ከካንሰር ህመም ሁሉ በብዛት የጡት ካንሰር በአንደኛነት ደረጃ የሚታይ በሽታ ነው:: ገዳይነቱም አያጠያይቅም ምክንያቱም የጡት ካንሰር በሴቶች ላይ ለሚከሰቱት የካንሰር ሞት መንስኤ ከሳንባ ካንሰር ቀጥሎ ሁለተኛው ነው።
ማሞግራም የጡት ኤክስሬይ ምስል ነው። ዶክተሮች የጡት ካንሰር የመጀመሪያ ምልክቶችን ለመፈለግ ማሞግራም ይጠቀማሉ። መደበኛ ማሞግራም ዶክተሮች የጡት ካንሰርን ቀድመው ለማግኘት የሚደረግ ምርመራ ነው፣ አንዳንዴም እስከ ሶስት አመት ድረስ አስቀድሞ የጡት ካንሰርን ለማወቅ ያስችላል::
በምርመራው ወቅት በምስሉ ላይ እንደሚታየው ባለሙያው ጡትዎን በሁለት የፕላስቲክ ሳህን መሀል ያስቀምጣል. ሳህኖቹ ኤክስሬይ በሚወሰድበት ጊዜ ጡቱን ጠፍጣፋ ያደርጋሉ እናም አንዳንድ ጫናዎች እና ህመሞች ይሰማዎታል::
የጫናው ህመም መጠን በተወሰነ መልኩም ቢሆን ስለሚጨምር ይህን ምርመራ በወር አበበ ስዓት ማድረግ አይመከረጠርም:: በተጨማሪም ዲኦድራንት ወይም ሽቶ የመሳሰሉትን ምርቶች መጠቀም በኤክስሬይ ላይ እንደ ነጭ ነጠብጣቦች በመፍጠር የምርመራውን ተዓማኒነት ስለሚቀንሱ አይመከሩም።
በእድሜ ከ40 በላይ የሆኑ ሴቶች በ1-2 አመት ልዩነት የማሞግራም ምርመራ ማድርግ ይኖርባቸዋል:: ማሞግራም ዋነኛ የቅድመ ካንሰር ምርመራ ቢሆንም ሌሎች አማራጮም መኖራቸውን መዘንጋት የለበትም:: በዳበሳ የሚደረግ የቅድመ ካንሰር ምርመራ በሀኪም ዘንድ ቀርቦ ወይም በ'ራስ በመዳበስ ገና እየጀመረ ያለ እጢ ማግኘት ሌላኛው አማራጭ ነው:: ልዩነቱ ማሞግራፊ በእጅ ላይ ለመሰማት በጣም ትንሽ የሆኑ እጢዎችን ሊያገኝ ይችላል። ይህም ማሞግራፊን ተመራጭና ተዓማኒ ያደርገዋል:: እድሜ ከ40 በታች ከሆነ የጡት አልትራሳውንድም 3ኛው አማራጭ ነው::
ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ ነውና ነገሩ ይህን የማሞግራፊ ምርመራ ማድርግ አስፈጊ ነው:: በኢትዮጵያ ቢያንስ በአዲስ አበባ ደረጃ የአገልግሎቱን ሁኔታ ለመግለፅ የክል በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ደረጃ ክፍያው 360ብር ነው::
ይህ ምርመራ በተጨማሪም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል እና በተለያዩ የግል ተቋማት ይሰጣል:: በእንሹራንስ በኩልም ምርመራውን በነፃ ማድረግ ይቻላል:: በአረብ ሀገር ያላቹ እህቶቼም በአቅራቢያ በሚገኝ የህክምና መእከል በመቅርብ ምርመራውን ማድርግ ጠቀሜታው የጎላ ነው::
Dr. Zerihun Gelashe Hailu
Friday, 27 October 2023 00:00
ከካንሰር ህመም ሁሉ በብዛት የጡት ካንሰር በአንደኛነት ደረጃ የሚታይ በሽታ ነው::
Written by Administrator
Published in
ዋናው ጤና