Saturday, 04 November 2023 00:00

አንጋፋውና ገናናው አርቲስት ስዩም ተፈራ የምስጋና ሽልማት ተሰጠው

Written by 
Rate this item
(1 Vote)
አንጋፋው ደራሲ፣ ገጣሚ፣ ሀያሲ፣ ተዋናይ፣ ዳይሬክተር... ጋሽ ስዩም ተፈራ በአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ እና ሰምና ወርቅ ሚዲያና ኢንተርቴይመንት በጋራ በመሆን በተዘጋጀው መድረክ ላይ የጥበብ አፍቃርያን ፣ አንጋፋ አርቲስቶች በተገኙበት የምስጋና መድረክ ዛሬ ጥቅምት 24/2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ የባህል አምባሳደር ዮድ አቢሲኒያ ባህላዊ የምግብ አዳራሽ የምስጋና አዋርድና በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተሸለሙትን ለአንጋፋ አርቲስቶች ያበረከቱት ኒሻን ጨምሮ የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶለታል።
በሀገራችን የትወና ሙያ የጎላ አሻራና ማህተም ያሳረፈ ታላቁ አርቲስት ጋሽ ስዩም ተፈራ በሀገራችን ኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ ስራ
ዎች ለማሳደግ የተለያዩ የጥበብ ሰራዎች በመስራት አስተዋፅኦ ካደረጉ እውቅ አርቲስቶች አንዱና በተለያዩ የኪነ-ጥበብ ሙያዎች 50 አመታትን ያገለገለና ለሀገራችን የኪነ-ጥበብ እድገት የታገለ የተመሰከረለት አርቲስት ነው።በዚህ የምስጋና መድረክም ጋሽ ስዩም የፃፋቸውን 3 መፅሓፎችን በይፋ አስመርቀዋል።
 
በፕሮግራሙም ጋሽ ስዩም ታምሞ በነበረበት ወቅት ድጋፍ ላደረገለት የኢትዮጵያ ህዝብና ግለሰቦች እንዲሁም የህክምና ተቋማት ምስጋና አቅርበዋል።
Read 583 times Last modified on Monday, 06 November 2023 18:50