Print this page
Saturday, 31 December 2022 13:06

“ጥፍሮዬ” መፅሀፍ ዛሬ ይመረቃል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በደራሲ ተክለስላሴ ጋሻውጠና የተደረሰውና በሰሜን ሸዋ ማህበረሰብ ወግ፣ ባህልና በጎ ልማድ በተለይም በሰርግ ሥነ ስርዓታቸው ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰናዳው “ጥፍሮዬ” መፅሀፍ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ አዲሱ ገበያ አካባቢ በሚገኘው ጉለሌ ክ/ከተማ አዳራሽ ይመረቃል፡፡
በሰሜን ሸዋ ተጋቢዎች ሲተጫጩ ጀምሮ እስከ ሰርጉ ሥነ ስርዓት ያለውን ሂደትና ባህል እንዲሁም ማህበረሰቡ በእጅ ስራ ጥበብ ያለውን ልዩ ተሰጥኦ የሚያሰገነዝበው ይሄው መፅሀፍ የሽያጩ ገቢ ሙሉ በሙሉ ለበጎ አድራጎት ይውላል የተባለ ሲሆን፣ በዕለቱም ገጣሚ አስታውሰኝ ረጋሳና ድምፃዊ ግዛቸው ተሾመን ጨምሮ የተለያዩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ሥራዎቻቸውን ያቀርባሉም ተብሏል፡፡
በዕለቱ ደራሲያን፣ የኪነ ጥበብ ወዳጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በምርቃት ሥነ ስርዓቱ ላይ እንደሚታደሙም ታውቋል፡፡

Read 3640 times