Saturday, 14 January 2023 10:31

በአሜሪካ ተጥለው የነበሩ ማዕቀቦችና አስገዳጅ ህጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸው ተገለጸ

Written by 
Rate this item
(4 votes)

በአሜሪካ የዴሞክራት 117ኛው ምክር ቤት፣ በኢትዮጵያ ላይ ተጥለው  የነበሩ ማዕቀቦች እንዲሁም  አስገዳጅ ህጎችና  ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ መሰረዛቸውን የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት  ትናንት  አስታወቀ፡፡
“አዲሱ የሪፐብሊካን 118ኛው ምክር ቤት ኮንግረሱን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠሩ በኢትዮጵያ ላይ ወጥተው የነበሩ የዴሞክራቶች ረቂቅ ህጎች ሙሉ በሙሉ ጊዜው ያለፈባቸው ሆነዋል” ብለዋል፤  የም/ቤቱ  ሰብሳቢ ዲያቆን  ዮሴፍ_ተፈሪ፡፡  
ባለፉት ሁለት ዓመታት ከሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ጋር ተያይዞ የአሜሪካ መንግሥት የተለያዩ ማዕቀቦች በመጣልና አስገዳጅ ህጎች በማውጣት በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር ሲጥር መቆየቱ  ይታወቃል፡፡  
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ አሁን በኢትዮጵያ በዜጎች ላይ እየተከሰተ ባለው የሰብአዊ መብት ጥሰት ዙሪያ   ከአዲሱ የኮንግረሱ መሪ ኬቨን ማካርቲ ሃላፊዎች ጋር  ንግግር መጀመሩን ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር  ገጹ አስታውቋል፡፡
 በተያያዘ ዜና፤ የኢትዮጵያ አሜሪካውያን የዜጎች ምክር ቤት  ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር በወቅቱ አገራዊ  ጉዳይ ላይ  ለመወያየት ልዩ  የልኡካን ቡድን ትላንት ከአሜሪካ ተነስቶ  እስራኤል መግባቱ ተጠቁሟል፡፡

Read 3144 times