Friday, 28 April 2023 00:00

ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ የመጀመሪያ የጥናትና ምርምር ጉባኤውን አካሄደ

Written by 
Rate this item
(1 Vote)


        በቢዝነስና ቴክኖሎጂ የትምህርት ዘርፎች ላይ አተኩሮ የሚሰራው ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ፤ የመጀመሪያውን የጥናትና ምርምር ጉባኤ፣ ትላንት ካዛንቺስ በሚገኘው ነጋ ሲሳ ቲሞል የኢንተርፕረነር ልማት ኢንስቲትዩት አዳራሽ አካሄደ።
ለጉባኤው ከ30 በላይ የሚሆኑ የጥንት ወረቀቶች ለውድድር ቀርበው የነበረ ሲሆን፤ በዕለቱ የተመረጡት ሰባት የጥናት ወረቀቶች መቅረባቸውን የሲልከን ቬሊ ኮሌጅ ስራ አስኪያጅ አቶ እሱባለው ታሪኩ ተናግረዋል። ጉባኤው በዋናነት አንተርፕረነርሽፕ፣ እንዲሁም ትምህርትና ቴክኖሎጂን ያማከለ ነው ተብሏል።የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ንጉሱ ጥላሁን በቦታው ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፣ ኢንተርፕረነርሽፕ፣ ትምህርትና ቴክኖሎጂ የማይነጣጠሉና ተቆራኝተው ውጤት የሚያመጡ እንደመሆኑ ኮሌጁ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ አተኩሮ ጉባኤውን ማዘጋጀቱ ትልቅ ተግባር ነው ብለዋል።
ሰባቱም የጥናት ወረቀቶች በአንተርፕረነርሽፕ በትምህርትና በቴክኖሎጂ ዙሪያ ያሉትን ተስፋዎችና ተግዳሮቶች ብሎም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚጠቁሙ መሆናቸው ተናግሯል።
ኮሌጁ በዚሁ ዙሪያ ከኢንተርፕረነርሽፕ ልማት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ የተፈራረመ ሲሆን የጥናትና ምርምር ጉባኤውም ከኢኒስቲትዩቱ ጋር በመተባበር መዘጋጀቱ ታውቋል።
ሲልከን ቫሊ ኮሌጅ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የቢዝነስና የቴክኖሎጂ የትምህርት ዘርፎች በማስተርስና በዲግሪ ደረጃ ትምህርትና ስልጠና እየሰጠ የሚገኝ እውቅ  ኮሌጅ ስለመሆኑም ተብራርቷል። በጉባኤው ላይ የተለያዩ ኮሌጆች አመራሮችና ምሁራን እንዲሁም የኢኒስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር፣ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

Read 1137 times