Sunday, 12 March 2023 10:17

2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የህዝብ ንብረት በሙስና ተዘርፏል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 • 226ሺ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ምርመራ እየተካሄደ ነው ተብሏል
     • 640 የሚሆኑ ሰዎች ከሙስና ጋር የተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸዋል
          
       ባለፈው ህዳር ወር ላይ ለተቋቋመው የብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴ በደረሱ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የህዝብ ንብረት በሙስና መዘረፉ መታወቁን የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አስታውቋል፡፡ የክልል ፀረ ሙስና ኮሚቴዎች ባደረጉት ምርመራ ያገኟቸው ውጤቶች ሲጨመሩ ጉዳዩ እጅግ የከፋ እንደሚሆንም ተገልጿል፡፡
በፌደራል፣ የክልልና የከተማ አስተዳደሮች ስር የተቋቋሙት የፀረ ሙስና አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ከትናንት በስቲያ በስካይ ላይት ሆቴል ባደረጉት ግምገማና በቀረበው ሪፖርት ላይ እንደተገለፀው ፤ ብሔራዊ ፀረ ሙስና ኮሚቴው ከተለያዩ አካላት በደረሰው ጥቆማ መሰረት ምርመራ አድረጎ ክስ የመሰረተባቸው ሰዎች 640 መድረሳቸውንና ለተለያዩ ወገኖች ያለ አግባብ ተላልፏል በተባሉ 226ሺ ካሬሜትር ቦታ ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት ዋና ዳይሬክተርና የአስተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ፤  ለብሐራዊ የፀረ ሙስና ኮሚቴው የደረሱ ጥቆማዎችን የማጥራትና ተጨባጭ በሆኑ ጥቆማዎች ላይ ምርመራ የማካሄድ ስራ እየተሰራ መሆኑን አመልክተው ለብሄራዊ ኮሚቴው ከደረሱ 759 ጥቆማዎች በ175 ያህሉ ላይ  ምርመራ ተጀምሯል ብለዋል፡፡ በ81 የክስ መዝገቦች በ640 ሰዎች ላይ ክስ መመስረቱንም አመልክተዋል፡፡
 2.2 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግስትና የህዝብ ሀብት በሙስና መዘረፉን ያመለከቱት ዳይሬክተሩ ፤ ይህ ቁጥር የክልል መንግስታትና የከተማ አስተዳደሮች ያዋቀሯቸው ኮሚቴዎች በምርመራ ያገኙትን ቁጥር ሲጨምሩበት በከፍተኛ መጠን ሊያድግ እንደሚችልም ገልፀዋል፡፡




Read 1702 times