ክፍል ሁለት የጥበብ መሰናዶ
ዛሬ በሀገር ፍቅር
ይካሄዳል
በገጣሚ አስታውሰኝ ረጋሳና ጓደኞቹ የተሰናዳው “አንድ ለመንገድ” ክፍል ሁለት የኪነ-ጥበብ መሰናዶ ዛሬ ሰኔ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ጀምሮ በሀገር ፍቅር ቴአትር ይካሄዳል። በዕለቱ ግጥም ሙዚቃ የኮሜዲ ሥራና ሌሎችም ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች የሚቀርቡ ሲሆን ገጣሚያኑ አስታውሰኝ ረጋሳ፣ ዘውድአክሊል፣ ፌቨን ፋንጮ፣ ኮሜዲያን ምናለ ያረጋል፣ አማኑኤል የሺወንድ፣ አቤል ሀጎስ እንዳልክ አሰፋ፣ ድምጻዊያኑ ዳግም፣ ፍቅሩ (ዳኒ)፣ አክሊሉ፣ መላኩ እና አርቲስት ሰለሞን ሙሄ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡም ታውቋል። በዚህ ልዩ የኪነ-ጥበብ መሰናዶ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው 150 ብር እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል።
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና