Saturday, 04 November 2023 00:00

አዲስ ዘመን ድሮ

Written by 
Rate this item
(0 votes)

ታሪክ ማንበብ  ያ ል ኖ ሩ በ ት ን ዘመን ያስኖራል››
ይባላል።ይህ ማለት እኛ ባልነበርንበት ዘመን የነበረውን ሁነት ይነግረናል ማለት ነው።አዲስ ዘመን ጋዜጣ የተለያዩ ዘመናት የየዕለት ሁነት ሰንዶ ያስቀመጠ የ82 ዓመታት ታሪክ ነው።ጋዜጣው በሰነዳቸው መረጃዎቹ ያልነበርንበትን ዘመን እንድንኖረው ያደርገናል።በዚያ ዘመን፤ የመንግስት አስተዳደር እና የማህበረሰቡ ሥነ ልቦና ምን ይመስል እንደነበር፣ ምን ነውር ምንስ አስገራሚ እንደሚሆን፣ በዘመኑ የነበሩ ህግና
ደንቦች፣ የኑሮ ሁኔታ እና የመሳሰሉትን ያሳየናል።በማስታወቂያዎች፤ በዘመኑ የነበረውን የገበያ፣ የቅጥር፣ የሚከለከሉና የሚፈቀዱ ነገሮችን ይጠቁመናል።በዜናዎች ደግሞ የዘመኑን ክስተቶች ያሳየናል።እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል።በዘመኑ ጋዜጣ ላይ ይወጡ የነበሩ ዘገባዎችን፣ ማስታወቂያዎችን፣ ወዘተ. ዛሬ ላይ ሆነን ስናነባቸውና ስንመለከታቸው ‹‹አሁን ይሄ ዜና ይሆን ነበር? ጋዜጣ ላይ መውጣት ነበረበት?›› የሚያሰኙ ነገሮችን እናገኛለን።ይህ ሲያጋጥመን ልብ ማለት ያለብን የዘመኑን ባህሪ ነው።ያኔ እንደዛሬው የማህበራዊ መገናኛ አውታሮች እንዲሁም ተፎካካሪ ጋዜጦችና መጽሔቶች አልነበሩም፡፡

እናም ከአፋልጉኝ ማስታወቂያ ጀምሮ የጠጅ ቤት እና የአረቄ ቤት ወሬዎች ሳይቀር በጋዜጣው ላይ ልናገኝ እንችላለን።ምክንያቱም በወቅቱ አስገራሚ ከነበሩ ከዚህ ጋዜጣ ውጭ ሌላ መታያ አማራጭ አልነበራቸውም። ለዛሬው በጥቅምት ወር በጋዜጣው ላይ የወጡትን
እናያለን ።ፋንቱ ያለሰፈሯ ሌሊት ስትዞር ተይዛ ታሰረች ጥቅምት 7 ቀን 1963 ዓ.ምወይዘሮ ፋንቱ ወንደማርያም የተባለች በንፋስ ስልክ አካባቢ የምትኖር ሴት ያለሰፈሯ ከሌሊቱ በ10 ሰዓት በየካቲት 12 አደባባይ ስትዘዋወር በመገኘቷ ተይዛ የሶስተኛ ወረዳ ፍርድ ቤት የአንድ ወር እስራት የቀጣት መሆኑን አስታውቋል።

ስትዘዋወር መገኘቷንና ተላላፊ መኪናዎችንም አድርሱኝ በማለት ማስቸገሯን ፖሊሶች
መመስከራቸውን አስታውቋል።ተከሳሿም ፍርድ ቤት ቀርባ በተጠየቀች ጊዜ በአድራጎቷ ጥፋተኛ መሆኗን ስላመነች ፍርዱ ተሻሽሎላት በ30 ብር መቀጫ ወይም በአንድ ወር እስራት እንድትቀጣ ተደርጎ መቀጫውን መክፈል ስላልቻለች አንድ ወር እንድትታሰር ወደ ወህኒ ወርዳለች ሲል ከአንደኛ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘ ዜና ያስረዳል።ማስታወቂያጥቅምት 8 ቀን 1934 ዓ.ምበተፈሪ መኮንን ትምህርትቤት ገብተው
ለመማርለሚፈልጉ ልጆች ሁሉተማሪ ቤት ከመግባታቸው በፊት ጤናቸውን መመርመር ፈንጣጣ መከተብና ማናቸውንም የተማሪ ቤቱን ደንብፈጽመው በተማሪ ቤቱመዝገብ እንዲጻፉ የሚያስፈልጋቸውስለሆነ ይህንኑ ለመፈጸምከሚመጣው ማክሰኞ ጥቅምት11
ቀን ጀምሮ እስከጥቅምት 18 ቀንድረስ ጧት ከ3ሰዓት እስከ 7 ሰዓትእንዲሁም ከ9 ሰዓትእስከ 11 ሰዓትከተፈሪ መኮንን ተማሪቤት ድረስ እንዲሰበሰቡ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስት የትምህርትና የጥበብሚኒስቴር ያስታውቃል፡፡

የእስረኞች ሱቅ የሰረቀው በእስራት ተቀጣ ጥቅምት 10 ቀን 1972 ዓ.ምየግቢ አውራጃ ወህኒቤት ባልደረባ የነበረውተሾመ አያና የወህኒቤቱ የህግ እስረኞችዕቃ የሚሸጡበት ሱቅውስጥ ሌሊት ገብቶከሁለት ሺ 232 ብርበላይ መስረቁ ስለተረጋገጠበትበሰባት ዓመት ጽኑእስራት እንዲቀጣ የአውራጃውፍርድ
ቤት ባለፈውሳምንት ውስጥ በዋለው ችሎት በይኖበታል።በተያያዘም በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር የጎፋ አውራጃ የርዳታ ማስተባበሪያና ማቋቋሚያ
ኮሚሽን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ባልደረባ የሆነው አሰግድ አስፋው በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ዘላቂ መፍትሔ ማካሄጃ እንዲውል በኃላፊነት ከተሰጠው ገንዘብ ውስጥ ሶስት ሺ 147 ብር ከ45 ሳንቲም አጉድሎ ለግል ጥቅሙ አውሏል በመባል ተከሶ አድራጎቱ በማስረጃ ስለተረጋገጠበት ሰሞኑን በአምስት ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የጎፋ አውራጃ ፍርድ ቤት ወስኖበታል።
ሊሰርቅ የሄደው ሌባ ጠጅ አስክሮት ተያዘ ጥቅምት 10 ቀን 1959 ዓ.ምአባዲ ተስፋዬ መስከረም10 ቀን 1959 ዓ.ም ከሌሊቱ አምስት ሰዓት ላይ ከሁለት ጓደኞቹ ጋር ሆኖ የአቶ ካህሳይን ቤት ለመስረቅ ሄዶ ከዚያም ሲደርሱ በሩ ስለተዘጋባቸው በዕድሜና በሰውነት ያነሰው አባዲ በአጥር ተንጠልጥሎ ገባ።

አባዲ የቤቱን በር ከፍቶ እንደገባ እያማረጠ ለመስረቅ ጥሩ ጊዜ ሆነለት።በዚህ ሁኔታ የተሰረቀውን ዕቃ እያማረጠ እያጋዘ በማመላለስ እውጭ ካስቀመጠ በኋላ ጠጅ ጠጅ ሸተተው።ወደኋላው መለስ ቢል ጠጅ የሞላው በርሜል አየ።ጎንበስ ቢል የውሃ መቅጃ ቆርቆሮ አገኘ።ከዚህ በኋላ ምን ይጠየቃል ራሱን በራሱ ጋባዥ ሆነ።ከዚያ በኋላ ስካር ተጫጭኖት ስለተሸነፈ አባዲ ከወደቀበት ሥፍራ ሳይነሳ በዚያው ተኝቶ አደረ፡፡በማግስቱ ጠዋት ባለቤቶቹ ከእንቅልፋቸው ተነስተው ቤት ሊጠርጉ ሲሉ አባዲ ተጋድሞ አገኙት።ወዲያው በፖሊስ አስያዙት።ከዚያም ወደ ማረፊያ ቤት ተወስዶ በወታደር ደስታ በቃኸኝ አማካኝነት ቃሉን ሲሰጥ ‹‹ለመስረቅ
ሔጄ ጠጅ አስክሮኝ በዚያው ተኛሁ›› ሲል አረጋግጧል ብለው ሻለቃ ጌራ ወርቅ ገልጠዋል።
በትግሬ ግዛት የኢትዮጵያ የወሬ ምንጭ

Read 208 times