Saturday, 17 December 2022 13:56

“እኔነኝ ኢትዮጵያ” 8 የህፃናት መፅሀፍትና መዝሙሮች ነገ ይመረቃሉ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

ኑሮዋን በሀገረ አሜሪካ ያደረገችው የህፃናት መፃህፍት የደራሲ የታቲያና ክፍሌ 8 የህፃናት መፅሀፍትና 4 መዝሙሮች ነገ ታህሳስ 9 ቀን 2015 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ ካዛንቺስ በሚገኘው ፈንድቃ የባህል ማዕከል በድምቀት ይመረቃሉ፡፡ በዕለቱ ሀገር ተረካቢ  በሆኑት ልጆች ጉዳይ ላይ ወላጆች፣ የአዕምሮ ጤናና የስነ ልቦና ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ይመክራሉ የተባለ ሲሆን፤ ከሚመረቁት መፅሀፍት የተመረጡ ክፍሎች በልጆች ለታዳሚ እንደሚነበቡም ታውቋል፡፡
በዚሁ መርሃ ግብር የተለያዩ ት/ቤቶች ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ጋር በፈንድቀ ባህል ማዕከል ተገኝተው ጭቃ ማቡካት፤ ጥጥ መፍተል በስዕል ባለሙያ እየታገዙ ስዕል መሳልና የተለያዩ ጫዎታዎችን የሚጫዎቱ ሲሆን በዕለቱ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ልጆቻቸውን ይዘው በመምጣትና በምረቃው ላይ በመታደም ልጆች ላይ በሚደረገው ምክክርም እንዲሳተፉና ልጆችዎ ጥሩ ጊዜ እንዲያሳልፉ ጋብዘናል ሲሉ ደራሲዋ ታቲያና ክፍሌ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Read 20617 times