Saturday, 19 November 2022 19:40

ኢትዮ ቴሌኮም ለአለማቀፍ የቴሌኮም ተቋማት ጥሪ አቀረበ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

  • የኢትዮ ቴሌኮም 40 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ቀርቧል
        • ሳፋሪኮም በአንድ ወር ውስጥ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አፍርቷል።

       በኢትዮጵያ ውስጥ በብቸንነት የቴሌኮም አገልግሎትን ሲሰጥ የቆየውና ካፒታሉ 400 ቢሊዮን ብር መድረሱ የሚነገረው ኢትዮቴሌኮም በቴሌኮም፤ ዘርፍ ለተሰማሩ አለማቀፍ ተቋማት ጥሪ አቀረበ። መንግስት ይህንኑ ግዙፍ የመንግስት የልማት ድርጅት 40 በመቶ ድርሻ ለሽያጭ ለማቅረብ ያዘጋጀው ጨረታ በይፋ ተከፍቷል።
ለበርካታ አመታት ብቸኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጭ ሆኖ የቆየው ኢትዮቴሌኮም ለሦስተኛ የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ተቋም ፈቃድ ለመስጠት ተወዳዳሪዎች ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ጥሪ አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት ከ52 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ኢትዮቴሌኮም ለደንበኞቹ የስልክ የኢንተርኔትና ሌሎች የቴሌኮም አገልግሎቶችን እየሰጠ ይገኛል።
ለበርካታ አስርት ዓመታት በኢትዮቴሌኮም በብቸኝነት ተይዞ የቆየውን የአገልግሎት ዘርፍ ለመቀላቀል ፍላጎት በማሳየት  ጨረታውን አሸንፎ  ፍቃድ ያገኘውና በተለያዩ የአፍሪካ አገራት ታዋቂ የቴሌኮም ኢንዱስትሪ የሆነው ሳፋሪኮም፤  ከወር በፊት በኢትዮጵያ በጀመረው የቴሌኮም አገልግሎት ከአንድ ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ደንበኞቹን ማፍራቱንና ባለፉት ሁለት ሳምንታት ብቻ 200ሺ ደንበኞችን ማፍራቱን ከኩባንያው የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።


Read 14673 times