Saturday, 11 November 2023 00:00

ኢ.እ.ፌ በዓመት ውስጥ ከሩብ ቢሊዮን ብር በላይ ያስገባል፤ ያስወጣል

Written by  ግሩም ሰይፉ
Rate this item
(0 votes)

 የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን (ኢ.እ.ፌ) ከሁለት ሳምንት በፊት ባካሄደው 15ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ  በዓመት ውስጥከሩብቢሊዮንብርበላይ እንደሚያስገባና እንደሚ ያስወጣ አስታውቋል። ለኢ.እ.ፌ ጠቅላላጉባኤበቀረበውሪፖርትእንደተገለፀው በ2015 ዓመታዊገቢው 272 ሚሊየን 944ሺ 478 ብር ሲሆን ወጭው ደግሞ 272 ሚሊዮን 266ሺ 890 ብር ሆኖ ከወጭ ቀሪ 677ሺ 588 ብር መያዙተገልጿል።


የፌዴሬሽኑ  የገቢ ምንጮች ከዓለም አቀፋዊ፤ አህጉራዊና ክፍለአህጉራዊ የእግር ኳስ ማህበራት በውድድር ተሳትፎ ከሚከፋፈል በጀትና የአባልነት ድርሻ ፤ ከመንግስት ከሚለቀቅ በጀት፤ ከማርኬቲንግና ስፖንሰርሺፕ እንዲሁም ከተጨዋቾች የዝውውር ገበያ  የሚሰበሰቡ ናቸው። ከዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር ፊፋ ማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፎ፤ ከዓለም ዋንጫ ከሚገኝ ፈሰስና ከተለያዮ ድጋፎች ከ105.8 ሚሊዮን ብር በላይ ተቀብሏል። ከአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በተመሣሣይ አህጉራዊ ውድድሮች ተካፋይ ናት። ማጣሪያዎቹ ተሳትፎ በአንድ ዓመት ውስጥ  ከ44.9 ሚሊዮን ብር በላይ የወሰደ ሲሆን  ከመካከለኛውና ምስራቅ አፍሪካ የእግር ኳስ ምክር ቤት 11ሚሊዮን 431 ሺብር አግኝቷል።

ከኢትዮጵያ መንግስት ከ24 ሚሊዮን 890 ሺ ብር በላይ በበጀት  መውሰዱን ከስፖንሰርሺፕ ተያያዥ ንግዶች 14 ሚሊዮን 850 ሺ ብር እንዲሁም ከተጨዋቾች የዝውውር ገበያ 23 ሚሊየን 560 ሺ  ብር ገቢ መደረጉንም ሰምቶ ጠቅላላ ጉባኤው በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ከሚያወጣው ወጭ 50 በመቶው ለዋናው የወንዶች ብሔራዊ ቡድን፤ ለሴቶችና በተለያዩ የዕድሜ ደረጃዎች ለሚወዳደሩ ቡድኖች የሚሰጠው በጀት ነው። ለወንዶች ብሔራዊ ቡድን 66 ሚሊዮን 807ሺ 721 ብር እንዲሁም ለሴቶች ብሔራዊ ቡድንና በተለያዮ የእድሜ ደረጃ ለሚገኙ ቡድኖች 40 ሚሊዮን 982ሺ 624 ብር በአጠቃላይ 107 ሚሊዮን 792ሺ 945 ወጭ መሆኑ ተገልጿል። ዓለምቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታድዬም ኢትዮጵያ ውስጥ አለመገንባቱ በውድድሮች ተሳትፎ የሚወጣውን ወጭ ጨምሮታል፡፡
የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ በ2014 አስመዝግቦት ከነበረው ገቢው  በ37ሚሊዮን160ሺ944ብር እንዲሁም ወጭው 19ሚሊዮን461ሺ179ብር በ2015 መጨመሩን ያመለከተው ሪፖርት ወደ 2016 ሲሸጋገር በጥሬ ገንዘብ 26 ሚሊየን 024ሺ 097 ብር እንዲሁም በንብረት መልክ 101 ሚሊዮን 167ሺ 592 ብር በድምሩ227ሚሊዮን191ሺ689ብርሐብት ማስመዝገብ መሆኑን አስታውቋል።
ፌዴሬሽኑ  ክለቦች በታዳጊና የሴቶች ቡድኖች ዙርያ ትኩረት አድርገው አለመሥራታቸውን  በጠቅላላ ጉባኤው የወቀሰ ሲሆን  እንዲያስተካክሉ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።መንግስት ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የሚሰጠውን የበጀት ድጋፍ እንዲያሳድግ የተጠየቀም ሲሆን  ብሔራዊ ቡድኖች የአገር አርማ መሆናቸውን ግምት ውስጥ ያስገባ በጀት ከመንግስት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያን በብሔራዊ ቡድኖች ለመሠለፍ እንዲችሉ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ መሆኑም በጠቅላላ ጉባዔው ተነስቷል። ሲሆን ይህን አስመልክቶ ልዮ ሰነድ በ37 ገፅ በማዘጋጀት ለፊፋ መቅረቡን ከኢምግሬሽን ቢጫ ካርድ በማግኘት ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ መጫወት እንዲችሉ እየተሰራ ነው ተብሏል።


በኢትዮጵያ ያሉ ስታድየሞች ደረጃቸውን ለማሳደግ በስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለፀው ፌደሬሽን
የባህርዳር የአዲስ አበባና  የቃሊቲ ስታድየሞችን በመገንባት ሂደት ላይ አስተዋፅኦ ማረጉን አመልክቷል። የስታድዬሞችን ግንባታ ለማጠናከር ልዩ ልዑካን ወደ አይቮሪኮስት መላክ ጉብኝት አድርገዋል ቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ አዘጋጅ በመሆኑም ከፍተኛ ---------ተወስኗል።
በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ስቴዲየሞች የፊፋና ካፍን መመዘኛ አሟልተው እንዲገነቡና ለጉባዔው አባላት ገልጿል። በፍጥነት እንዲጠናቀቁ እየተሰራ መሆኑን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጸ።  በአፍሪካ ኅብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ  የተካሄደው 15ኛው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የማሟያ ምርጫ ተካሂዶ ነበር።  ኮሎኔል አወል አብዱራሂም ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ92 ድምጽ፣ ኢብራሂም ሙክታር ከአፋር ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ80 ድምጽ እና ማዕረጉ ሀብተማርያም ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን በ76 ድምጽ የፌዴሬሽኑ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት በመሆን ተመርጠዋል።


የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ መተዳደሪያ ማሻሻያ ደንብ፣ የፌዴሬሽኑ የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸምና  የ2016 እቅድ ሪፖርት ውይይት ተደርጎበት በጠቅላላ ጉባኤው ፀድቋል።


Read 617 times