እንኳን ለ127ኛው የዓድዋ ድል በአል በሰላም አደረስን። ወጣቶች በዚህ አጋጣሚ ብታነቡት ማለፊያ የምለውን መጻሕፍት ልጋብዝ።
1ኛ. አፄ ምንሊክ እና የኢትዮጵያ አንድነት
ደራሲ ተክለ ጻድቅ መኩሪያ
2ኛ. ዐድዋና ምኒልክ
ደራሲያን ፀሐፊ ገ/ሥላሴ እና ግራዝማች ዮሴፍ
3ኛ. የአድዋው ውሎ
የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም
4ኛ. አጤ ምኒሊክ
ደራሲ ጳውሎስ ኞኞ
5ኛ. ተክለ ሐዋርያት ተክለ ማሪያም
የህይወት ታሪክ
6ኛ. ከንግስት ሣባ እስከ ታላቁ አድዋ ድል
ደራሲ ብላቴን ጌታ ህሩይ ወ/ሥላሴ
7ኛ. የአድዋው ጀግና
ደራሲ ኤስ ጴጥሮስ ፔትሪዲስ
በዚሁ ጉዳይ ላይ ሌሎችም በርካታ መጻሕፍት መኖራቸውን ተረድታችሁ፣ ፈልጎ ማንበቡን ለእናንተው ልተው ። በድጋሚ እንኳን ለታላቁ የአድዋ በአል አደረሰን!
ኢትዮጵያ በነጻነቷ እንደኮራች ለዘለአለም ትኑር !
ሰላም በምድራችን ላይ ይስፈን!
(ደራሲ ዘነበ ወላ)
Published in
ህብረተሰብ