከብት አያስተኛ” የሚለውን ተረት ነው ፡፡ አዲስ እረኛ ወደ ኩሬ ከብቶችን መርቶ ሲያበቃ ማድረስ እንጂ ማስጠጣት እንደማይችል ሁሉ ማንም መሪ ህዝብን መንገድ እና መስመር ከማሳየት በቀር በግድ ብላ በግድ ጠጣ በመበረሻም በግድ ኑር ማለት አይቻልም በርካታ ስደቶች የዚህ በግድ የማስኖር ስልት ምክንያቶች ናቸው ፡፡ ወጣቶቻችን ሀገር ጥለው የሚጠፉት መልካም አስተዳደር አጥተው መሆኑን አንርሳ እንጂ ፈረንጅ ሀገር ናፋቂ ሆነው እንዳልሆነ ማንም መንግስት ማንም መሪ ልብ ይበል፡፡ በተደጋጋሚ እንደፃፍነው ልብ ከፍቅር እንጂ ከሃይል ኤወለድም የሄንን በተለይ የዛሬ መንግስታችን ልብ ይበል እንላለን፡፡
ለልባም ልብ ይስጠው!
ከለታት አንድ ቀን አንድ እጅግ ሃብታም የሆነ እና ባለፀጋ ሰው ነበር፡፡ ልጁ የደረሰች ነበረችና ለሌላ ሀብታም ዳራት፡፡ መቼም ሴት ልጅ ከእናት ውጪ ሚስጥር የላትም እና አንድ ቀን እናት ለልጇ የእኔ ልጅ አንቺ እኮ ልጅ ነሽ ልጅ ስለሆንሽ ቀንሽን መቁጠር ላይሆንልሽ ይችላል። ለመሆኑ ድንገት ወርሽ ከገባ የገንፎ እህል እንዳዘጋጅ ቀደም ብለሽ አሳውቂኝ ፡፡ ሆድሽ እኮ እየገፋ ነው ይታየኛል፡፡ ስለዚህ እባክሽ ቀድመሽ የወር አበባሽ ከቆመ አሳውቂኝ አለቸት ፡፡ ልጅቷ ሌላ የመትመልሰው ነገር ስላልነበራት እማየ ሰውዮው፤
በየቀኑ ይጨምርበታል እነዴት አድርጌ ማርገዜነ ልወቀው አለቻት ፡፡
እናትም በርግጥም አዝና በይ አርግዘሽ ካልሆነ ከዛሬ ጀምሮ የርግዝና ምልክት የሚባሉትን ነገሮች ያስተውሽ ተጓዢ ፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ለባሏ በተኙ ቁጥር “ባሌ እባክህ እንዳላረግዝ ማለት ጀመረች”
በልቶም እርግዝና ለምን ትፈሪያለሽ እኔ ምንም ይሁን ማን ከሰውየው ይልቀቅ የሆድሽን መግፋት ከልቤ የማከብር ሰው ነኝ ስለዚህ አትጨነቂ መቼም ቢሆነ እርግዝና ትንሽ የለውም (there is no little pregnancy)
ኢትዮጵያ ሀገራችን እኛን ሁሉ ወልዳ ዛሬም እርጉዝ ናት ዛሬም አዋላጅ ትፈልጋለች ዛሬም ገናዥ እና አናዛዥ ትፈልጋለች፡፡ እኛ ልጆችም አንዴ ተወልደናል እና ነገን መውለድ አለብን ጭንቀታችን ሁሉ ነገን ለማዋለድ ነው፡፡ አገር በትግል እንጂ በእድል አታድግም ሁላችንም ለየልጆቻችን ይህን ሀቅ እንንገር ኢትዮጵያ የምንፈልጋት ሱዳን እና ኬንያ ስላልሆነች ብቻ ሳይሆን እናታችን ስለሆነች ነው፡፡ መኩራት ያለብን የሀገራችን ልጆች ስለሆንን ነው፡፡      

Read 1261 times