Saturday, 25 March 2023 17:35

የህወሓት ከሽብርተኝነት መሰረዝ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(3 votes)

 “ውሳኔው አገሪቱን ወደለየለት ቀውስ የሚያስገባና ለአላዊነቷን የሚፈታተን ነው”
                            
        የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 13 /2015 ዓ.ም ባካሄደው “ልዩ ጉባዔ”  በህዝባዊ አርነት ትግራይ (ህውሐት) ላይ ተላልፎ የነበረውን የሽብርተኝነት ፍረጃ መሰረዙ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሞታል። “ውሳኔው አገሪቱን ወደለየለት ቀውስ የሚያስገባና ለአላዊነቷን የሚፈታተን ነው” ተብሏል።
ምክር ቤቱ ህውሐትን ከአሸባሪነት ለመሰረዝ ባካሄደው ጉባዔ ላይ ከተገኙት 280 የምክር ቤት አባላት መካከል 61 የሚሆኑት የህውሀሐትን ከሽብርተኝነት የመሰረዝ የውሳኔ ሃሳብ አጥብቀው ተቃውመውታል። አገሪቱ በተወሳሰበ ችግር ውስጥ ባለችበት ሁኔታና የፖለቲካ መረጋጋትና የዜጎች ደህንነት በጣም አሳሳቢ ሁኔታ ላይ በደረሰበት በአሁኑ ወቅት በህውሓት ላይ የተጣለውን የአሸባሪነት ውሳኔ አንስቶ ድርጅቱን ወደ ፖለቲካ ስርአቱ ማስገባት አደጋው ከፍ ያለ ነው ሲሉ የምክር ቤቱ አባላት ተቃውሞአቸውን አሰምተዋል። ከዚህ ውሳኔ በፊት ሊቀድሙ የሚገቡና የእኛን ውሳኔ የሚጠባበቁ በርካታ ጉዳዮች አሉ ያሉት የምክር ቤቱ አባላት መቅደም ያለበትን ጉዳይ ትተን ይህንን አሸባሪ ነጻ ማድረግ አገሪቱን ወደለየለት ቀውስ መስደድ ነው ብለዋል።
“ከጠቅላላው የምክር ቤት አባላቱ ብዛት ያላቸው ባልተገኙበትና ከተገኙም ከስልሳ በላይ ተወካዮች ተቃውሞአቸውን ባሰሙበት ሁኔታ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲፋቅ ውሳኔ መተላለፉ አግባብነት የለውም” ብሏል- አብን በመግለጫው።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በበኩሉ፤ “ህውሃት ትጥቅ ሙሉ በሙሉ ባልፈታበት፣ የሽግግር መንግስቱ በፌደራል መንግስቱ የበላይት ስር መቋቋሙ ባልተረጋገጠበት፣ ለተፈጸሙ ጥቃቶችና ወንጀሎች ተጠያቂነት በሌለበት፣ መከላከያ ሰራዊት ክልሉን ሙሉ በሙሉ ባልተቆጣጠረበት ሁኔታ ቡድኑን ከአሸባነት ፍረጃ ለመሰረዝ የተሰጠው ውሳኔ አግባብነት የሌለው ነው” ሲል ተቃውሞታል። ህውሃትን ከሽብርተኝነት ሰርዞ ከተጠያቂነት ነጻ ማድረግ ሊቀለበስ የማይችል ጥፋት ነው ያለው የኢዜማ መግለጫ፤ በዚህ ሳቢያ በህውሃት አማካኝነት ለሚደርሰው አገራዊ ጉዳት ዋንኛ ተጠያቂዎች ገዥው ብልጽግና ፓርቲና መንግስት ይሆናሉ” ብሏል።
ህውሃትን ከሽርተኝት መሰረዝ ዳግም ለአገርና ለህዝብ ስጋት መሆን የሚችልበትን ዕድል መስጠት ነው የሚሉት የፖለቲካ ምሁሩና የህግ ባለሙያው ዶ/ር አንተነህ ተስፋዬ፤ ውሳኔው አገሪቱን ወደለየለት አገራዊ ቀውስ የሚያስገባና ሉአላዊነቷን የሚፈታተን ነው ሲሉ ተችተውታል።
በመከላከያ ሰራዊታችን ላይ ያን የመሰለ ከባድ ክህደት ፈጽመው ከ3ሺ በላይ የመከላከያ አባላትን ጨፍጭፈው፣ ማይካድራ ላይ ዘርን መሰረት ያደረገ ያን የመሰለ ኢ-ሰብአዊ ወንጀል
ገዢው ብልጽግና ፓርቲ አብጫውን ድምጽ በያዘበትና በተቃዋሚ ፓርዎችና በግል ተመራጮች የተያዙ 16 ወንበሮች ብቻ ባሉበት በዚህ ምክር ቤት ተቃውሞ ገጠመው ከፎካካሪ  ከመንግሰት የቀረበው ውሳኔ ምክር ቤቱ የሽብርተኝነት መሰረዝ ውሳኔውን ካስተላለፈበት ልዩ ጉባዔው አንድ ቀን ብሎ አባላቱን ሰብስቦ ውይይት የሄደ ቢሆንም፣ ውሳኔውን የራሱ አባላት ጭምር መቃወማቸው ያልተለመደ ነው ተብሏል።
በምክር ቤቱ ተቃውሞአቸውን ካሰሙ ተቃዋሚ ፓርቲ አባላት መካከል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ተመራጭ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ አንዱ ሲሆኑ፤ ህውሃትን ከሽብርተኝነት መሰረዙ ውሳኔ ታሪካዊ ስህተት ነው ብለዋል።
“ህውሃት ከሽብርና ከጦርነት ፖለቲካ የመስራት ባህሪውን ባልቀየረበት ሁኔታ ድርጅቱን ከሽብርኝነት መሰረዝ ትልቅ ታሪካዊ ስህተት ነው” ብለዋል። ውሳኔው ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ ይችላል ወይ? የሚለው ጉዳይ በሚገባ ሊጤን ይገባዋ ያሉት ዶ/ር ደሳለኝ፤ ምክር ቤቱ የውሳኔ ሃሳቡን ጊዜ ወስዶ እንዲያስብበትና ለሌላ ጊዜ እንዲያሻግረው ጠይቀው ነበር።
ይህንኑ የምክር ቤቱን ውሳኔ ተቃውመው መግለጫ ካወጡ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል አብን እና ኢዜማ ቀዳሚዎቹ ሲሆኑ የሁለት ፓርቲዎች ውሳኔ ተገማች በሆነ ጊዜ ውስጥ አገሪቱን ለሌላ ዘርና ግጭት ጦርነት የሚያጋልጥ ነው ብለውታል። አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን ውሳኔውን ተቃውሞ ባወጣው መግለጫ፤ ህውሃት ትጥቅ ባልፈታበት፣ ይልቁንም አዲስ የታጣቂዎች ምልመላና ስልጠና እያደረገ ለጦርነት እየተዘጋጀ ባለበት ሁኔታ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝ ሃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው ብለዋል።
ፈጽመው፣ በአገር ሉአላዊነትና ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ወንጀል ፈጽመው ሲያበጁ፣ ሁሉንም ነገር እንዳልተፈጠረ ረስቶ ቡድን ከአሸባሪነትና መዝገብ መፋቅና የወንጀል ፈጻሚዎቹን ነፃ ማድረግ፣ ከባድ ህሊና ቢስነትና ኃላፊነት ጎደለው ውሳኔ ነው ብለውታል።
“ቡድኑ ዛሬም ነገም ከወንጀል ተግባሩ የሚታቀብ እንዳልሆነ ዛሬ ድረስ ከሚሰራቸው ስራዎች መረዳት እየተቻለ በምክር ቤቱ አባላትም ሆነ በመንግሰት የተሰጠው ውሳኔ በእጅጉ የሚያሳዝን ነው” በማለት ምሁሩ ነቅፈውታል። አክውም መንግስት በጉዳዩ ላይ ማብራሪያ ሊሰጥ ይገባል ብለዋል።
በህውሃት በኩል ውሳኔውን አስመልክቶ በይፋ የተሰጠ ዝርዝር መግለጫ ባይኖርም የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ውሳኔው በክልሉ ለሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር ጠቃሚ ነው ብለውታል።


Read 1951 times