Print this page
Saturday, 24 December 2022 15:44

ኬንያ በ10 ዓመት ውስጥ 15 ቢ. ዛፎችን ለመትከል አቅዳለች

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 “ማዕከላቱ ከአሁን ጀምሮ እስከ 2032 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ 15 ቢሊዮን ችግኞችን ያመርታሉ። ችግኞቹ በ10.6 ሚ.ሄክታር የተራቆቱ ደኖችና የግጦሽ መሬት ላይ ይበቅላሉ። ይህ አገራዊ የዛፍ ሽፋናችንን ከ30 በመቶ በላይ ያደርሰዋል።”


          በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በኬንያ ምድር 15 ቢሊዮን ዛፎች የመትከል ዕቅድ የነደፉት የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ፤ የዛፍ ተከላ ሂደቱን የሚከታተል የሞባይል ስልክ አፕሊኬሽን በቅርቡ እንደሚያስጀምሩ አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ ይህን የገለጹት በንጎንግ ካጅያዶ ካንቲ የተፋጠነ የደንና የግጦሽ መሬት መልሶ ልማት ብሔራዊ መርሃ ግብርን ባስጀመሩ ወቅት ሲሆን፣ አፕሊኬሽኑ በየጊዜው የተተከሉ ዛፎችን ዕድገት ለመከታተል እንደሚያግዝ አስረድተዋል።
“እያንዳንዱ ኬንያዊ ወይም የኬንያ ተቋማት የተከሏቸውን ዛፎች ዕድገት ለመሰነድ የሚጠቀሙበት #Jaza Miti የተሰኘ አፕሊኬሽን በአጭር ጊዜ ውስጥ አስጀምራለሁ። አፕሊኬሽኑ የዛፎችን ዕድገት በየጊዜው ለመከታተል ያግዛል።” ብለዋል።
“በ10 ዓመት ውስጥ 15 ቢሊዮን ግብ ላይ በመድረስ ጉዟችን፣ የዛፎችን ዕድገት መከታተል እንፈልጋለን። የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ካቢኔን “ተልዕኮ 5 ቢሊዮን” ዘመቻ፣ እውነተኛ ዛፍ የማብቀል ዘመቻ እንዲያደርጉት አዝዤአለሁ”
በ10 ዓመቱ የዛፍ ተከላ ዘመቻ ወቅት ከ300 በላይ የሥራ ዕድሎች ለወጣቶችና ለሴቶች እንደሚፈጠርም ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል።
ይህ የመንግስት ፕሮጀክት 10.6 ሚሊዮን ሄክታር ገደማ የተራቆቱ ደኖችንና የግጦሽ መሬትን በዛፎች እንደሚሸፍን ፕሬዚዳንት ሩቶ ጠቁመዋል።
በመላ አገሪቱ በተቋቋሙ የተለያዩ የችግኝ ማዕከላት 15 ቢሊዮን ችግኞች እንደሚሰራጩም ነው የተናገሩት።
“ይሄ የሚቆምበት አንዳችም ምክንያት የለም። ምክንያቱም መንግስት በመላ አገሪቱ በኬንያ የደን ምርምር ተቋም ለተቋቋሙ 18 የችግኝ ማዕከላት 1ሺ ቶን ችግኞችን የማከፋፈል መርሃ ግብር ጀምሯል።” ብለዋል።
“ማዕከላቱ ከአሁን ጀምሮ እስከ 2032 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ 15 ቢሊዮን ችግኞችን ያመርታሉ። ችግኞቹ በ10.6 ሚ.ሄክታር የተራቆቱ ደኖችና የግጦሽ መሬት ላይ ይበቅላሉ። ይህ አገራዊ የዛፍ ሽፋናችንን ከ30 በመቶ በላይ ያደርሰዋል።” ሲሉ ተናግረዋል፤ ፕሬዚዳንት ሩቶ።  


Read 1258 times
Administrator

Latest from Administrator