Saturday, 27 October 2012 09:38

ባክቴሪያና ቫይረሶችን የሚያጣራ የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ አገራችን ገባ

Written by  መታሰቢያ ካሣዬ
Rate this item
(3 votes)

በቤት ውስጥ ባለው አየር ዙሪያ የሚገኙ አለርጂ አምጪ ተህዋስያን፣ ባክቴሪያዎችንና ቫይረሶችን በማጣራት ንፁህ አየር የሚፈጥር የተባለ የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ መሣሪያ አገራችን ገባ፡፡ LG በተባለው የኮሪያ ኩባንያ ተሠርቶ በሜትሮ ፒኤልሲ ወደ አገራችን የገባው የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ መሣሪያ አየር ውስጥ የሚገኙ ባክቴሪያዎች ለማጣራት የሚያስችል አራት ማጣሪያዎች የተገጠሙለት ሲሆን መሣሪያው አየሩን ከማሞቅና ከማቀዝቀዝ ባለፈ ንፁህ አየር እንዲሆን ለማድረግ እንደሚረዳው የ LG ምክትል ፕሬዚዳንት ሚስተር ሳንግሚን ሊ ሰሞኑን በሂልተን ሆቴል በተካሄደ የማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ ተናግረዋል፡፡ 

በሜትሮ PLC አስመጪነት ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ አገራችን የገባው ይኸው መሣሪያ፤ የሃይል መዋዠቅ ችግሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ለመቋቋም የሚያስችለው መሣሪያ የተገጠመለት በመሆኑ በየጊዜው የሚከሰት የኃይል መዋዠቅ እንደማያሰጋው ተገልጿል፡፡ የ LG ኩባንያ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ ዶኒር አቡበከር በበኩላቸው፤ ኩባንያው የተሻሉና ለህብረተሰቡ ጠቃሚ የሆኑ ዕቃዎችን በማምረት የሚታወቅ መሆኑን ጠቅሰው የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ መሣሪያዎች ተጨማሪ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉበትን መንገድ በማሰብና የወቅቱን የአየር ብክለት ከግምት ውስጥ በማስገባት አየርን ከማሞቅና ከማቀዝቀዝ ባለፈ የማጣራት አገልግሎት የሚሰጥ መሣሪያ ለገበያ ማቅረቡን ተናግረዋል፡፡
LG ኩባንያ ላለፉት ስምንት ዓመታት በአንድ መቶ ሚሊዮን የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ሽያጭ በአለም የአንደኝነት ደረጃ ይዞ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

Read 2072 times