Saturday, 06 May 2023 18:19

Oligohydramnios ….የሽርት ውሀ መጠን መቀነስ

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

ዶ/ር ጎበና ጤኖ ከአሰላ አርሲ ዩኒቨርሲቲ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻሊስት ናቸው፡፡ ዶ/ር ጎበና ጤኖ የተመለከቱት ተፈጥሮ ለሚጸነሰው ልጅ ምን ምቹ ሁኔታን እንደዳስቀመጠ እና በዚህም ምክንያት የተረገዘው ልጅ በሰላም ሊወለድ እንደሚችል ነው፡፡ ዶ/ር ጎበና በኢትዮያ የጽንስ ማህጸን ሐኪሞች ማህር 31ኛ አመታዊ ኮንፈረንስ ላይ ያቀረቡት ወረቀት እንደሚያሳየው የሽርት ውሀ ማለት የተጸነሰው ልጅ፡-
ተፈጥሮ ባመቻቸችለት ምቹ በሆነው ተንሳፋፊ መኝታው ማለትም በሽርት ውሀ ውስጥ እንደልቡ እንዲንሳፈፍ እንዲተኛ፤
በዚያ ምቹ በሆነው መኝታው ውስጥ ምንም እንዳይነካው ሆኖ እስከሚወለድበት ጊዜ ድረስ እንዲቆይና እንዲያድግ፤
በተመጣጠነ የሙቀት መጠን እንዲቆይ፤
ከውጭ ሊደርስት የሚችልን አደጋ የሚያስወግድ፤
በማህጸን እንቅስቃሴ ምክንያት ሊደርስ የሚችልን አደጋ የሚከላከልለት ተፈጥሮአዊ ስጦታ ነው፡፡
እንደ ዶ/ር ጎበና ማብራሪያ oligohydramnios የሚባል ከሽርት ውሀው ጋር በተገናኘ የሚከሰት ችግር አለ፡፡ እንደሚከተለው ብለውታል፡፡
የሽርት ውሀ በትክክል መኖሩ ለጽንሱ እንደተመቻቸ አልጋና ፍራሽ ከመቆጠሩም በላይ ሎሌች ብዙ ጥቅሞች አሉት፡፡ ለምሳሌ ጽንሱ እትብቱ ላይ እንዳይተኛ የማድረግ ተፈጥሮዊ ክንውን አሉት፡፡ ጽንሱ እትብቱ ላይ ከተኛ የመታፈንእና የመጎዳትን እድል ስለሚያስትል ይርት ውሀ ይሄንን በጣም ይከላከላል፡፡ ሰው ሙቀት ሲገጥመው በላብ መልክ እንደሚያ ስወግድ ሁሉ ጽንስ ደግሞ ሙቀት ሲኖረው ወደ ሽርት ውሀ በመላክ ሙቀታቸውን በዚያ ይቆጣጠራሉ፡፡ የሽርት ውሀ ጽንሱን ከኢንፌክሽን፤ከባክቴሪያ ከመሳሰሉት የመከላከል አቅምም አለው፡፡ አንዲት እናት የመውደቅ ወይንም በሆድዋ አካባቢ የመመታት አደጋ ቢደርስባት በቀላሉ ጽንሱን ጉዳት እንዳያገኘው የሽርት ውሀው ይከላከላል፡፡
ጽንሱ በሽርት ውሀ ውስጥ በመንቀሳቀሱ የእግር የእጅ የሌሎችንም አካላት እድገቱን የሚያገኝት አንዱ መንገድ ነው፡፡ አንዳዴም ወደውስጥ ወደሆድ እቃውም የሽርት ውሀው ስለሚገባ ለአንጀቱ መብሰል ፤ለሳንባው አተነፋፈስ እንዲላመድ ይረዳዋል፡፡ ለምሳሌ ጽንሱ 26 ሳምንት ከመድ ረሱ በፊት የሽርት ውሀው ቢጎዳ የሳንባው እድገት አይኖርም፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ ልጁ በሚወለ ድበት ጊዜ በውጭው አለም የሚጥመውን የመተንፈስ ሂደት ሊላመደውም ሊተገብረውም አይችልም፡፡ ይህ ከፍተኛ ጉዳትን ያስከትላል፡፡ ምጥ ሲመጣ የማህጸን መኮማተር መዘርጋት  ጽንሱ ጋ እንዳይደርስ ይከላከላል፡፡ የምጡ ኃይል የሚያደርሰው መኮማተርና መዘርጋት ጽንሱ ጋ የሚደርስ ከሆነ ልጁና እትብቱ አንድ ላይ እንዲጨመቅ ስለሚያደርገው ልጁ እንዲታፈን ያደርገዋል፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር ጽንሱ አየርም ሆነ ምግብ የሚያገኘው ከእቱ በእትብቱ በኩል ነው፡፡ ይህ ከሌለ እና oligohy- dramnios የሚባለው ችግር ከተከሰተ እትብቱ በሚታፈንበት ጊዜ የልብ ምቱ ሊቀየር ይችላል፡፡ ጽንሱ ካካውንም በዚያው ሊለቅ ይችላል፡፡ ካካውንም በመልቀቁ ምክንያት ተያያዘው የሚመጡ ችግሮች ሲኖሩ አንዱ የአተነፋፈስ ችግር ይሆናል፡፡ ባጠቃላይም ጽንሱ በመወለድ ወቅት ሕይወት ቢኖረውም ውሎ አድሮ ግን ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡
ዶ/ር ጎበና ጤኖ እንደገለጹት የሽርት ውሃው መጠን መቀነስ በሁለት በኩል ችግር ሊያስከትል ይችላል፡፡ አንዱ በእናት ሲሆን ሌላው በጽንሱ ላይ ነው፡፡
ለእናትየው ከሚያመጣቸው ችግሮች አንዱ በቀዶ ሕክምና የመውለድን እድል ከፍ ማድረግ ነው፡፡ የሽርት ውሀ መጠን የቀነሰባቸው እናቶች ከሌሎች ጋር ሲነጻፀሩ በ2.5 ያህል በቀዶ ህምና ለመውለድ እድላቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ ምጥ በሚመጣም ጊዜ ማህጸን በሚያከናውነው ግፊት ምክንያት ከእትብት ጋር በተያያዘ ጽንሱ የመታፈን እድል ስለሚኖረው በአፋጣኝ በቀዶ ሕክምና እንዲወልዱ ማድረግ ልጁ እዲተርፍ ያደርጋል፡፡
ሌላው ደግሞ እናቶች የሽርት ውሀቸው መጠን ከቀነሰ ምጥ እስኪመጣ መጠበቅ ስለማያ ስፈልግ የምጥ ማምጫ መድሀኒት ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ በእርግጥ የሽርት ውሀው መጠን ከቀነሰ በልጁ የልብ ምት መድከምን እና የመሳሰሉትን ችግር ስለሚያስከትል እንጂ የምጥ ማምጫው መድሀኒት በራሱ አርተፊሻል ምጥን የሚፈጥር በመሆኑ የእንግዴ ልጅን ከቦታው እንዲነቃነቅ ማድረግ፤ልጅ እንዲታፈን የማድረግ፤ደም እንዲፈስ የማድረግ ሁኔታዎች ሁሉ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡
Oligohydramnios ወይንም የሽርት ውሀ መጠን የቀነሰባቸው እናቶች በ7/ እጥፍ ከሌሎቹ ከፍ በሚል ሁኔታ የምጥ ማምጫ መድሀኒት ይወስዳሉ፡፡  
ሌሎቹ ተጎጂዎች ከጅምሩ ጀምሮ እንደተገለጸው ጽንሶቹ ናቸው ፡፡ ይህም ከላይ በተለያዩ መንገዶች እንደተገለጸው ሲሆን ለማስታወስ ያህል፡-  
Oligohydramnios የሚባለው ችግር ከተከሰተ ጽንሱ በእትብቱ በሚታፈንበት ጊዜ የልብ ምቱ ሊቀየር ይችላል፡፡ ጽንሱ ካካውንም በዚያው ሊለቅ ይችላል፡፡ ካካውንም በመልቀቁ ምክንያት ተያያዘው የሚመጡ ችግሮች ሲኖሩ አንዱ የአተነፋፈስ ችግር ይሆናል፡፡ ባጠቃላይም ጽንሱ በመወለድ ወቅት ሕይወት ቢኖረውም ውሎ አድሮ ግን ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡
በ31ኛው የኢትዮጵያ የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ የቀረበው oligohydramnios ከሽርት ውሀ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ቸግር እንደማሳያ የተለያዩ ሀገራት ጥናትን አጣቅሶአል፡፡ ታዲያ በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ዶ/ር ጎበና ሲገልጹ በእኛም አገር ቢሆን ጥናቶቹ ከተለያዩ ቦታዎች ናቸው፡፡
አንዱ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡ ሌላው መቀሌ አይደር ሆስፒታል የተሰራ ጥናት ነው፡፡ ይህንን ስናስተያይ የጎንደር (80.25)በጣም ከፍተኛ ሆኖ ይታያል፡፡ የመቀሌው (69.6 ) ሆኖ ተመዝግቦአል፡፡ ጥናቱ የተሰራበት ወቅት ግን የአምስት አመት ልዩነትን ስለሚያሳይ ይህን ያህል ከፍ ዝቅ ማለቱ ብዙም ላያስገርም ችላል፡፡
ቀደም ሲል የሚታወቀው አሰራር የልጁን የልብ ምት የሚደመጠው በጆሮ ነበር፡፡በአሁኑ ጊዜ ባለው አሰራር oligohydramnios ማትም የሽርት ውሀ እጥረት ከገጠመ እና በዚያውም ምጥ ከመጣ የጽንሱን የልብ ምት የምንከታተልበት መሳሪያ ስለመጣልን እንደቀድሞው ተጣድፈን ወደ (CS) ቀዶ ህክምና አንገባም፡፡ የጽንሱን የልብ ምት በመሳሪያው እየተከ ታተል እናትየው በምጥ የምትወልድበት እድል እንዲኖራት ከፍተኛ ጥረት እናደርጋለን ብለዋል ዶ/ር ጎበና፡፡
የሽርት ውሀ አራት ከረጢቶች አሉት፡፡ በእዚህ ከረጢቶች ውስጥ ያለው የሽርት ውሀ ድምር ከአምስት ሴንቲሜትር በታች ከሆነ ወይም ደግሞ አንዱዋ ከረጢት ከሁለት ሴንቲ ሜትር በታች ከሆነች ከፍተኛ የሽርት ውሀ እጥረት ደርሶአል ማለት ነው፡፡ እንደዚህ ያለው ክስተት ካጋጠመ አንዳንዶ ጋ የምጥ ማምጫ መድሀኒት አንዳንዶቹጋ ደግሞ በቀጥታ በቀዶ ህክምና የማዋለድ አገልግሎት ሊሰጥ ይችላል፡፡ ይሄም የሚያሳየው በአገራችን ባሉ የጤና ተቋማት በብሔራዊ ደረጃ በአንድ አይነት መንገድ አገልግሎቱ እንዲሰጥ የተደረገ ስምምነት ስለሌለ ወይንም ጋድ መመሪያ ስላልተሰጠ በየአካባቢው ለጽንሱም ሆነ ለእናትየው ቀና ነው የተባለው አገልግሎት ይሰጣል ማለት ነው፡፡ ይህ አሰራር በብዙ አገሮችም በኛ ሀገር ባለው ሁኔታ የሚተገበር ነው፡፡
ዶ/ር ጎበና ጤኖ ጥናቱን ያደረጉበትን ምክንያት ሲገልጹ ይህ ችግር በኢትዮጵያ ውስጥ በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ የሚያሳይ ጥናት ባለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ጥናት እንደመነሻ ጥናት እንዲያገለግልና ወደፊትም በብሔራዊ ደረጃ ባሉ የጤና ተቋማት ውስጥ የሚያጋ ጥሙትን ችግሮችን መፍትሔውን የሚጠቁሙ መንገዶችን መጠቆም ቢቻል ጥሩ ነው ብለዋል ዶ/ር ጎበና፡፡
በጥናት ወረቀቱ ላይ የሰፈረው የጥናቱ የወደፊት ጠቀሜታ፡-
Oligohydramnios በሚመለከት በጥናቱ የተገኙ ውጤቶች ለወደፊቱ በጤና ተቋማት ላይ ተመስርተው ለሚሰሩ ጥናቶች እንደመረጃ ያገግላል፡፡
ከ oligohydramnios ጋር በተያያዘ በብሔራዊ ደረጃ ከማህጸንና ጽንስ ጋር በተያያዘ ለሚወጡ መመሪያና ፖሊሲዎች አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
Oligohydramnios የሽርት ውሀ እጥረት እና ምጥ ጋር በተያያዘ የተሸለ ጥናት ለማድረግ እና የእናቶችንና የጨቅላዎችን ደህንነት ለማሻሻል ወይም ለማረጋገጥ የሚያስችል ሲደረግ እንደመነሻ ያገለግላል ብለዋ ዶ/ር ጎበና ጤኖ፡፡

Read 363 times