Saturday, 26 November 2022 00:00

“የዘመን መስታወት” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 የአንጋፋዋ ደራሲ የዝና ወርቁ አዲስ ስራ የሆነው “የዘመን መስታወት” መፅሀፍ ዛሬ ህዳር 17 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል ይመረቃል፡፡
የምርቃቱ አዘጋጅ ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት እንደገለፀው በዕለቱ በርካታ ወጣትና አንጋፋ ፀሀፍት ተገኝተው ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ፡፡
በመፅሀፉም ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ ደራሲ የዝና ወርቅ በአሁኑ ወቅት የደራሲያን ማህበር ስራ አስኪያጅ ስትሆን ለቁጥር የሚያታክቱ በተለያዩ ዘውጎች የተሰናዱ መፅሀፍትን ለንባቢያን ማድረሷ ይታወሳል፡፡ በዕለቱ አዲሱን ሥራዋን “የዘመን መስታወት”ን መጥተው እንዲመርቁ አዘጋጁ ሰምና ወርቅ ኢንተርቴመንት ጥሪ አቅርቧል፡፡   

Read 17716 times