Print this page
Saturday, 14 January 2023 10:29

ኢትዮ ቴሌኮም በስድስት ወራት ውስጥ 8.18 ቢሊዮን ብር ማትረፉን አስታወቀ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   ኢትዮ ቴሌኮም፤ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ  33.8 ቢሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን ያስታወቀ ሲሆን  8.18 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማስመዝገቡንም  ገልጿል።
ኩባንያው በስድስት ወር አፈጻጸሙ ያገኘው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ19.9 በመቶ እድገት እንዳለው የተጠቆመ ሲሆን፤ ዓምና  በመጀመሪያ መንፈቅ  ዓመት ያገኘው ገቢ 28 ቢሊዮን ብር ነበር።
በ2014 በጀት ዓመት 61.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ያስመዘገበው  ኢትዮ ቴሌኮም፤ በዘንድሮው ዓመት ገቢውን ወደ 75.05 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ ባለፉት ስድስት ወራት ያገኘው ገቢ የእቅዱን 96 በመቶ ያሳካ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ወ/ት  ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡
ኩባንያው  ባለፉት ስድስት ወራት የደንበኞቹን  ቁጥር  አምስት በመቶ በማሳደግ  70 ሚሊዮን ማድረሱ  ከትላንት በስቲያ  በስካይ ላይት ሆቴል፣ የ2015 የመጀመሪያ መንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙን  አስመልክቶ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጠቁሟል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም የደንበኞቹን ቁጥር በዚህ ያህል  መጠን ያሳደገው፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት መጀመርን ተከትሎ በተፈጠረው  “የውድድር ገበያ” ውስጥ መሆኑን ወ/ት ፍሬህይወት ታምሩ አመልክተዋል፡፡  

Read 1768 times
Administrator

Latest from Administrator