የታዋቂው ድምጻዊ ዲበኩሉ ታፈሰ “የቱ ጋር ነህ” የተሰኘ አዲስ የሙዚቃ አልበም አርብ ታህሳስ 28 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ተገለጸ፡፡
አልበሙ 13 ዘፈኖችን ያካተተ ሲሆን በግጥም ይልማ ገ/አብ እና ያምሉ ሞላ ተሳትፈዋል፡፡ አልበሙን ለመሥራት አንድ ዓመት ነው የፈጀው ተብሏል፡፡
አልበሙ በኬኔትክ መልቲሚዲያ እና በዲበኩሉ ዩቲዩብ እንዲሁም በሁሉም ኦንላይን መተግበሪያዎች እንደሚለቀቅ ተጠቁሟል፡፡