Saturday, 03 June 2023 13:19

በአማራ ክልል በጦርነቱ 522 ቢ. ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል

Written by  መታሰቢያ ሳሣዬ
Rate this item
(2 votes)

      የክልሉ የ2015 ዓመት አጠቃላይ በጀት ከ100 ቢሊዮን ብር ያነሰ ነው
             
         በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ጦርነትና ግጭት ተከትሎ፣ በአማራ ክልል የደረሰው የንብረት ውድመት 522 ቢሊዮን ብር መድረሱ ተገለፀ፡፡ የክልሉ መንግስት ከወራት በፊት ባወጣው ሪፖርት በክልሉ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የደረሰው የንብረት ውድመት 294 ቢሊዮን ብር መሆኑን ገልፆ ነበር፡፡
በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ፅ/ቤት አከናወንኩት ባለው ጥናት መሰረት፤ በክልሉ በጦርነትና በግጭቱ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡ ጦርነቱ ከግማሽ ትሪሊዮን ብር በላይ ንብረትን አውድሟል ያለው የፅ/ቤቱ ሪፖርት፤ ይህም በአገሪቱ ታሪክ እጅግ ከፍተኛው ነው ብሏል፡፡ የአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት፣ ይፋ ያደረገው ሪፖርት፣ ለሁለተኛ ጊዜ በተጠና ጥናት የተገኘ ውጤት መሆኑንም አመልክቷል፡፡ የክልሉ መንግስት ከወራት በፊት በክልሉ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ የደረሰው የንብረት ውድመት 294 ቢሊዮን ብር የሚገመት እንደሆነ አመልክቶ ነበር፡፡ ይህንኑ በክልሉ መንግስት የተደረገውን ጥናት ተከትሎ በፅ/ቤቱ በተደረገ አጠቃላይ ጥናት፣ በክልሉ በጦርነቱ የደረሰው የንብረት ውድመት ከ522 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት ተመላክቷል፡፡የአማራ ክልል የ2012 ዓ.ም አጠቃላይ በጀት ከ100 ቢሊዮን ብር ያነሰ መሆኑን ያመለከተው ሪፖርቱ፤ የክልሉ መንግስት ከበጀቱ ላይ አብቃቅቶ በመደበው አንድ ቢሊዮን ብር የመልሶ ማቋቋም ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል፡፡ ጦርነቱ በፈጠረው ጦስ እስከ አሁን ግማሽ የሚሆነው የክልሉ ህዝብ በችግር ላይ እንደሆነም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል፡፡  

Read 1222 times