Print this page
Saturday, 20 May 2023 20:49

"ባክ ቱ ስኩል" አውደርዕይ በአብርሆት ቤተመጻህፍት እየተካሄደ ነው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
ትኩረቱን በትምህርት፣በቴክኖሎጂና ኢንፎርሜሽን ላይ ያደረገው 5ኛው "ባክ ቱ ስኩል" የተሰኘ አውደርዕይ፣ በዛሬው ዕለት ረፋዱ ላይ በአብርሆት ቤተመጻህፍት ተከፍቷል፡፡
ዛሬና ነገ ለሁለት ቀናት የሚካሄደውን አውደርዕይ፤ ኑስፌር አፌርስ፣ ከዓለማቀፍ አጋሩ ኢቨንትስ አርክቴክት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጀው፡፡
በአውደርዕዩ ላይ የአገር ውስጥና የውጭ አገራት ት/ቤቶች፣ ዩኒቨርስቲዎችና የሥልጠና ተቋማት እየተሳተፉበት ሲሆን፤ከእነዚህም መካከል ከጃፓን 700 ዩኒቨርስቲዎችን ወክለው የመጡ እንደሚገኙበት ታውቋል፡፡
በኢትዮጵያ ብቸኛው የትምህርት አውደርዕይ እንደሆነ የተነገረለት ይኸው "ባክ ቱ ስኩል"፤ የትምህርት ተቋማትንና ዕድሎችን ከተማሪዎችና መምህራን ጋር የሚያገናኝ መድረክ ነው ተብሏል፡፡
በነገው ዕለት የሚጠናቀቀው አውደርዕዩ፣ በኦንላይን አዳዲስ መረጃዎች እየታከሉበት ለአንድ ዓመት ክፍት ይሆናል ይዘልቃል ተብሏል፡፡
Read 1967 times
Administrator

Latest from Administrator