Thursday, 18 April 2024 20:42

በእርግጥም እጆች የሚናገሩበት፤ ዓይኖች የሚያዳምጡበት!

Written by 
Rate this item
(1 Vote)

 “እኛ ት/ቤት እጆች ይናገራሉ፤ ዓይኖች ያዳምጣሉ” የሚል መፈክር መሰል ማስታወቂያ በየቦታው ተለጥፎ ይታያል፡፡ አንዳንድ ተቋም ስሙና መፈክሩ ሳይቀር ይለያል፡፡ ስሜትና ትኩረት ይስባል፡፡ የማወጋችሁ በመዲናዋ አንድ ለእናቱ ስለሆነው ት/ቤት ነው። “አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት”። ት/ቤቱ በ1956 ዓ.ም የዛሬ 60 ዓመት በውጭ ሚሽነሪዎች የተመሰረተ ነው፡፡ መጀመሪያ ላይዓላማው ለት/ቤት ሳይሆን ለመፅሐፍ ቅዱስ ጥናት እንደነበር ይነገራል።በኋላ ላይ ግን መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችት/ቤት ሆነ፡፡ በአሁኑ ወቅት አምሳያ የሌለውብቸኛውመስማት የተሳናቸው ተማሪዎች ብቻ ትምህርታቸውን የሚከታተሉበት የመንግሥት ት/ቤት ነው ተብሏል። ሆኖም በ ሁሉ ነገሩ፡- በአስተዳደሩ፣ በአደረጃጀቱ፣ ተማሪዎቹን ለማገዝና ለውጤት ለማብቃት በሚያደርገው ጥረትና ተነሳሽነቱ እንዲሁም በችግር አፈታትዘዴው ፈጽሞ የመንግስት ት/ቤት አይመስልም።
ት/ቤቱ ከመንግሥት በዓመት 11 ሚሊዮን ብርበጀት እንደሚበጀትለት የሚናገሩት የት/ቤቱርዕሰ መምህር ወ/ሮ ከበቡሽ በቀለ፤ ይህም የሠራተኞችን ደሞዝ ጨምሮ አጠቃላይ ወጪዎችን ለመሸፈን የሚውል ነው ይላሉ። አልፋ በአሁኑ ጊዜ 125 መስማት የተሳናቸውን ልጆች ከኬጂ እስከ 8ኛ ክፍል እንደሚያስተምር የገለፁት ርዕሰ መምህሯ፤ ከእነዚህ ልጆች ውስጥ የተወሰኑት መስማት የተሳናቸው ብቻሳይሆኑ የአዕምሮ ውስንነት ያለባቸው ጭምር
መሆናቸውን ጠቁመዋል። ተደራራቢ ችግሮች ያለበትና ትኩረት ያላገኘ ት/ቤት መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮከበቡሽ፤ ከአዲስ አበባ የተለያዩ አቅጣጫዎች
ለሚመጡ 37 ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ ባንሸፍንላቸው ኖሮ ት/ቤት ላይመጡ ይችሉ ነበር ብለዋል። እንግዲህ የመንግስትት/ቤት ለተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ እንደማይሸፍን ይታወቃል፡፡ አልፋ ከየት አምጥቶ ነው ለ37 ቤታቸው ሩቅ ለሆነተማሪዎች የዕለት የትራንስፖርት ወጪያቸውን
የሚሸፍነው? ለዚህ ነው ይለያል ያልኳችሁ፡፡ የት/ቤቱ አመራሮች የራሳቸውን ችግር በራሳቸውየመፍታትና ከተለያዩ ወገኖች ጋር በትብብር የመሥራት ባህልና ልምድ አዳብረዋል፡፡ የ37ቱ ተማሪዎች የትራንስፖርት ወጪ የሚሸፈነው ት/ቤቱ ያለበትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችበተረዱና እጃቸውን ለእገዛ በዘረጉ እጆች ነው ተብሏል፡፡ እጆች እንዲዘረጉ ግን ት/ቤቱ መጀመሪያ ችግሩን በሚያሳምን መልኩ መናገርና መቀስቀስ አለበት፤ አንድ ጊዜና ሁለቴ ብቻ ሳይሆን ደጋግሞ - ዓመቱን ሙሉ፡፡ በነገራችን ላይ እኔም ባለፈው ሐሙስ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ት/ቤቱ ያቀናሁት፣አይ.ሲ.ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ ድጋፎችን ለት/ቤቱ እንደሚያደርግ ጥቆማ ደርሶኝ ነው። በእርግጥም የሆስፒታሉ አመራሮችበዕለቱ በት/ቤቱ ቅጥር ግቢ ተገኝተው፣
ለእንስት ተማሪዎች ለ6 ወር የሚያገለግል የንፅህና መጠበቂያ፣ 60 ደርዘን ደብተር እንዲሁም የዕደ-ጥበባት ማዕከልን ለማጠናከርና ለተማሪዎች ትራንስፖርት ወጪ የሚውል 99ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
   ተማሪዎቹ የኢኮኖሚ ችግር እንጂ ትምህርት የመቀበል ችግር እንደሌለባቸው በልበሙሉነት የተናገሩት ርዕሰ መምህሯ፤ እስካሁን ት/ቤቱበ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 100 ፐርሰንት ነው ያሳለፈው ብለዋል፡፡ ይህ ብቻ ግን አይደለም፡፡ ተማሪዎቹ በዕደ-ጥበብና በፈጠራሥራዎችም አ ልተቻሉም ነ ው የ ተባለው፡፡ በየጊዜው ከሌሎች ት/ቤቶች ጋር እየተወዳደሩ በርካታ ዋንጫዎች ለት/ቤቱ ማስገኘት እንደቻሉ ርዕሰ መምህሯ በድል አድራጊነት ስሜት ተናግረዋል። በእርግጥም ይሄንን እውነት በት/ቤቱ ለዘገባ የተሰባሰብን የሚዲያ ባለሙያዎች በሙሉ በዓይናችን ማረጋገጥ ችለናል፡፡ አንድ
ቢሮ ውስጥ ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት የሚበቃ የሚመስል ሥፍር ቁጥር የሌለው የዋንጫ ዓይነት ተደርድሯል፡፡ የአሸናፊነትና የስኬት አርማ ነው፡፡
የት/ቤቱን የዕደ-ጥበባትና የፈጠራ ማዕላት ተዟዙረን በጎበኘንበት ወቅት፣ ያ ሁሉ ዋንጫ በዘበት እንዳልተሰበሰበ ለመረዳት ችለናል።ተማሪዎች በልብስ ስፌት ማሽን ላይ ሥልጠና እየወሰዱ የሚሰሯቸው አልባሳት፣ መጋረጃዎች፣ ምንጣፎችና፣ የአልጋና ኮሞዲኖ ናሙናዎች ተዓምር የሚያሰኙ ናቸው። የዕደ-ጥበባትአሰልጣኞቹ እንደነገሩን፤ አንዳንዶቹ ተማሪዎች የልብስ ስፌት ማሽን የሚገዛላቸው ቢያገኙየራሳቸውን ሥራ ለመጀመር የሚያስችል
አቅምና ችሎታ አዳብረዋል፡፡አሁንም ለዚህ ሁሉ ውጤትና ስኬት የአንበሳውን ድርሻ የሚወስዱት ርዕሰ መምህሯንጨምሮ የአልፋ መምህራንና ሰራተኞች ናቸው፡፡
   ለዚህም ትልቅ ምስጋናና አድናቆት ይገባቸዋል። ከዚያም በ ላይ ግ ን ሁ ሉም ወ ገን የ አቅሙን ያህል ሊያግዛቸውና ሊደግፋቸው ይገባል።
አይ.ሲ.ኤም.ሲ አጠቃላይ ሆስፒታል በዕለቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ርዕሰ መምህሯ፤ እነዚህን ህፃናት መርዳት ማለትአገርን መርዳት ነው፤ ብለዋል፡፡ በነገራችን ላይ በአልፋ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚታየው የተማሪዎቹ የተስፋ ብርሃንና የመምህራኑ የመነቃቃት ስሜት በራሱ ለለውጥና
ለተጨማሪ ስኬት መንደርደርያ እንደሚሆናቸው አያጠራጥርም፡፡ በእርግጥም ህፃናትን መርዳት አገርን መርዳት ነው!!


Read 1036 times