Saturday, 20 August 2011 10:20

ታሪክን ሲያጠምቋት

Written by  ደረጀ ፀጋዬ
Rate this item
(0 votes)

አገር ሃይማኖተኛ መሪ ካላገኘች አትበለግም የሚል የፖለቲካል ሳይንስም ሆነ የኢኮኖሚክስ አስተሳሰብ ስለመኖሩ ከዚህ ቀደም ያነበብን ወይም የሰማን አይመስለኝም፡፡ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ ይህንን አዲስ የፖለቲካል-ኢትምህርት የሰማነው በዚሁ የክረምት ወቅት ነው፡፡
ጤና ይስጥልኝ በማለት ወደ ዛሬ ወጌ ልግባ፡፡ (መቼስ ተንኮለኛ አንባቢ ..ማን ይስጥልህ?.. ሳይለኝ አይቀርም፡፡ ኢ-አማኒ እራሱ የሚሰጠው እንጂ የሚሰጥለት ማን አለውና) ሰላምታዬን እንደተለመደ አባባል ቁጠሩልኝ፡፡

የዛሬ ወጌ በነሐሴ 7ቱ የዶ/ር ፍቃዱ አየለ ሁፍ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ ፀሐፊው ከሳምንት ሳምንት ሳይሰለቹ በናት ላመኑበት መፋለማቸውን ሳላደንቅ አላልፍም፡፡ ችግሩ ግን የተቀናቃኞቻቸውን ሃሳብ በሰለጠነ መንገድ መርታት ሲሳናቸው በሚጮሁ ፀያፍ ርእሶች የታጀቡ ሁፎችን በመደርደር ከንፁህ ክርክር ይልቅ እሽከለኬታመምረጣቸው ነው፡፡እንደ እውነቱ ..ተደላድዬ ከተኛሁበት የህልም ዓለም ለምን ትቀሰቅሱኛላችሁ.. የሚል የብስጭት ስሜት ካልሆነ በቀር በሃሳብ መቆራቆስ እንግዳ ነገር ሆኖ አይደለም፡፡ ባይሆንማ ኖሮ እንደ ክርስቶስ |የሚያደርጉTN አያውቁምና ይቅር በላቸው.. ማለት ሲገባቸው እግዜር እንኳን ሆደ ሰፊ በሆነበት ወቅት እንደ ቁጡው የብሉይ ዘመን አምላክ የስድብ መብረቅ ባላዘነቡ፡፡ በዚህ ጴጥሮሳዊ ትኩሳታቸው በብዕር ፈንታ ሰይፍ ይዘው ቢሆን ኖሮ የተቃዋሚዎቻቸውን ጣቶች እንደ ጐመን ቅጠል ይቀነጣጥሷቸው ነበር፡፡
ሰሞኑን ደግሞ እኚሁ ፀሐፊ ከተፈጥሮ ሳይንስ ወደ ማህበራዊ ሳይንስ ምህዋር ገብተው የአሜሪካን ታሪክ ክርስትና ሲያነሱ አይተናል፡፡ ምንም እንኳን የክርክሩን ዙር ቢያከሩብንም እኛም የእለት ጉርሳችንን ለማሸነፍ ከምንባዝንበት ውሎ ስንመለስ ከቤተሰብ የጨዋታ ሰዓት ላይ በምንቀነጫጭባት ጥቂት ጊዜ የሞነጫጨርናትን ጀባ እንላለን፡፡ ፀሐፊው በዚሁ ሰሞነኛ ሁፋቸው አገራችን ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካና ሌሎችም የሦስተኛ ዓለም አገራት የምጣኔ ሃብት ጉስቁልና መንስኤው የህዝቦች እውነተኛ እምነት/ሃይማኖት ማጣትና በእውነተኛ አማኝ መሪዎች መመራት አለመቻላቸው መሆኑን ገልፀውልናል፡፡
አገር ሃይማኖተኛ መሪ ካላገኘች አትበለግም የሚል የፖለቲካል ሳይንስም ሆነ የኢኮኖሚክስ አስተሳሰብ ስለመኖሩ ከዚህ ቀደም ያነበብን ወይም የሰማን አይመስለኝም፡፡ ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም እንዲሉ ይህንን አዲስ የፖለቲካል-ኢ÷ñ¸ ትምህርት የሰማነው በዚሁ የክረምት ወቅት ነው፡፡ ለዚህም አዲስ ትምህርት ምሳሌ ተደርጋ የቀረበችልን አሜሪካ ናት፡፡ ዶ/ሩ ይህንን ትምህርት ያመጡልን ..የአሜሪካ ህገ-መንግስት መሰረቱ መሐፍ ቅዱስ ነው.. ከሚሉ የሃይማኖት መቻቻል ከማይገባቸው ንፈኛ ክርስቲያኖች ሊሆን እንደሚችል የተረዳሁት በዚሁ ጉዳይ ላይ መረጃ ሳገላብጥ ነው፡፡የዛሬይቷ አሜሪካ ከአሮጌው አለም በፈለሱ ህዝቦች ከመመስረቷ በፊት በብዙ ክ/ዘመን ቀደምት የነበሩት የዛሬዋ ኢትዮጵያ ሰሜናዊ ክልል ህዝቦች ክርስትናን ተቀብለው ስለመኖራቸው እሰጥ-አገባ መግጠም አያሻንም፡፡ ክርስትናውን ብቻ መጥቀሴ የእስልምና እምነት ተከታይ ማህበረሰብ ተዘንግቶኝ ሳይሆን የዶ/ሩ የግርግር ሰፈር በክርስትናው ርእሰ-ደብር በመሆኑ ነው፡፡ ከ1966 ዓ.ም በፊት (አቆጣጠሩ አገርኛ ነው) የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች በሙሉ (የውስጣቸውን ባናውቅም) ቢያንስ በመርህ ደረጃ የእምነት ስርዓቱ ደጋፊና አባላት እንደነበሩ ይታወቃል፡፡ በእምነት ማጣት ሳይሆን በፖለቲካ አካሄድ yቤተ-KRStEÕN አባቶች በመጠኑም ቢሆን ያስቆጡ መሪ ቢኖሩ አንድ አፄ ቴዎድሮስ ናቸው፡፡ (በእምነት ሰበብ በሱስንዮስ ዘመን የፈሰሰውን ያበሻ ደም ሳንዘነጋ) ታዲያ አማኝ ህዝቦቿንና መሪዎቿን ይዛ ያልበለፀገች ኢትዮጵያ እያለች አሜሪካ ከእምነቷ ናት የተነሳ እንደበለፀገች ማስወራት እድገትና ብልግና ለስራ ክብር ሰጥቶ ከመታተር እንደሚመጣ መዘንጋት ነው፡፡ለዶ/ሩ የተሳሳተ አመለካከት ትልቅ እማኝ የሚሆኑኝ የሩቅ ምስራቆቹ አገሮች ቻይናና ጃፓን ናቸው፡፡ እንደ ዶ/ሩ ..እውነተኛ እምነት.. አተረጓጐም ቻይናም ሆነች ጃፓን የእውነተኛ እምነት አገሮች አይደሉም፡፡ ቻይናና ጃፓን ከአሜሪካ ቀጥሎ ግዙፍ ኢኮኖሚዎች ናቸው፡፡ አብዛኛው የቻይና ህዝብ የሚያምነው በሦስት ዋና ዋና እምነቶች ነው፡፡ እነሱም ኮንፈሺያኒዝም ታኦይዝ እና ቡዲሂዝም ናቸው፡፡ በጃፓን ደግሞ ሺንቶይዝምና ቡዲሂዝም ይታመናሉ፡፡
ከነዚህ ግዙፍ የምጣኔ ሀብት ያላቸው አገሮች ሌላ ለአዳጊ አገሮች እንደ ተምሳሌት የሚቆጠሩ አራቱ የኤዥያ ነብሮች እነ ሆንግ ኮንግ፣ ሲንጋፖር፣ ደቡብ ኮሪያና ታይዋን የፀሐፊያችንን ..እውነተኛ እምነት ለእድገት.. መፈክር ፉርሽ የሚያደርጉ ተጨማሪ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ እነዚህ የምጣኔ ሀብት ተአምር ያሳዩ አገሮች እንደ ፀሐፊው ሃሳብ ..የእውነተኛ እምነት አገሮች.. አይደሉም፡፡ ለእድገታቸው መሰረት የሆናቸው የእምነት ስንቅ ሳይሆን መንግስታቶቻቸው ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ስርፀት የሰጡት ትኩረትና በትምህርት ዘርፉ ላይ ያፈሰሱት ከፍተኛ መዋዕለ-ንዋይ (Investment) ነው፡፡ አፍራሽ ምሳሌዎችን በማንሳት ይህን ያህል ካልኩ በኋላ ዶ/ሩ ..የእምነት አገር.. ስለሚሏት አሜሪካ ደግሞ ጥቂት እንባባል፡፡ በዛሬይቷ አሜሪካ ንፈኛ ክርስቲያኖች እምነታቸውን በጠቅላላው ህዝብ ላይ ለመጫን የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም፡፡ ለአላማቸው መሳካት በሳይንስ ካባ የእምነት ትምህርት በመንግስት ት/ቤቶች እንዲሰጥ
ፍርድ ቤት ከመቆም እስከ ፖለቲከኞች የማባበል ስራ (Lobbying) ተሰማርተዋል፡፡ እንደው ለነገሩ ዶ/ሩ ላነሱት እኛም ለትምህርት ይሁነን ብለን እንጂ አሜሪካኖች በአገራቸው ያሻቸውን ቢያደርጉ ጥልቅ የሚያደርገን ኖሮ አይደለም፡፡ በዛ ላይ በባሌም በቦሌም አቆራርጦ ሊኖሩባት ለሚከጅሏት አሜሪካ ጥቂት ማወቅ አይከፋም፡፡ እንደሚታወቀው አሜሪካ የብዙ የተለያዩ ህዝቦችና እምነቶች መናኸሪያ ናት፡፡ የብዙ ህዝቦችና ባህሎች ጥርቅም በመሆኗም “Melting Pot” እያሉ ይጠሯታል፡፡ አሜሪካን የመሰረቷት ቀደምት ምዕራባውያን ሰፋሪዎች ሁሉም በአንድ የእምነት ጥላ ስር አልነበሩም፡፡ ሰፋሪዎቹ ከሚከተሏቸው እምነቶች ውስጥ ካቶሊክ፣ የተለያዩ የፕሮቴስታንት ዘርፎች፣ ፕዩሪታንስ፣ ፕሪስባይቴሪያንስ፣ ክዌከርስ፣ ሜቶዲስትስ እና ባፕቲስት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ ሃይማኖቶች ታዲያ የየራሳቸው የእምነትና የአምልኮ ስርዓቶች አሏቸው፡፡ እነዚህ ሁሉ እምነቶች ባሉበት ሁኔታ ፀሐፊው አሜሪካን ለገናናነት ያበቃት የትኛው የእምነት ዘርፍ እንደሆነ በግልጽ ሊያስቀምጡልን ይገባል፡፡
የሃይማኖት ጭቆናና ብጥብጥ ሸሽተው በአሜሪካ ምድር የሰፈሩት የመጀመሪያዎቹ አውሮፓውያን ትተውት ያለፉት ሊነገርለት የሚገባ ትልቅ ታሪክ በምዕራብ አውሮፓ የተከሰተው የሃይማኖት ቀውስ በነሱም እንዳይደገም የሃይማኖትና የፖለቲካ ስርዓቱን መለየት ነበር፡፡ ይህም ከዘመነ ተሃድሶ (Reformation) በኋላ የተከሰተ ቀውስ በአብዛኛው በጀርመን በተካሄደ የሰላሳ ዓመት ጦርነት፣ በእንግሊዝ የእርስ በርስ ጦርነትና በፈረንሳይ አገር በካቶሊኮችና በፕሮቴስታንቶች መካከል በተደረገ ጦርነት የብዙ አውሮፓውያኖችን ህይወት ቀጥፏል፡፡ እነዚህ በሃይማኖት ምክንያት የተነሱ ጦርነቶች በማንኛው ዓለማዊ ምክንያት ከሚነሱ ጦርነቶች በጭካኔያቸው የሚተናነሱ አልነበሩም፡፡
የአሜሪካን አብዮት በፈነዳበት ወቅት አሜሪካኖች በሃይማኖት ሰበብ በአውሮፓ ወንድሞቻቸው ከማንኛውም የሃይማኖት ፍጥጫ ነፃ የሆነች አሜሪካን ለመመስረት ጥረዋል፡፡ መንግስት በማንኛውም መንገድ በዜጐች እምነት ውስጥ ገብቶ ሊወስን እንደማይገባው ያሳሰቡ ታዋቂ አሜሪካኖች ነበሩ፡፡
እነ ጀፈርሰን፣ ማዲሰንና ሌሎችም የአሜሪካ ታላላቅ ሰዎች በአሜሪካ የመንግስት አስተዳደርና በእምነት መሀል ቋሚ መለያ ግንብ እንዲበጅለት ጥረዋል፡፡
ምንም እንኳን አሜሪካ ከቀደምት ነዋሪዎች (Indigenous people) ውጪ በአብዛኛው የክርስቲያን ሰፋሪዎች አገር ብትሆንም በህገ መንግስታቸው ቀረፃ ላይ ከፍተኛ ሚና የተጫወተው ሃይማኖታዊው መጽሐፍ ሳይሆን የዘመነ አብርኾት (Enlightment) አስተሳሰብ ለመሆኑ ብዙ መረጃዎች ማቅረብ ይቻላል፡፡ በነፃነት አዋጃቸውም ሆነ በህገ - መንግስታቸው ላይ የነ ጆን ሎክ፣ ሞንቴስክ እና ሩሶ የአስተሳሰብ ተጽእኖ በጉልህ ይታያል፡፡ የዘመነ አብርኸት ልሂቃን በፖለቲካ አስተዳደር ላይ የህዝብን ዓይን በመክፈት በኩል ትልቅ ሚና ተጫውተዋል፡፡
ቀድሞ ይታመንባቸው የነበሩትን እንደ መለኮታዊ የስልጣን ምንጭ (ስዩመ እግዜርነት) ዓይነት የአምባገነን ነገስታት መሸሸጊያ ሃሳቦችን ተገዳድረዋል፡፡ ሰዎች በዚህ ምድር ላይ ቁሳዊ ሃብትን የመፍጠርና የማከማቸት፣ ማህበራዊ ፍትህና ደስታን የማግኘት ሰብአዊ መብቶች እንዳሏቸው አትተዋል፡፡
በአሜሪካ ህገመንግስት ውስጥ በመንግስት አካላት መካከል ሊኖር ስለሚገባው የሃይል መመጣጠንና የእርስ በርስ ቁጥጥር (balance and check) ሃሳብ የተወሰደው በቀጥታ kMontesquieu ነው፡፡ የዘመነ - አብረኸት ሊሂቃን አስተሳሰብ ቶማስ ጀፈርሰን በቀረፀው የነፃነት አዋጅ ውስጥ ተቀምጠው እናገኛቸዋለን፡፡ በምሳሌ ለማየት ያህል የልሂቆቹን ጥቂት ሃሳቦች ከአሜሪካ የነፃነት አዋጅ ጋር እናነፃጽር፡፡ እንደ ፈላስፎቹ አስተሳሰብ:- 
ሰዎች የማይገሰስ ተፈጥሯዊ ሰብአዊ መብት አላቸው
መንግስት መቋቋም ያለበት የዜጐችን መብት ለመጠበቅ ነው፤
የመንግስት የስልጣን ምንጭ የዜጐች ነፃ ፍቃድ ነው፡፡
z¤gÖC ኢ - ፍትሐዊ መንግስትን የማስወገድ መብት አላቸው፡፡
እነዚህኑ ሃሳቦች ደግሞ በቶማስ ጀፈርሰን በጁላይ 4, 1776 ዓ.ም (እ.ኤ.አ) በረቀቀው የአሜሪካን የነፃነት አዋጅ ውስጥ እንዴት እንደሰፈሩ እንመልከት፡፡ 
የብሪ¬NÃ መንግስት የአሜሪካ ሰፋሪ ህዝቦችን ተፈጥሯዊ ሰብአዊ መብቶች ገፋለች
ህዝቡ ኢ - ፍትሃዊ አስተዳደርን የማስወገድ መብት አለው
HZbù መብቱን የሚያስከብርለት አዲስ መንግስት የማቋቋም መብት አለው፡፡
ከላይ ያየናቸው ሃሳቦች የአሜሪካ መስራች አባቶች ለዘመነ አብርሆት አመለካከት ምን ያህል ቅርብ እንደነበሩ ያሳየናል፡፡
የአሜሪካ ህገ - መንግስት የረቀቀው ፍፁም ዓለማዊ በሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ መሆኑን የሚያሳየን bConstitutional Convention ውስጥ ሃይማኖት የተጠቀሰው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን እሱም bArticle VI  Section 3 ውስጥ እንዲህ ይላል፤ “No religious test shall ever be required as a qualification to any office or public trust under the united states”   በአጭሩ ሲገለጽ ሃይማኖተኛ መሆን ለስልጣን አያበቃም፤ አለመሆንም ከስልጣን አያግድም፡፡ ሌላ ምሳሌ እንጨምር፡፡ በጆርጅ ዋሽንግተን የስልጣን ዘመን አሜሪካ በትሪፖሊ ስምምነት ላይ በሃይማኖት ጉዳይ ግልጽ አቋማን አሳይታለች፡፡ የዚህ ስምምነት Article II  እንዲህ ይነበባል “The government of the United States is not in any sense founded on the Christian religion…”  የስምምነቱን ሃሳብ ዋሽንግተን አንብቦት ተስማምቶበታል፡፡ በጆን አዳምስ የርዕሰ - ብሔርነት ዘመን ለሴኔት ቀርቦ ፀድቋል፡፡ እንግዲህ ለዶ/ሩ የአሜሪካ ክርስቲያንነት ተረት ከዚህ የበለጠ መረጃ ምን እናቅርብ?
የአሜሪካ መንግስት ስለ እምነት ያለውን አቋም ከተመለከትን በኋላ እስቲ ታላላቅ ስብዕና ስላላቸው አሜሪካን ስለመሰረቱ አባቶች የእምነት አስተሳሰብ ጥቂት እንጨዋወት፡፡ አሜሪካን የመሰረቷት መሪዎችና አባቶች ምንም እንኳን የአስተዳደጋቸው መሰረት በክርስቲያን ቤተሰቦች ውስጥ ቢሆንም እምነታቸው ግን ባህላዊው የክርስትና እምነት ሳይሆን ዴይዝም (Deism) ነበር፡፡ ዴይዝም በአሜሪካ አብዮት ወቅት በብዙዎች ምሁራን ዘንድ ተቀባይነት የነበረው ፍልስፍና እንደነበር ይነገራል፡፡ ዴይስቶች ሰው በምክንያታዊነት (Reason) ማህበራዊና ፖለቲካዊ ህይወቱን መምራት ይችላል ብለው ያምናሉ፡፡ እንደ ዴይስቶች እምነት ምልዓተ ዓለምን (Universe) የፈጠረ አምላክ በሆነ ባልሆነው በሰው ልጆች የእለት - ተእለት ኑሮ ጣልቃ እየገባ የሚመራ ሳይሆን ምልዓተ - ዓለምን ከነመተዳደሪያ ህጐች (natural laws) ፈጥሮ ዞር ያለ ነው፡፡ በተፈጥሮ ክስተቶች ላይ ምንም ተጽእኖ አያሳድርም (ታዋቂው አሜሪካዊ የክርስቲያን እምነት ሰባኪ ፓት ሮበርትሰን እንደሚለው ዓይነት አምላክ ሃይቲዎች በዘመነ ኮሎኒያሊዝም ለነፃነታቸው ሲሉ ከሰይጣን ጋር የአጋርነት ውል በመፈራረማቸው አገርና ህዝብ በመሬት መንቀጥቀጥ ዶጋመድ አያደርግም፡፡)
ለሰዎች በልዕለ - ተፈጥሮም (Supernatural) ሆነ በሌሎች መንገዶች አይገለጥም፡፡ በመሆኑም ለክርስትና እምነት መሰረታዊ የሚባሉትን አስተምህሮቶች አይቀበሉም፡፡
ዴይስቶች የድንግል መውለድን፣ ቅድስናን እና የክርስቶስን ትንሣኤ አይቀበሉም፡፡ በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስ በመለኮት ምሪትም ሆነ ፍቃድ ተጽፏል ብለው አያምኑም፡፡ አሜሪካን ከመሰረቷት ታላላቅ ሰዎች ውስጥ እንደ ጆርጅ ዋሽንግተን፣ ቶማስ ጃፈርሰን ቤንጃሚን ፍራንክሊን፣ ኤታን አለን ጀምስ፣ ማዲሰንና ጀምስ ሞንሮ የመሳሰሉት የዚህ ፍልስፍና አማራጆች እንደነበሩ ብዙ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በፖለቲካ ህይወታቸው ላይ ሊያስከትለው የሚችለውን ተጽእኖ በመገንዘብ አደባባይ የክርስትና እምነት አፍቃሪዎች ቢመስሉም ቅሉ በሚጻጻፏቸው ደብዳቤዎች ውስጥ ስሜታቸውን የገለባቸው አጋጣሚዎች ብዙ ናቸው፡፡
ቶማስ ጃፈርሰን ከፍተኛ የቀሳውስት ጥላቻ ነበረው፡፡ በ1814 ዓ.ም. (እ.ኤ.አ.) Horatio spafford ለተባለ ሰው በጻፈው ደብዳቤ ..በሁሉም አገርና በሁሉም ዘመን ቄስ የነጻነት ጠላት ነው፡፡ ለግል ጥቅሙ ሲል አምባገነኖችን ሲደግፍ ኖሯል፡፡. . ... ሲል ጽፏል፡፡ ለወ/ሮ Harrison Smith በጻፈው ሌላ ደብዳቤ ..እምነታችን ሊገለ የሚገባው በልሳናችን ሳይሆን በኑሮአችን መሆን አለበት፡፡ አለም ሊፈርደኝ የሚገባው በዚህ መንገድ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ቀሳውስቱን አያስደስትም፡፡ ለሚቀባጥሩት ሁሉ የአዎንታ ቃላችንን በአደባባይ እንድንሰጥ ይሻሉ፡፡. . ... ሲል ዳግም ጽፏል፡፡ ጃፈርሰን ጽንፈኛ ክርስቲያኖች እንደሚያስቡት ዓይነት ክርስቲያን አለመሆኑን የሚያረጋግጥ ሌላ ጠንካራ ምሳሌ እናቅርብ፡፡ ጃፈርሰን መጽሐፍ ቅዱስ በቅዱስ መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው ብሎ አያምንም፡፡ ይህንንም ስሜቱን ..የጃፈርሰን መጽሐፍ ቅዱስ.. እየተባለ በሚጠራው እራሱ ባዘጋጀው የክርስቶስ ታሪክ ውስጥ አንባርቋል፡፡ ጃፈርሰን በጻፈው የክርስቶስ ታሪክ ውስጥ ክርስቶስ የሠራቸው ተአምራት ተወግደዋል፡፡ ታሪኩም የሚያከትመው ክርስቶስ ሞቶ ሲቀበር ነው፡፡ ትንሳኤ የለውም፡፡ ይህ ለክርስቲያኖች ከፍተኛ የመለኮት መዳፈር ነው፡፡ ለጃፈርሰን ዴይስቲክ አስተሳሰብ ግን ትርጉም የሚሰጥ ነው፡፡ ለጃፈርሰን ዴይስቲክ አስተሳሰብ ግን ትርጉም የሚሰጥ ነው፡፡ ለጆን አደምስ በጻፈው ደብዳቤ ..ከቁሳዊ አካል ውጪ ያለ ህላዌ (existence) ተረት-ተረት ነው፡፡.. ብሏል፡፡ እኛ ደግሞ በዚህ የጋዜጣ ጭውውት ሁሉንም ለመተረክ ስለሚያስቸግረን አንባብያንን ለተጨማሪ የግል ንባብ እየጋበዝን ወደ ሌሎቹ እንለፍ፡፡
ቀጣዩ ባለታሪካችን ደግሞ ጆርጅ ዋሽንግተን ነው፡፡ ዋሽንግተን ከባለቤቱ ጋር በሰንበት ቤተ ክርስቲያን እንደሚያዘወትር ይነገራል፡፡ ከሚያዘወትርበት ቤተ ክርስቲያን ኃላፊዎች የተገኘው መረጃ እንደ¸ÃmlKtW# ከባለቤቱ ጋር ቤተ ክርስቲያን ከማዘውተሩ ውጪ አንድም ቀን ቅዱስ ቁርባን ወስዶ እንደማያውቅ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ቅዳሴ መገባደጃ ላይ ባለቤቱን በቤተ ክርስቲያን ጥሎ እንደሚሄድ ይነገራል፡፡ ዶ/ር ዊልሰን የተባለ ሰባኪ ስለ ጆርጅ ዋሽንግተን በሰጠው ቃለ ምልልስ ..ዋሽንግተን ለህዝቡ ያደረጋቸውን ንግግሮች ሁሉ በጥንቃቄ መርምሬአቸዋለሁ፡፡ አንድም ጊዜ ክርስቲያናዊ ወገናዊነቱን የሚገልጽ ንግግር አላገኘሁም፡፡ ጉዳዩን በቅንነት የሚመረምር ማንኛውም ሰው ዋሽንግተን ዴይስ ነው ብሎ ከመደምደም ውጪ ሌላ አማራጭ አያገኝም.. ሲል ገልል፡፡ የዋሽንግተንን የእምነት አቋም በተመለከተ ብዙ የታሪክ ፀሐፍት ያሉት ቢኖርም አሁንም ማጣራቱን ለአንባብያን ትተን ወደ ዝነኛው ቤንጃሚን ፍራንክሊን እንለፍ፡፡
ቤንጃሚን ፍራንክሊን የብዙ ሞያዎች ባለቤት ነው፡፡ አሳታሚ፣ ደራሲ፣ ሳይንቲስት፣ ፈላስፋ፣ ፖለቲከኛ. . . ኧረ ስንቱ፡፡ ህይወትን እስከ ጥግ የኖራት ሰው ነው፡፡ የቤንጃሚን ፍራንክሊን ቤተሰቦች የፕዩሪታን እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ ለልጃቸው ይመኙለት የነበረውም ሞያ yቤተKRStEÃN አገልጋይነትን ነበር፡፡ ፍራንክሊን ግን የወላጆቹን ምኞት ትቶ ገና በጐልማሳነቱ ዴይስት መሆኑን እ.ኤ.አ በ1725 ዓ.ም. በጻፈው “A dissertation on liberty and necessity, pleasure and pain” በሚለው ጽሑፉ ገልል፡፡ ለስነ-ምግባር ትምህርት የተደራጀ ሃይማኖት ተግባራዊ ጠቀሜታ እንዳለው ያምን ነበር፡፡ ከሃይማኖት ነጻ የሆኑ መንግሥታቶች (secular governments) ይህንን የሃይማኖት ሚና bcivic education (የሥነ-ዜጋ) ትምህርት መተካት እንደሚቻል ያምናሉ፡፡ ፍራንክሊን ሁሉንም እምነቶች በእኩል ዓይን የሚያይ (pluralist) ነበር፡፡
በእውቀት የሚያምን ሰው ሰብዕናና ግብረ ገብነት የሚቀርው በጭፍን እምነት ሳይሆን በመመርመር ነው፡፡
ለዚህ ሃሳባችን አብነት እንደተለመደው ሶቅራጥስን እንጥቀስ፡፡ (በሰሞኑ ክርክሮች የአዋቂነታችን ልኬት እስከሚመስል ድረስ የማናስገባበት ቦታ የለም፡፡) ሶቅራጥስ ..ያልተመረመረ ህይወትን መኖር ፋይዳ ቢስ ነው፡፡.. ይለናል፡፡ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ህይወት ..ምን ማድረግ አለብኝ?.. ብሎ የህይወቱን ትርጉም ሲፈልግ ጭፍን አማኝ ግን ..ምን ማድረግ ይጠበቅብኛል.. በሚል ስሜት የሹፌርነቱን ቦታ ለቆ ለሸክም የተመቻቸ ጋሪ ይሆናል፡፡ለዛሬ እቺን ያህል ካልኩ ..ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም.. የሚለውን ብሂል አስቀድሜ ወደ ጉዳዬ መቋጫ ልዝለቅ፡፡ የሰው ልጆች በተለያየ ዘመን የተለያዩ አማልክትን ሲያነግሱና ሲሽሩ ኖረዋል፡፡አንዳንዶችም ዘመን አቆራርጠው ከኛ ደርሰዋል፡፡ ለመጥፊያችን ምክንያት ካልሆኑን በቀር ከሚቀጥሉት ብዙ ትውልዶች ጋር ይኖራሉ፡፡ ለመንፈስ ደካሞች ብርታት እንደሚሆኗቸው አይጠረጠርም፡፡ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በሰረበት በአሁኑ ዘመን በነዚህ አማልክት መተማመን የስልጣኔ መንገድ ሳይሆን ከሰማይ መናን መጠበቅ ነው፡፡ ለአኮኖሚያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ስኬታችን መሠረት ሊሆነን የሚገባው የሰው ልጅ አእምሯዊና ስጋዊ ጥረት ብቻ ነው፡፡ ከአሜሪካም ሆነ ከሌሎች ያደጉ አገራት ልንማር የሚገባንም ይሄንን ነው፡፡

Read 2604 times