Saturday, 29 July 2023 12:25

”ራስህን የመሆን ምስጢር” መጽሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

    በእየሩሳሌም ሹምዬ የተዘጋጀው ”ራስህን የመሆን ምስጢር” የተሰኘው መጽሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡
ደራሲዋ በመጽሐፉ ጀርባ ላይ ባሰፈረችው መልዕክት፤ ”ባለፉት አሥርት ዓመታት የህይወት ሂደቴ ውስጥ የተማርኩት፣ የተገነዘብኩት፣ የሄድኩበትና ለዛሬው በነጻነቴ ልክ የሚሰፈረው፣ በነጻ ፍቃዴና ፍላጎቴ፣ በእስትንፋሴ ሙሉ የማጣጥመው የህይወት ምዕራፌ ካደረሱኝ ምስጢሮች መካከል የመጀመሪያዋን ምዕራፍ በዚህ መንገድ ከትቤ እንደኔ የህይወት ሂደታችሁ ግራ ላጋባችሁ፣ ላንገደገዳችሁና ገና አዲስ የህይወት ምዕራፎቻችሁ ሙሽሮች ለሆናችሁ ሁሉ አንድ ብዬ አቀረብኩላችሁ፡፡” ብላለች፡፡
መጽሐፉ በስድስት ምዕራፎች የተከፋፈለ ሲሆን፤ በ100 ገጾች ተቀንብቧል፡፡ በየምዕራፎቹ ከተካተቱት ርዕሶች መካከልም፡- ”ራስህን መሆን” ፣ ”ራስህን ማወቅ” ፣ ”ለህልምህ ሙሉ ራስህን መስጠት” ፣ ”ስኬታማነት” ፣ ”የራስህን ዓለም መምራት” ፣ ”በብቃትና በጥበብ መመራት” ፣ “ጠባቂነትን ማስወገድ“  ወዘተ የሚሉ ይገኙበታል፡፡
”ራስህን የመሆን ምስጢር” መጽሐፍ፤ ለአገር ውስጥ በ450 ብር፣ ለውጭ አገራት ደግሞ በ30 ዶላር ለገበያ ቀርቧል፡፡

Read 765 times