Saturday, 29 July 2023 12:27

የእስከዳር ግርማዬ “ናፍቆት” መፅሀፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዩሴፍ
Rate this item
(1 Vote)

   የደራሲ ተዋናይትና ፕሮዲዩሰር እስከዳር ግርማይ 3ኛ ሥራ የሆነው “ናፍቆት” መፅሀፍ ለንባብ በቃ፡፡ በበርካታ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮሩ የአጫጭር ልብወለዶች ስብስብ የሆነው “ናፍቆት” በማህበራዊ፣ በፍቅርና በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚያጠነጥኑ ሀሳቦች ማካተቱም ታውቋል፡፡ በ162 ገጽ የተቀነበበው መጽሀፉ በ300 ብር ለገበያ ቀርቧል፡፡ የመጽሀፉ ደራሲ እስከዳር ግርማይ ከዚህ ቀደም “ኢትዮጵያዊ ሀገሩ የት ነው” እና “የፈረንጅ ሚስት” የተሰኙ መፅሀፍትን ለንባብ ማብቃቷ የሚታወስ ሲሆን የፊልም ፅሁፍ ደራሲ፣ ተዋናይት፣ ሞዴልና ፕሮዲዩሰር ስትሆን ከዚህ ቀደም በ”ሰውነቷ” ፊልም ላይ በፕሮዲዩሰርነትና በተዋናይነት እንዲሁም በ”ጥቁር እንግዳ” ፊልም ላይም በፅሁፍና በትወና ተሳትፋለች፡፡ እስከዳር ግርማይ በባህሬን  የክብር ቆንስል በመሆን አገሯንና ህዝቧን እያገለገለች እንደምትገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡

Read 1183 times