Error
  • JUser: :_load: Unable to load user with ID: 62
Print this page
Saturday, 27 October 2012 10:56

የግጥም ጥግ

Written by 
Rate this item
(8 votes)

ምሕዋረ - ሥልጣን
አሳብ ምን ግድ አለው፤
ውስጥ ውስጡን ሳስበው ሳወጣው ሳወርደው
እሰየው ተመስገን ሥልጣን ነፍስ አወቀ
በማስተዋል ሚዛን ደቀቀ ረቀቀ፣
ጥንተ-ርስቱን አጥኖ በጊዜ ቁራስማ
ሥልጣን ነገር ገባው ለቀቀ አዲስ ዜማ፡፡
ይማረው! ያኑረው! ዲሞክራሲም ባተ
“እቴ አገርሽ የት ነው?” በቃ ተከተተ!
ኦርቢቱን አሹሮ ይዟል መወንጨፉን
አቅጣጫውን ሊያስስ ምዕራቡን ደቡቡን
ቅደመ አከራረሙ ተወግዟል በካህን
መነደፍ ጀምሯል በፈረቃ ደጋን!!
እንደቆመ ሰዓት በሰፈር ማለሙ
እዚያው መወዝወዙ ሆኖበት ድካሙ
ታሪክ ይሁን ብሏል የጥንቱ ክተራ
ይጓዝ በየአቅጣጫው ይዳረስ ወርተራ!
ከዓይን ያውጣህ እንግዲህ ሥልጣን እወቅበት
ለአንተም አይበጅህም ማደር በዋልክበት
ይልቁንስ ስልጣን አንተም ታሪክ ስራ
ራስህን አድን ከዘመን ኪሳራ፡፡
ደመቀ ወልዴ
መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም

Read 28637 times

Latest from