Print this page
Saturday, 20 May 2023 15:16

ከ20 በላይ በጉዞ ላይ የሞቱ ሴት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስክሬን ተገኘ

Written by  መታሰቢያ ካሳዬ
Rate this item
(0 votes)

 መነሻቸውን ከየመን በማድረግ ወደ ሳኡዲ በመጓዝ ላይ የነበሩ ከ20 በላይ ኢትዮያውያን ሴት ስደተኞች አስክሬን መገኘቱ ተገለፀ። ቢቢሲ ከስፍራው አረጋገጥኩ ብሎ ባሰራጨው ዜና  እንደተገለጸው፤ ስደተኞቹ ህይወታቸው ያለፈው በከፍተኛ ድካምና ረሃብ ነው።
የሟቾቹን አስከሬን የያዘ ዘግናኝ ምስል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጨ መሆኑን ያመለከተው ቢቢሲ፤ ምስሉ መቼና የት እንደ የተቀረፀ ለማረጋገጥ አልቻልኩም ብሏል። ስደተኞቹ በጦርነት ውስጥ ከምትገኘው የመን ወደ ሳውዲ አረቢያ በእግር ሲጓዙ እንደነበርና እጅግ በበዛ ረሃብና ድካም ሳቢያ ህይወታቸው ማለፉን ገልጿል። የስደተኞቹ አስክሬን የተገኘው በየመንና ሳውዲ መካከል በሚገኘው ራጎ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን የጠቆመው የቢቢሲ ዘገባ፤ ሟቾቹ ግንቦት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ሳውዲ አረቢያ ለመሄድ ጉዞ መጀመራቸውን ጠቁሟል።  የአብዛኛዎቹ አስክሬን አለመቀበሩንና ጥቂቶቹን በአካባቢው የነበሩ ስደተኞች እንደቀበሯቸውም ተዘግቧል። በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ ሳኡዲ አረቢያ ለመግባት እጅግ አደገኛ የሆኑ መንገዶችን የሚጠቀሙ ሲሆን ይኸው በየመንና ሳውዲ መካከል የሚገኘው ራጎ የተባለው ስፍራ ከዚህ ቀደምም የበርካቶቹ ህይወት እንደበላ መረጃዎች ይጠቁማሉ።


Read 2245 times