Print this page
Saturday, 29 April 2023 19:30

ከማህበራዊ ሚዲያ በጨረፍታእንግሊዝና ጋና የሚሻሙበት ቦክሰኛ?

Written by  ዋሲሁን ተስፋዬ
Rate this item
(0 votes)

በጠዋት ይነሳና ፡ በጋና ዋና ከተማ አክራ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች ወዳሉበት ቦታ በመሄድ ፡ የቀን ሰራተኛ ይፈልጉ እንደሆን ይጠይቃል ። ስራ ከተገኘ ቀኑን ሙሉ ሲሚንቶ ሲሸከም ፡ ኮንክሪት ሲያቦካ ፡ በአካፋ ሲዝቅ ፡ በባሬላ ሲሸከም ይውልና ፡ ሲደክመው ፡ የእሱ ብጤ ከሆኑ ሰዎች ጋር በጋራ በተከራዩት  መብራት የሌለው ጨለማ ክፍል ውስጥ ሄዶ ጎኑን ያሳርፋል ።
.ስራው ድካም አለው ፡ ተመጣጣኝ ክፍያም አያገኝም ፡ ሆኖም ሁሌም ህይወት ፊቷን አጥቁራበት እንደማትቀር ያስባል ። እና በአንድ ቃለመጠይቅ ላይ እንደገለፀው፤ አንድ ቀን ህይወት እንደምትስቅልኝ አውቅ ነበር ብሏል ።
ፍሪዚ ማክቦንስ ፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ፡ አንድ ቀን ባላሰበው አጋጣሚ እንግሊዝ የመሄድ እድል አጋጠመው፤  እዛም ሄዶ.ግን  ..  ቢያንስ ጋና ውስጥ እያለ የሚሰራው አይነት  የቀን ስራ እንደሚያገኝ አስቦ ነው ለንደን የደረሰው፡፡
ሆኖም  ነገሮች እንዳሰበው አልሆንለት አሉት።
እና ለምኖ እየበላ ፡ የማክዶናልድ መደብሮች በረንዳ ስር ማደር ጀመረ።
እንዲህ እንዲህ እያለ ፡ ቋንቋውን ፡ ሀገሩን እየለመደ ሲሄድ፤ በአንድ የነጻ ጂም ውስጥ ተመዝግቦ መስራት ጀመረ።
 ይህ ሁሉ ሲሆን  አንድም ቀን በህልሙም በውኑም ቦክሰኛ እሆናለሁ ብሎ አስቦ አያውቅም ነበር። እናም  በአንድ አጋጣሚ ለገቢ ማሰባሰቢያ ተብሎ በተዘጋጀ የቦክስ ግጥሚያ ላይ ተሳተፈ።
በዚህ ውድድርም በሚያስደነግጥ ሁኔታ ተጋጣሚውን በመርታት አሸነፈ። በዚያው እለትም የቦክስ አሰልጣኞች አይን ውስጥ ገባ።
ህይወት መልካም ጎኗን እንደምታሳየኝ ፣ አንድ ቀንም እንደምትስቅልኝ እያሰብኩ የኖርኩ ሰው ብሆንም፤ በዚህ መልኩ ህይወቴ ይለወጣል ብዬ ግን አስቤ አላውቅም፤ ነገር ግን ፈጣሪ መንገዶች እንዴት እንደሚጠርግ ያውቅ ነበርና፣ ባላሰብኩት መንገድ አስጉዞ እዚህ አድርሶኛል ይላል።
ከአመታት በኋላ፤ ዛሬ ላይ  ያ ፣ በፍቃደኝነትና በነጻ የውድድር መድረክ ፡ የቦክስ ጓንቱን አሟሽቶ ፡ የሪንጉን አለም የተዋወቀው ፍሪዚ ማክቦንስ፤ በተለያዩ የቦክስ ውድድሮች ላይ ባሳየው ብቃት አብዛኛውን ግጥሚያዎቹን በዝረራ እያሸነፈ፣ እንግሊዛዊው ማይክ ታይሰን የሚል ስም ለማግኘት በቃ፡፡  ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ  በእንግሊዝ ውስጥ በተካሄደው ታላቅ የቦክስ ውድድር ላይ ካሸነፈ በኋላ፣ ስሙ  ይበልጥ መግነን ጀምሯል።
በጋና የኮንስትራክሽን ግንባታዎች ላይ ባሬላና አካፋ በመዛቅ የድህነት ጥግ ውስጥ ይኖር የነበረው ፍሬዚ ማክቦንስ፤ አንድ ቀን የአለም ሻምፒዮን እንደሚሆን እያሰበ  ወደፊት መገስገሱን ቀጥሏል ።
 ዛሬ ጋና እና እንግሊዝ ይህን ሰው ይሻሙበታል። “እንግሊዛዊው ማይክ ታይሰን ሳይሆን ጋናዊው ነው” መባል ያለበት የሚል ውዝግብ  ሁሉ እየተነሳበትነው፡፡
ገንዘብና ዝና ከስር ከስሩ የሚከተሉት፣ በእንግሊዝና አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስሙ እየገነነ የመጣው የ32 አመቱ ፍሬዚ ማክቦንስ፤” በእጆቼ የሲሚንቶ መዛቂያ አካፋ ይዤ ፡ አንድ ቀን ህይወት እንደምትስቅልኝ አስብ የነበረው ነገር እንደተሳካ አውቄያለሁ፤ ባልታሰበ አጋጣሚ ወደ ቦክስ ስፖርት አለም የገባሁት እጅግ ዘግይቼ ነው ።  
ነገር ግን . ..... ዘግይቼ ጀመርኩ ማለት .... አልችልም ማለት አይደለም። አንተም የዘገየህ ቢመስልህ እንኳን ማድረግ አትችልም ማለት አይደለምና  የተሻለ ነገር ለመስራት
 የተሻለ ህይወት ለመኖር ዛሬውኑ ተነስ፡፡” ሲል ያነቃቃል፡፡





Read 557 times