Saturday, 29 July 2023 12:20

“ተጓዥ ኪነ-ጥበብ” መሰናዶ ዛሬ ይካሄዳል

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(0 votes)

  “ተጓዥ ኪነ ጥበብ” የተሰኘ የኪነ ጥበብ መሰናዶ ዛሬ ሀምሌ 22 ቀን 2015 ዓ.ም አራት ኪሎ በሚገኘው አምባሳደር ሞል ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ አዘጋጆቹ ገለፁ፡፡ በእለቱ ግጥም፣ መነባንብ፣ ድራማ፣ ቴአትር፣ ሙዚቃ፣ ውዝዋዜ፣ ሰርከስ፣ ሥዕልና ሌሎችም ኪነ-ጥበባዊ መሰናዶዎች ይቀርባሉ ተብሏል፡፡ በዚህ የኪነ ጥበብ መሰናዶ ላይ ጉንጉን የባህል ሙዚቃ ባንድና ግሩቭ ባንድ ዝግጅቱን የሚያጅቡ ሲሆን፣ ሰለሞን ሽፈራው፣ አይ ቲሞቲ፣ እስካለ ልቅና፣ ህሊና ሽፈራው ነፃነት ሱልጣን(ጉርበዮ) ዊሳም አህሳንና የውብዳር በቀለ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡ ታውቋል፡፡ በዚህ ደማቅ የኪነጥበብ መሰናዶ ላይ ለመታደም የመግቢያ ዋጋው አንድ መቶ ብር (100) ሆኖ መተመኑንም አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡

Read 675 times