Saturday, 25 February 2023 13:46

127ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ማክሰኞ በተለያዩ መሰናዶዎች ይከበራል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(2 votes)

   አብርሃም ግዛው ኢንተርቴይመንትና የህትመት ስራዎች ድርጅት 127ኛውን የአድዋን ድል “ዝክረ አድዋ ኢትዮጵያዊነት” በሚል ርዕስ የፊታችን ማክሰኞ የካቲት 21 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በኢትጵያ ብሄራዊ ቴአትር በድምቀት ያከብራል። በእለቱ ስለ አንድነታችንና ጽናታችን እንዲሁም ስለታላቅ ህዝብነታችን የሚመሰክሩ አነቃቂ ንግግሮች፣ ግጥም፣ መነባንብ፣ በምሁራን የሚቀርቡ ጥናታዊ ጽሁፎች፣ ዲስኩርና ስታንዳፕ ኮሜዲ ለታዳሚ እንደሚቀርብ አዘጋጁ አብርሃም ግዛው ገልጿል።
በዚሁ የአደዋ ድል መታሰቢያ ልዩ መሰናዶ ላይ ቀሲስ መምህር ዘበነ ለማ፣ መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ፣ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፣ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ፣ ገጣሚ፣ ጸሐፌ ተውኔትና ባለቅኔ አያልነህ ሙላቱ፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ኦባንግ ሜቶ፣ የታሪክ መምህሩ ታዬ ቦጋለ፣ ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ፣ የፍልስፍና ምሁሩ ዮናስ ዘውዴ (ዶ/ር)፣ አርቲስት አበበ ባልቻ፣ አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ፣ አርቲስት እመቤት ወ/ገብርኤል እና ህፃን ቅዱስ እንቁባህሪ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡና ያልተጠበቁ ደንገቴ እንግዶች እንደሚገኙም ታውቋል። እንደአዘጋጁ ገለፃ መከላከያ ማርቺንግ ባንድ ትርኢት የሚያቀርብ ሲሆን በእናትና በአባት አርበኞች ፉከራና ሽለላ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል በሚቀርብ አጭር ተውኔት 127ኛው አድዋ ድል በድምቀት እንደሚዘከር ታውቋል።

Read 2126 times