Saturday, 21 October 2023 21:09

በኢትዮጵያ አትሌቶች የተያዙት 19 የዓለም ሪከርዶች

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(2 votes)

 14 በሴቶች 5 በወንዶች ተመዝግበዋል


      በዓለም አትሌቲክስ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተመዘገቡ የዓለም ሪከርዶች ብዛት 19 ደርሷል። እነዚህ 19የዓለም ሪከርዶች በትራክ፤ በጎዳና ላይ ሩጫና በቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድሮች የተያዙ ሲሆን  14በሴቶችና5 በወንዶች ተመዝግበው ይገኛሉ።የሪከርዶቹ ብዛት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ኃያልነት ያመለክታle። በተለይ በሴቶችምድብ ባለፉት3 አመታት የተመዘገቡ ሪከርዶች አስደናቂናቸው። በወንዶች የ5ሺ ሜትር፤ የ10 ሺ ሜትርና የማራቶን ሪከርዶች በኡጋንዳና በኬንያ አትሌቶች ቁጥጥር ውስጥ መግባታቸው ያስቆጫል።ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም አትሌቲክስ ላይ በኦፊሴላዊ ደረጃ ያስመዘገቧቸው 19 ሪከርዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል
     ትግስት አሰፋ በማራቶን 2:11:53 በ2023 በርሊን ማራቶን
ጉዳፍ ፀጋይ በ5ሺ ሜትር 14:00.21 በ2023 ዳይመንድ ሊግ ዮጂን አሜሪካ
ድርቤ ወልተጂ በ1 ማይል ጎዳና 4:20.98 በ2023 የዓለም የጎዳና ሩጫ ሻምፒዮና ሪጋ ስሎቫኪያ
ሰንበሬ ተፈሪ በ5ኪሜ ጎዳና (በሴቶች ብቻ) 14:29 በ2021 ሔርዞግንራክ ጀርመን
እጅጋየሁ ታዬ በ5  ኪሜ ጎዳና ( ከወንድ አሯሯጮች ጋር)  14:19 በ2021 ባርሴሎናስፔን
ለተሰንበት ግደይ በ10ሺ ሜትር 29:01.03 በ2021 ሔንግሎ ሆላንድ
ቃልኪዳን ገዛሐኝ በ10 ኪሜ ጎዳና  (በሴቶች ብቻ) 29:38 በ2021 ጄነቫ ስዊዘርላንድ
ያለምዘርፍ የኋላው በ10ኪሜ ጎዳና ( ከወንድ አሯሯጮች ጋር) 29:14 በ2022 ካስተሎን ስፔን
ለተሰንበት ግደይ በግማሽ ማራቶን ( ከወንድ አሯሯጮች ጋር) 1:02:52 በ2021 ባርሴሎና ስፔን
አማኔ በሪሶ በ50 ኪ ሜ 3:00:30 በ2023 ጂኪይባራህ ደቡብ አፍሪካ
ጉዳፍፀጋይ በ1500 ሜ (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 3:53.09 በ2021 ሌይቪን ፈረንሳይ
ገንዘቤ ዲባባ በ1 ማይል (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 4:13.31 በ2016 ስቶክሆልም ስዊድን
ገንዘቤ ዲባባ በ3000  ሜትር (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 8:16.60 በ2015 ስቶክሆልም ስዊድን
ገንዘቤ ዲባባ በ5000 ሜትር  (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 14:18.86 በ2014 ስቶክሆልም ስዊድን
በሪሁ አረጋዊ በ5 ኪሜ ጎዳና 12:49 በ2021 ባርሴሎና ስፔን
ለሜቻ ግርማ በ3ሺ ሜትር መሠናክል 7:52.11 በ2023 በፓሪስ ፈረንሳይ
ዮሚፍ ቀጀልቻ  በ1 ማይል (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 3:47.01 በ2019 ቦስተን አሜሪካ
ለሜቻ ግርማበ3ሺ ሜትር (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 7:23.81 በ2023 ሌይቪን ፈረንሳይ
ቀነኒሳ በቀለበ5ሺ ሜትር (የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ) 12:49.60 በ2004 በርሚንግሃም እንግሊዝ


Read 1121 times