የድምፃዊ ብስራት ሱራፌል አዲሱ “ማለፊያ” የተሰኘ የሙዚቃ አልበም የፊታችን ቅዳሜ፣ ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሸራተን አዲስ ጋዝላይት እንደሚመረቅ ተገለጸ፡፡
የግጥምና ዜማ ደራሲ እንዲሁም ፕሮዱዩሰር የሆነው ድምፃዊ ብስራት ሱራፌል፣ በቅርቡ ለአድማጭ ያደረሰው ሁለተኛ የሙዚቃ አልበሙ፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትና ተቀባይነት እንዳገኘ ይነገርለታል፡፡
በርካታ የግጥምና ዜማ ሥራዎችን ለሌሎች ድምጻውያን በመሥራትና በመስጠትም የሚታወቀው ድምጻዊው፤ እስካሁን ከሰጣቸው መካከልም ድምፃዊት ኩኩ ሰብስቤ፣ ሄለን በርሄ፣ ቬሮኒካ አዳነ፣ ሐይማኖት ግርማ ይጠቀሳሉ፡፡
የ“ማለፊያ” አልበም የምረቃ ሥነስርዓት፤ ታዋቂ ድምጻውያን፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎችና ታዋቂ ግለሰቦች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የአርቲስቱ አድናቂዎች በተገኙበት ይከናወናል ተብሏል፡፡
Published in
ኪነ-ጥበባዊ ዜና