Saturday, 04 November 2023 00:00

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተላት

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ከጃፓን መንግስት ለውጭ ሀገር ዜጎች የሚሰጠውን የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር ሽልማት ተበረከተላት።

ሽልማቱ የተበረከተላት በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለው የስፖርት ዲፕሎማሲ እንዲጠናከር ላደረገችው አስተዋጽኦ መሆኑም ተገልጿል።

አትሌት ደራርቱ የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስቴር ሺንዞ አቤ በፈረንጆቹ 2014 ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት ከኢትዮጵያውያን አትሌቶች ጋር እንዲወያዩ እድርጋ እንደነበር ተመላክቷል፡፡

በአውሮፓውያኑ 2019 ላይም ደራርቱ የጃፓን ስፖርት ኤጀንሲ ኮሚሽነር ከሆኑት ሱዙኪ ዳይቺን እና የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሃላፊ ሃሺሞቶ ሴይኮ ጋር በመምከር የልምድ ልውውጥ ማድረጓ ተገልጿል፡፡

ለረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የተሰጠው ይህ እውቅናና ሽልማት እኤአ ከ1875 ጀምሮ ለውጭ ሃገር ዜጎች በጃፓን መንግስት የሚሰጥ አንጋፋ የክብር ሽልማት መሆኑን በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ መረጃ አመልክቷል።

ይህ ሽልማት የውጭ ሀገር ዜጎች በጃፓን እና በሌሎች ሀገራት መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማሳደግ ላበረከቱት አስተዋፅኦ የሚሰጥ ሲሆን፤ ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉም ይህን ከፍተኛ የክብር ሽልማት በማገኝት የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊት ሆናለች።

Read 566 times Last modified on Monday, 06 November 2023 18:51