Saturday, 31 December 2022 12:36

“ኢትዮጵያ የተቃርኖ ምኩራብ የመቀራመት ወይስ የማዳን ተልዕኮ” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

 “አሀዱ መድረክ” በተሰኘው ፕሮግራማቸው የምናውቃቸው የጋዜጠኞቹ ሊዲያ አበበና ሱራፌል ዘላለም ስራ የሆነው “ኢትዮጵያ የተቃርኖ ምኩራብ የመቀራመት ወይስ የማዳን ተልዕኮ” የተሰኘ መፅሀፋቸው ዛሬ ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በብሄራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡
 በእለቱ፡- በኩረ ትጉሃን ደራሲና ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ፣ የፍልስፍና መምህሩ ዮናስ ዘውዴ፣ መምህር አብይ ልማና አቶ ታደለ ደርሰህ ንግግር የሚያደርጉ ሲሆን ከመፅሀፊ የተመረጡ ክፍሎች ለታዳሚ በንባብ እንደሚቀርቡም ታውቋል፡፡
በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ የኤፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ በእንግድነት  ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለፁት ጋዜጠኞቹ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ የኪነ ጥበብ ሰዎች ዲፕሎማቶችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Read 3593 times