Saturday, 03 June 2023 20:05

የህብረት ባንክ “ይቆጠቡ ይሸለሙ” የዕጣ አሸናፊዎች ተሸለሙ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

   ህብረት ባንክ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ከፍ ለማድረግና የተቀማጭ ገንዘቡን ለማሳደግ ለሦስተኛ ጊዜ ባካሄደው  “ይቆጠቡ፣ ይቀበሉ፣ ይመንዝሩና ይሸለሙ” መርሃ ግብሩ ተሳታፊ የሆኑ የዕጣ አሸናፊዎችን ትናንት ግንቦት 25 ቀን 2015 ዓ.ም በባንኩ ዋና መ/ቤት ሸለመ።
የዕጣው አሸናፊዎች ከሞባይል ቀፎ እስከ መኪና ድረስ ነው የተሸለሙት። በዚህም መሰረት፡- የቤት አውቶሞቢል አቶ ፀጋዘአብ ምንውዬለት ናቸው። አቶ ክንፈ ሃይሉና አቶ ግርማ ታደሰ አብዲሳ ደግሞ ባለ 3 እግር ተሸከርካሪ ተሸልመዋል።
 አቶ ግርማ ኤጀርሳና አቶ ይልማ የተባሉ ደንበኞች የውሃ መሳቢያ ሞተር ሲያሸንፉ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ያሸነፉት ደግሞ አቶ ሁሴን ኡመር መሃመድና አቶ እሸቱ ሽፈራው ናቸው።በተመሳሳይ አቶ ስለው ወርቁ ወ/ሚካኤልና አቶ ደርቤ ሳቀው አለማየሁ ፍሪጅ (ማቀዝቀዣ) ተሸልመዋል።
ሌሎች የባንኩ ደንበኞችም ስማርት ቴሌቪዥን፣ የውሃ ማጣሪያና ዘመናዊ የስልክ ቀፎ አሸንፈው ሽልማቶቹን ከባንኩ ከፍተኛ አመራሮች እጅ ተረክበዋል።Read 470 times