Print this page
Saturday, 17 December 2022 12:54

“አፍሪካ ቴሌ ሜዲስን ኔትወርክ” የመጀመሪያ ጉባዔውን በአገራችን አካሄደ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 በአፍሪካ  በሚገኙ የተለያዩ አገራት ውስጥ ያሉ የህክምና ባለሙያዎችን ከአገራችን የጤና ባለሙያዎች ጋር በኔትወርክ በማስተሳሰር ለህሙማን በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የተደገፈ ህክምና ለመስጠት የሚያስችለው “አፍሪካ ቴሌሜዲስን ኔትወርክ”፣ የመጀመሪያ ጉባዔውን በአገራችን አካሄደ።
መቀመጫውን በአሜሪካ ያደረገው የአፍሪካ ቴሌሜዲስን ኔትወርክ፣ በአህጉሪቱ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎችን በኔትወርክ በማስተሳሰርና ዘመኑ ያመጣውን ቴክኖሎጂዎች በስፋት በመጠቀም ለህብረተሰቡ ደረጃውን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል።
በአገራችን ውስጥ ያሉ የጤና ማዕከሎች በተቀናጀና እርስ በርስ በኔትወርክ በተሳሰረ ሁኔታ እንዲሰሩ በማድረግ ለህሙማን የተሻለ ህክምና መስጠት ስለሚቻልበት ሁኔታ በመከረው በዚህ ጉባዔ፤ ህሙማን አቅማቸውን ባገናዘበ ተመጣጣኝ ክፍያ አገልግሎት ስለሚያገኙበት ሁኔታ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
በትናንትናው ዕለት የተካሄደውን ይህንኑ ጉባዔ አሜሪካን ሜዲካል ሴንተርና አፍሪካ ቴሌሜዲስን ኔትወርክ በጋራ አዘጋጅተውታል።



Read 11556 times