Monday, 06 November 2023 12:04

ለህክምና ቅድሚያ መስጠት ይገባል

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

• ‹‹….አንድ ሐኪም ተመርቆ ወደ ስራ ሲገባ ህብረተሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃል ይገባል…››
• ሐኪሙ በሚያጋጥመው ነገር ቢከፋም ቢደሰትም ለታካሚው የሚሰጠው አገልግሎት ወጥና ደረጃውን የጠበቀ ሊሆን ይገባል፡፡ሰዎች ባለን ልማድ ምንግዜም ተገደን ለምናደርገው ነገር ቅድሚ እንደምንሰጥ ይነገራል፡፡ ለምሳሌ መኪና የምንነዳ ከሆነ አመታዊ ግብር መክፈል ግድ ስለሆነ ጊዜው እንዲያልፍብን አንፈልግም፡፡ ምክንያቱም መኪና ሳይገበር መንገድ ላይ ሲገኝ ስለ ሚያስቀጣ ነው፡፡ ሌሎችም ለምሳሌ ከእለታዊ ፍላጎት ጋር የሚገናኙ ነገሮች ችላ ሳይባሉ በጊዜው እንዲታደሱ ወይንም እንዲለወጡ ተገዝተውም እንዲተኩ ይደረጋሉ፡፡ ወደ ጤንነት ሁኔታ ስንገባ ግን አዛዣ የሌለበት የግል ውሳኔን የሚጠይቅ በመሆኑ …አ…አ…ይ…ይደርሳል፤ ዛሬ ምንም አልሆንኩም ፤ተኝቼ ስነሳ ይሻለኛል፤ነገ ይሻለኛል ሲባል ቀን እንዲገፋ ይደረጋል፡፡

ምናል ባትም ወደ ሐኪም ቤት የሚኬደው የሁዋላ ሁዋላ ሲብስ በቤተሰብ እገዛ ሊሆን ይችላል፡፡ ይሄ መሻሻል የሚገባው ነገር ሲሆን ግን እንዴት የሚለው ውይይት ይፈልጋል፡፡ ይህንን ጨምሮ በሚቀጥሉት ሳምንታት ከተለያዩ ባለሙያዎች ጋር ስለሐኪምና ታካሚ ግንኙነት እንዲሁም የህክምና ስነምግባርን የሚመለከቱ ነገሮችን እናስነብባችሁዋለን፡፡ ላነሳነው ርእስ አስተያየታቸውን እንዲያጋሩን ለዚህ እትም ከጋበዝናቸው መካከል የማበራዊ ሰራተኛዋ ወ/ሮ አዲስ አለም ብርሀኔ ይገኙበታል፡፡ ወ/ሮ አዲስ አለም እንደሚሉት የህክምና አገል ግሎትን መፈለግ እንደባህል መወሰድ ይገባዋል፡፡

በአብዛኛው የህብረተሰባችን ክፍል የተለመደው ህመም ሲጠና ወይንም ከመጨረሻ ደረጃ ላይ ሲደርስ አለዚያም ባጋጣሚ ወደ ሕክምና መሄድ ለውጤቱ አስተማማኝነት ወይንም ጥሩ መሆን አጠያያቂ ደረጃ ላይ ሊያ ደርስ እንደ ሚችል ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለዚህ አካሄድ እንደምክንያት የሚቆጠሩ ብዙ ምክን ያቶች አሉ፡፡ ቀደም ባለው ጊዜ በአገራችን ሕክምናው እንደአሁን ባልተስፋፋበት ጊዜ ህመምን ለማስታገስ ከጥቅም ላይ የሚውሉት ከሕክምናው ይልቅ ባህላዊው ወይንም ልማዳዊ ዘዴዎች እንደ ነበሩ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ባህላዊ ሲባል ከባህል ሐኪሙ ጋ መሄድ ብቻ ሳይሆን ከጉዋሮ ወይንም ከደጃፍ የተለያዩ ቅጠላ ቅጠሎችን ወይም ስራ ስሮችን መጠቀም የመሳሰሉት ህመሞቸን ለማስታገስ ጥቅም ላይ ይውሉ እንደነበር አይዘነ ጋም፡፡ በእርግጥ ባህላዊ ወይንም ልማዳዊ ህክምናዎች የራ ሳቸው ደረጃ ያላቸው እና ተቀባይነት የሚያገኙበት አሰራር ያላቸው እንዲሁም በጤና ሚኒስቴርም እውቅናን የሚያገኙበት አካሄድ ቢኖርም እንደ ብቸኛ መፍትሔ ተደርገው ግን አይ ወሰዱም፡፡ እንደምክንያት የሚቆጠሩትም ለየትኛው ሕመም የትኛው መድሀኒት፤ምን ያህል መጠን፤ለምን ያል ጊዜ …ወዘተ የሚለው ሁሉ ሊታይ የሚገባው በመሆኑ ነው፡፡ ብለዋል ወ/ሮ አዲስ አለም፡፡ ሰዎች ሲታመሙ በፍጥነት ወደ ሕክምና ያለመሄዳቸው ሌላው ምክንያት ደግሞ ኢንሹራንስ በስፋት አለመለመዱ ነው፡፡

አሁን አሁን ደረጃው ቢለያይም ኢንሹራንስ እየተለመደ መጥቶ አል፡፡ በመንግስት ደረጃም የጤና መድህን በሚል ማንኛውም ሰው ኢንሹራንስ እንዲኖረው የሚያስችል አሰራር ተዘርግቶአል፡፡ የተለያዩ ድርጅቶ ችም እንዲሁ ለሰራተኞቻቸው ሙሉ የኢንሹራንስ አገልግሎትን ይሰጣሉ፡፡ ነገር ግን አሁ ንም ቢሆን ኢንሹራንስ ያላቸው ሰዎችም ህመም ሲሰማቸው በፍጥነት ወደ ሆስፒ ታል የሚሄዱበት አጋጣሚ ደካማ ነው፡፡በሀገራችን በኑሮ ዝቅተኛ መሆን ወይንም ድህነት፤አልፎ አልፎ ደግሞ የሚከሰቱ ግጭቶች ፤ከከተሞች እራቅ ብሎ በተሄደ ቁጥር አልፎ አልፎ የሚኖረው የህክምና አገልግሎት አለ መሟላት የመሳ ሰሉት ነገሮች ድሞም ከነበረው በፍጥነት ሄዶ ያለመታከም ጋር ተዳምሮ በሽ ተኛው ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሐኪሙ ሲቀርብ ምን ያህል ታምሞአል የሚል ጥያቄ ቢነሳ በጣም ሕመሙ ጠንቶ አደገኛ ሁኔታ ላይ ደርሶ ነው ለማለት ያስደፍራል፡፡ ይህ ደግሞ ከህመም የማገ ገምን እድል በጣም ያጠበዋል፡፡

ስለዚህ ችግሩ የባህል ወይንም የል ማድ እንዲሁም የአሰ ራር ሁኔታም ነው ብሎ መቀበል ይቻላል፡፡ በሐገራችን ሌላው መታየት ያለበት ነገር ፍላጎትና አቅርቦት አለመጣጣሙ ነው፡፡ ለምሳሌ ከከተሞች በእርቀት የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በምንመለከትት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ሕመም ገጥሞአቸው ወደሕክምና ተቋም መሔድ ቢያስቡ…እርቀት….የገንዘብ አቅም….
መጉዋጉዋዣው…..ሕመምተኛውን አጅቦ ከሐኪም ቤት የሚያደርስ ሰው ባለመኖሩ …ወዘተ ብዙ ሰዎች ይጎዳሉ፡፡ ምናልባትም ሁሉም ነገር ተሟልቶ ወደ ሕክምናው ቢደርሱ እንኩዋን ምን ያህሉ ቦታ የጤና አገልግሎት መስጫ በተሟላ ባለሙያ እና የምርመራ ቁሳቁስ እንዲ ሁም መድሀኒት ህመምተኛውን ለመርዳት የተሟላ ሆኖ ይገኛል የሚለውም አጠያያቂ ነው፡፡ ስለዚህ ታካሚው ወደትክክለኛው እና ተገቢው
የህክምና ተቋምና ሐኪሙ ጋ የሚቀርበው መቼ ነው ለሚለው ጥያቄ መልሱ እጅግ ዘግይቶ ፤ሕመሙ ከጠና በሁዋላ ነው ማለት ይቻላል ብለዋል ወ/ሮ አዲስ አለም፡፡ ዶ/ር ያየህይራድ አየለ በአሁኑ ጊዜ በሚሽንስ ኦፍ ቻሪቲ በጠቅላላ ሐኪምነት እያገለገሉ ይገ ኛሉ፡፡

የሐኪምና ታካሚውን ግንኙነት በሚመለከት አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡፡ እኔ የመመረቂያ ጽሁፌን የሰራሁት በአማኑኤል የስነ አእምሮ
ህክምና ሲሆን ህሙማኑ የአእምሮ ሕመም ታካሚዎች በመሆናቸው ከሌላው ታካሚ ይልቅ ለጉዳት ሊጋጡ ይችላሉ ከሚል ነበር ትኩረቴን ወደዚያ ያደረኩት ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ እንደሀገርም የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒ ታል እና የጤና ሚኒስቴር ለተመራቂ ተማሪዎች አዘጋጅተውት በነበረው ስልጠና ላይም ከፍተኛ ክፍተት የታየበት ሁኔታ ነበር፡፡ የህክምና ባለሙያው ታካሚውን ያማከለ፤ ለታካ ሚው ክብር መስጠት፤ጥንቃቄ ያለበት አገልግሎት መስጠት የሚለውን በሚመለከት አነስ ተኛ ሆኖ የሚታይበት ሁኔታ ቀላል አይደለም፡፡ በእርግጥ ይህ በእኛ ሐገር ብቻ ሳይ ሆን በሌሎች ሀገሮችም የሚታይ ችግር ነው፡፡

በትክክል ቁጥሩ ይህን ያህል ነው የሚለውን ለጊዜው ተወት ብናደርገው እንኩዋን ሐኪሙ ለታሚው የሚሰጠው ማንነትን ያማከለ፤ክብር እና ጥንቃቄን ያሟላ የሚለው ዝቅተኛ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት ከሚ ጠቀሱት ውስጥ ነገሩን በትክክል ያለመረዳት፤የስራ ጫና የመሳሰሉት ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ግምት አለ፡፡ እንግዲህ እኔም ጥናቱን በሰራሁበት ወቅት ያገኘሁት ውጤት የሚጋነን ባይሆ ንም ግን በመጠኑ ችግሩ ይታይ ነበር፡፡ የህክምና ባለሙያው እና የታካሚውን ግንኙነት ሁኔታ ከእነዚህ ክብር፤ጥንቃቄ እና ማንነ ትን ያማከለ ከሚለው ነጥብ መጉዋደል አንጻር ዶ/ር ያየህ ይራድ ሲመለከቱት የሐኪሙን ከስራ በፊት የሚገባውን ቃል አስታውሰዋል፡፡ ‹‹….አንድ ሐኪም ተመርቆ ወደ ስራ ሲገባ ህብረተሰቡን  በታማኝነትና በቅንነት ለማገልገል ቃል ይገባል…›› ይሄ ለአንድ ሐኪም ሞራላዊም ህጋዊም ግዴታው ነው፡፡ ግን አንዳንድ ጊዜ በተለያዩ ምክንያ ቶች ክፍተት ሊፈጠር ይችላል፡፡ 

የስራ ጫና፤የሐኪሙ የግል ባህርይ፤ ግድየ ለሽነት …ወ ዘተ…የመሳሰሉት፡፡ ነገር ግን ይህ መሆን የለበትም ፡፡ እንደ አንድ ባለሙያ ስነምግ ባሩን መላበስና ሐኪሙ በግሉ ጉዳይ ቢከፋም ቢደሰትም ለታካሚው የሚሰጠው አገልግሎት ወጥና ደረጃውን የጠበቀ ለሆን ይገባል …››ብለዋል፡፡ ዶ/ር የህይራድ በመቀጠልም ይህንን የሐኪምና ታካሚነትን ግንኙነት ለማሻሻል ምናልባት የህክምና ባለሙያውን ትውስታ ለማዳበር ወይንም እውቀቱን ለማደርጀት በክትትል ወይንም በስልጠና ማገዝ ሊያስፈልግ እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡ በስተመጨረሻም የሀገራችንን የህዝብ ቁጥር እና የሕክምና ባለሙያውን ቁጥር በማነጻጸር አጥጋቢ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት ምናልባትም ለታካሚው አስፈ ላጊውን ለማድረግ እንደአንድ ችግር ሊቆጠር ይችላል፡፡ አንድ ሐኪም እስከ አርባ እና ሀምሳ ሰው በቀን የሚያይባቸው አካባቢዎች አሉ፡፡

ይህ እንግዲህ ከአቅም በላይ የሚሆንበት አጋ ጣሚን እንደሚፈጥር መጠርጠር ይገባል፡፡በተጨማሪም ያለው የሐኪም እጥረት አንድን ታካሚ ወደ ሐኪም የሚቀርብበትን ጊዜ እንደሚያሳጥረው ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ለምሳሌ በአንዳንድ ሕመሞች ሳቢያ ወደሐኪም ለመቅረብ ረዘም ያለ ቀጠሮ የሚጠባበቁ ሰዎችን ሁኔታ መመልከት በቂ ይሆናል፡፡ከዚህ ሌላ ህመምተኛው መቼ ነው ወደ ሐኪም መቅረብ ያለበት ለሚለው …
በማንኛውም ጊዜ ሕመም ሲሰማው በተቻለ ፍጥነት…. የሚለው መልስ ይሆናል፡፡ ቢቻል ቢቻል እንዲ ያውም ሕመም ቢሰማም ባይሰማም ያለበትን የጤና ሁኔታ ወደ ህክምና ተቋም ቀርቦ የማረጋገጥ ልምድ እንዲያዳብር ይመከራል፡፡ በእርግጥ ታካሚ ለምን በጊዜው ወደ ህክምና አይቀርብም ለሚለው አንዱ ምክንያት ገንዘብ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፡፡ነገር ግን የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ጊዜ የጤና መድህን የሚል አሰራርን በመዘርጋቱ ማንኛውም ሰው ስነስርአቱን አሟልቶ በመቅረብ በመንግስት
ሆስፒታል መታከም ይችላል ብለዋል ዶ/ር ያየህይረድ አየለ ከሚሽን ኦፍ ቻሪቲ፡፡

Read 657 times