Friday, 01 September 2023 13:04

የጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ “ስለእኛ” አዲስ መፅሐፍ ለንባብ በቃ

Written by  ናፍቆት ዮሴፍ
Rate this item
(0 votes)
የአንጋፋዋ ጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ ሁለተኛ ስራ የሆነው “ስለእኛ” መፅሐፍ ሰሞኑን ለንባብ በቃ፡፡ መፅሐፉ በዋናነት በፋሽን፣ በውበትና በአኗኗር ዘይቤ ላይ የሚያተኩር ሲሆን፤ ለአንባቢና ለተጠቃሚ በሚመች መልኩ ተዘጋጅቶ ለንባብ መብቃቱ ተናግሯል፡፡
መፅሐፉ በቤት ውስጥ ውበትን ለመንከባከብ የሚረዱ ተፈጥሯዊ ዘዴዎችን የሚጠቁምና ተለዋዋጭ በሆነው የፋሽን ዓለም ለሁኔታዎች ካለን አመለካከት፣ ከቁመና፣ ከእድሜና ከውሏችን ጋር የተጣጣመ የአለባበስ ስታይል (ዘይቤ) እንዴት መምረጥ እንደምንችል በቀላል አቀራረብና በምስል የተደገፈ ገለፃ የሚሰጥ ነውም ተብሏል፡፡
በ206 ገጾች የተቀነበበው መሐፉ፤ በጃፋር መፅሀፍት መደብር፣ በተመረጡ የውበት መጠበቂያ ማእከላትና ቡቲኮች እንደሚሸጥም ለማወቅ ተችሏል፡፡
ደራሲና ጋዜጠኛ ኤልሳ አሰፋ፣ ከዚህ ቀደም በልጆች አስተዳደግ ላይ ያነጣጠረ መፅሐፍ ለንባብ ማብቃቷ የሚታወስ ሲሆን፤ በብስራት ሬዲዮ በምታዘጋጀው በውበት ጤናና ፋሽን ላይ ያተኮረ “ስለእኛ” የሬዲዮ ፕሮግራሟ ይበልጥ ትታወቃለች፡፡
የቴሌግራም ቻናልችንን በመቀላቀል የአዲስ አድማስን መረጃ ይከታተሉ…
 
Read 1425 times