እናቶች ልጅ ለመውለድ ሲያስቡ አስቀድሞ ወደ ሕክምናው ቀርበው በራሳቸው ጤንነት ጉዳይ ከባለሙያ ጋር በመምከር አሁን ልጅ ለመውለድ እችላለሁ ወይንም ለጅ ለመውለድ መጀመሪያ በጤንነት ጉዳይ ማስተካከል ያለብኝ ነገር አለ በሚል ሙሉ መረጃ ማግኘትና መሰናዶ ማድረግ ይጠበቅባቸወል፡፡ በእርግዝናው ወቅትም ሆነ ከወለዱ በሁዋላ ህክምናውን እንዲሁም የምክር አገልግሎቱን ቸል ማለት የለባቸውም እንደባለሙያዎቹ ማብራሪያ፡፡ ባለፈው እትም ልጅ ከወለዱ ባልና ሚስት ጋር ቆይታ አድርገን ከራሳቸው ልምድ መሆን አለበት ብለው የሚየምኑትን ለንባብ ማለታችን ይታወሳል፡፡ በጊዜውም ርእሱን የምንቋጨው በባለሙያዎች ድጋፍ እንደሚሆን ገልጸን ነበር፡፡ እነሆ በዚህ እትም በዚህ ዙሪያ ስልጠና የሚሰጥ የእናቶች መክሊት የተበለ ፕሮግራምን በሚመለከት ከባለሙያዎች እና ከእናቶች ያገኘነውን ለዚህ እትም ብለናል፡፡
ሃሳቡን ይዘን ያመራነው ሙሉ ጂ ጠቅላላ ሆስፒታል ነው፡፡ ሙሉ ጂ የዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ እና የባለቤታቸው ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የግል ሆስፒታል ነው፡፡ ሆስፒታሉ የእናቶችና ህጻናት እዲሁም የጠቅላላ ህክምና የሚሰጥበት ነው፡፡ መክሊት የተባለው እናቶች ቅድመ ወሊድም ሆነ ከወሊድ በሁዋላ ስለልጆቻቸው አስተዳደግ የሚሰለጥኑበት የተቋቋመው በዚህ ሆስፒታል አማካኝነት ነው፡፡
ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ ሀሳባቸውን እንደሚከተለው ነበር ያብራሩት፡፡
እኔ የጨቅላ ህጻናት ህክምና እስፔሻሊስት ብሆንም ላለፉት ሰላሳ ሰባት አመት ከህጻናት ጋር ነው የኖርኩት፡፡ በየካቲት ሆስፒታል ብቻ የህጻናት ሐኪም በመሆን ለ30/አመታት ሰርቻለሁ፡፡ ለእናትየው በልጁዋ ላይ የምታደርገው ክትትል ሁሉ በልጁ ላይ ይታያል፡፡ እናትየው ጥሩ ልምድና ስልጠና ወይንም እውቀት ከሌላት ልጅዋ ይጎዳል፡፡ እናትየው ከወለደች በሁዋላ ሳይሆን ከመውለድዋ በፊት እንዲያውም ሳታረግዝ አስቀድሞ ሁሉ በህክምና ተቅዋም ብሎም ስልጠናው በሚሰጥባቸው ቦታዎች እንድትገኝ ያስፈልጋል፡፡ እናትየው በውስጥ ደዌ ህመም የተያዘች ከሆነ ለምሳሌ እንደስኩዋር የደም ግፊት የመሳሰሉትን ለመከታተል ወይም በእርግዝናው ወቅት ችግር እንዳይከሰት ለመድረግ እንደሁም ሌሎች የአካል ብቃት ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንዲረዳ አስቀድማ መታየት ይጠቅማታል፡፡ ከዚህም በላይ ትዳር ሲመሰረት ከማን ጋር መሆን አለበት የሚለውን በጤና ጉዳይም ይሁን በሌሎች ምክንያቶች እንድትዘጋጅ የሚያደርጋትን ስልጠና ከባለሙያዎች እንድታገኝ ይረዳታል፡፡ ስለዚህ ከማርገዝዋ አስቀድሞ፤በእርግዝና ላይ እያለች፤እንዲሁም ከወለደች በሁዋላ ስልጠናውን ማግኘት ከቻለች በጥሩ ሁኔታ ልጅዋን ማሳደግ ትችላለች፡፡ ህጻናቱ ጨቅላ ከሚባለው ጀምረው በየደረጃው የሚገጥማቸው ህመም በአብዛኛው ማለትም ወደ 80% የሚሆነው የሚከሰተው በኢንፊክሽን ወይንም በመመረዝ ስለሆነ ያንን ልጆቹ ሳይጎዱ በፊት ለመከላከል የሚቻለው ስልጠናው ወይንም እውቀቱ ሲኖር ነው፡፡ ኢንፌክሽንን በመከላከል ሊድኑ የሚችሉ ልጆች ሳይደረስላቸው በመቅረቱ በመሬት ላይ ሲንፉዋቀቁ ያየንበትን ጊዜ መርሳት አይቻልም፡፡ እንደዚህ የተጎዱ ልጆች ለራሳቸው፤ለቤተሰባቸው ብሎም ለሀገራቸው አሳዛኝ ውጤቶች ናቸው፡፡
አዲስ የተወለድ ልጅ ማለት የሰው ልጅ መጀመሪያው ነው፡፡ ያ ልጅ ነው አድጎ ተምሮ አገር የሚረከበው፡፡ ስለዚህ ልጁ በሚያድግበት ጊዜ እያንዳንዱ የሰውነት አካሉ በሚገባው ደረጃ በእንክብካቤ ካላደገ ለነገ ተረካቢ የምንለው ልጅ አጉል ሆኖ ሊያልፍ ይችላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እናትየው በተፈጥሮአዊ መንገድ አርግዛ፤ ወልዳ እንደፈለገው ሆኖ ይደግ ማለት ሳይሆን ስለጤንነቱ፤ ስለጽዳቱ፤ ስለአመጋገቡ፤ ስለትምርቱ ምን ማድረግ እንደሚገባት አስቀድማ ማወቅዋ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ብለዋል የጨቅላ ህጻናት እስፔሻሊስት ዶ.ር ሙሉአለም ገሰሰ፡፡
በ ሙሉጂ ሆስፒታል አማክኝነት በተከፈተው የእናቶች መክሊት ሰልጠና ተጠቃሚ የሆኑ ሁለት እናቶችን አስተያየት እናስነብባችሁ፡፡
ጽጌ ማርያም የሁዋላሸት ትባላለች፡፡ ልጆዋን በማሳደጉ ረገድ ከስድስት አመት በላይ አሁንም ድረስ በህክምናም ይሁን በምክር አገልግሎቱ የዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ ደንበኛ ነች፡፡ ጽጌ ማርያም እንደሚከተለው ነበር ልዩነቱን የገለጸችው፡፡ ‹‹‹…በእርግጥ ከመውለዴ በፊት ዶ/ርን አላወቅሁ ዋትም ነበር፡፡ በሌላ ሆስፒታል ወልጄ ለልጄ ስል ነበር ወደ ሙሉጂ የመጣ ሁት፡፡ በዚህም የሚሰጠውን የእናቶች ሰስልጠና ስመለከት ምነው ከመውለዴ በፊት መረጃው ቢኖረኝና ብጠቀምበት ኖሮ የሚል ቁጭት ነው ያደረብኝ፡፡ እኔ የወለድኩበት ሆስፒታል በእርግዝና ወቅት የሚሰጥ ስልጠና የሚባል ነገር አላየሁም፡፡ ምናልባት እናትየው ለምርመራ ስትቀርብ ሐኪምዋ ሊነግራት የሚገባው ነገር ካለ ይነግራታል እንጂ ከዚያ በተረፈ ግን በመክሊት ያየሁትን ስልጠና እኔ የወለድኩበት ሆስፒታል ሲሰጥ አላየሁም፡፡
እናት ጽጌ ማርያም በመቀጠልም የእናት መክሊት በሚል ቴሌግራም ላይ የተከፈተው ቻናል ላይ ከጤና ባለሙያዎች፤ከእናቶች ፤ከዶ/ር ሙሉአለም የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች ምንጊዜም ልጅን ለማሳደግ የሚያገለግሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ልጆች ከመረገዛቸው በፊት፤ከተረገዙም በሁዋላ ፤ከተወለዱም በሁዋላ ምን ማድረግ እንደሚገባ የሚሰጠው ምክር እና ስልጠና ሐኪም ቤት መሄድ ሳያስፈልግ ልጅን በተገቢው መንገድ ለማሳደግ ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ፡፡ ልጅ ከተወለደ በሁዋላ አመጋገቡ ምን መምሰል አለበት፤የጽዳት አጠባበቁ ፤ቤታችንን እንዴት መያዝ እንዳለብን፤ኢንፌክሽንን እንዴት መከላል እንዳለብን የመሳሰሉትን ሁሉ ስለምትነግረን እንዲያው ብድግ ብሎ ወደሆስፒታል መሄድ ወይንም ለሚፈጠረው አጋጣሚ ሁሉ መድሀኒተን መስጠት አያስፈልገንም ብላለች፡፡
ሌላዋ እናት ሰላም ግርማ ትባላለች፡፡ የሁለት ልጆች እናት ናት፡፡ ሙሉጂ ስከታተል ወደ ሁለት አመት ይሆነኛል፡፡ ወደሆስፒታሉ የመጣሁበት አጋጣሚ ጥሩ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በዶ/ር እርዳታ ልጄ ተሸሎአት ከሆስፒታል ወጥታልኛለች፡፡ ወደሆስፒታሉ ስመጣ ልጄ ኒሞኒያ ይዞአት በጣም መተንፈስ አቅቶአት ፤ደክማ፤ምግብ አቁማ በሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነበረች፡፡ ልጅትዋ የአንድ አመት ልጅ ነበረች፡፡ ገና ወደ ዶ/ር ጋ ስንገባ እየሳለች ስለነበር ምንም ሳትመረምራት ገና በማዳመጥ ነበር ያወቀችላት፡፡ በሌላ ሐኪም ታዞላት የነበረውን መድሀኒት አውጥተን ጉንፋን ተብላ ይሄ ታዞላት ነበር ስንል ዶ/ር አይደለም በማለት በሽታውን ነገረችን፡፡ እኔ ደግሞ በወቅቱ እርጉዝም ስለነበርኩ ሁኔታው እጅግ አስደንግጦኝ ሳለቅስ….የለም የለም ማልቀስማ የለብሽም በማለት ከህክምናው ጎን ለጎን ለእኔም የምክር አገልግሎት ስትሰጠኝ ነበር፡፡ ዛሬ ልጄ እጅግ በጣም ጤነኛ ናት፡፡ ከዚያ በሁዋላ የእናት መክሊትን አወቅሁ፡፡ ግን ቀድሜ ባውቀው ኖሮ ይህች ለሞት ደርሳ የነበረች ለጄ በዚያ ደረጃ ለህመም አትዳረግም ነበር፡፡ በጊዜው የተወለደችበት ሆስፒታል ከህጻናት ሐኪም ጋ አቅርቤአት የነበረ ሲሆን ከባለሙያው የተሰጠኝ መልስ ግን እጅግ አሳዝኖኛል፡፡የማያቋርጥ ትኩሳት የነበራት ሲሆን ከዚያ በላይ ከፍና ዝቅ ሊል ስለሚችል ሰፖዚተሪ ስጫት ብሎ ነው የመለሰኝ፡፡ ህመምዋ ምንድነው ስለውም ህጻናት ላይ ያጋጥማል ነበር ያለኝ፡፡ ስለዚህ እናቶች ለልጆቻቸው በጣም ሊያስቡ ይገባል፡፡ መጠራጠር ፤መጠየቅ፤ትክክለኛው ህክምና የት ይገኛል የምክር አገልግሎትስ የት ይገኛል የሚለውን መፈተሸ ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም እንደ መክሊት ለእናቶች አይነት የስልጠና ማእከል ካለ መሳተፍ፤መካፈል ለሌሎችም ለመሰሎቻችን መረጃ መስጠት ከእኛ ይጠበቃል ነበር ያለችው እናት ሰላም ግርማ፡፡
ዶ/ር ሙሉአለም የስራ ውሎአቸውን ሲያስታውሱ በየካቲት ሆስፒታል ለአስራ አምስት አመት በጠቅላላ ሐኪምነት ለአስራ አምስት አመት ደግሞ በእስፔሻሊስትነት ህጻናቱን በማከም ስራ ሲሰሩ የሚያጋጥሙአቸው ብዙ ሰዎች ስለነበሩ የጎደለውን ነገር ለመታዘብ እንደረዳቸው ይገልጻሉ፡፡ ከሰዎች ሁኔታ የታዘቡአቸውን ነገሮች ለማስተካከል ስህተቶችን ላለመድገም መጀመሪያ ለባለሙያዎች፤በመቀጠልም ልጆች ክትትል ስለሚያስፈልጋቸው እናቶች ሰብሰብ ብለው እንዲገናኙ እና ስልጠና ወይንም ምክር እንዲያገኙ የሚቻልበት ቦታ መፍጠር ሌላው አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እናቶች ጨቅላ ህጻኖቻቸውን መተንፈስ ካቆሙ ወይንም ህይወታቸው ካለፈ በሁዋላ ወደሆስፒታል ይዘው የሚመጡበት ጊዜ ያጋጥማል፡፡ ይህም የሞት ምልክቱን እንኩዋን ካለማወቃቸው የተነሳ ጨቅላ ህጻን ዝም ማለት ደንቡ ነው ከሚል የመነጨ ነው ፡፡ በአገራችን የተማሩ፤ያልተማሩ፤ረዳት ያላቸው፤ረዳት የሌላቸው….ብዙ አይነት እናቶች አሉ፡፡ወደ ባለሙያዎቹ ስንሄድ ነርሶች፤ሐኪሞች ህጻናቱን ማትረፍ ወይም ለተወለዱት ድጋፍ የሚለው ነገር በትምህርታቸው ወቅት ያልተካተተላቸው ነበሩ፡፡ ይህ ዘርፍ ቀድሞ ያልታወቀና ምናልባትም ከአስራ አምስት አመት ወዲህ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከውጭም ድጋፍ ከሚያደርጉ ጋር በመተባበር ስልጠናው መሰጠት ተጀምሮአል፡፡ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሙሉአለም በማስከተልም በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በመላው አለም ህጻናቱ የሚሞቱባቸው ሶስት ምክንያቶች አሉ፡፡ እነሱም አንዱ መታፈን፤ ልጁ ሲወለድ ታፍኖ ከወጣ ወዲያው ማስተንፈስ ያስፈልጋል፡፡ሁለተኛው ኢንፌክሽን ነው፡፡ ህጻናቱ መከላከያ ስለሌላቸው መመረዝ ወይንም ኢንፌክሽን ሊያጠቃቸው ይችላል፡፡ ሶስተኛው ጊዜያቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ህጻናቱን ለማዳን ሐኪሞችን፤ነርሶችን…ወዘተ ብቻ ሳይሆን እናቶችም ቢሰለጥኑ ልጆቻቸውን ከጉዳት ሊከላከሉ ይችላሉ በሚል እምነት የተጀመረ ነው የእናት መክሊት ስልጠና ብለዋል ዶ/ር፡፡ እናቶች ልጅ ለመውለድ ሲያስቡ አስቀድሞ ወደ ሕክምናው ቀርበው በራሳቸው ጤንነት ጉዳይ ከባለሙያ ጋር በመምከር አሁን ልጅ ለመውለድ እችላለሁ ወይንም ለጅ ለመውለድ መጀመሪያ በጤንነት ጉዳይ ማስተካከል ያለብኝ ነገር አለ በሚል ሙሉ መረጃ ማግኘትና መሰናዶ ማድረግ ይጠበቅባቸወል፡፡ በእርግዝናው ወቅትም ሆነ ከወለዱ በሁዋላ ህክምናውን እንዲሁም የምክር አገልግሎቱን ቸል ማለት የለባቸውም እንደባለሙያዎቹ ማብራሪያ፡፡ ባለፈው እትም ልጅ ከወለዱ ባልና ሚስት ጋር ቆይታ አድርገን ከራሳቸው ልምድ መሆን አለበት ብለው የሚየምኑትን ለንባብ ማለታችን ይታወሳል፡፡ በጊዜውም ርእሱን የምንቋጨው በባለሙያዎች ድጋፍ እንደሚሆን ገልጸን ነበር፡፡ እነሆ በዚህ እትም በዚህ ዙሪያ ስልጠና የሚሰጥ የእናቶች መክሊት የተበለ ፕሮግራምን በሚመለከት ከባለሙያዎች እና ከእናቶች ያገኘነውን ለዚህ እትም ብለናል፡፡
ሃሳቡን ይዘን ያመራነው ሙሉ ጂ ጠቅላላ ሆስፒታል ነው፡፡ ሙሉ ጂ የዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ እና የባለቤታቸው ዶ/ር ገመቺስ ማሞ የግል ሆስፒታል ነው፡፡ ሆስፒታሉ የእናቶችና ህጻናት እዲሁም የጠቅላላ ህክምና የሚሰጥበት ነው፡፡ መክሊት የተባለው እናቶች ቅድመ ወሊድም ሆነ ከወሊድ በሁዋላ ስለልጆቻቸው አስተዳደግ የሚሰለጥኑበት የተቋቋመው በዚህ ሆስፒታል አማካኝነት ነው፡፡
ዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ ሀሳባቸውን እንደሚከተለው ነበር ያብራሩት፡፡
እኔ የጨቅላ ህጻናት ህክምና እስፔሻሊስት ብሆንም ላለፉት ሰላሳ ሰባት አመት ከህጻናት ጋር ነው የኖርኩት፡፡ በየካቲት ሆስፒታል ብቻ የህጻናት ሐኪም በመሆን ለ30/አመታት ሰርቻለሁ፡፡ ለእናትየው በልጁዋ ላይ የምታደርገው ክትትል ሁሉ በልጁ ላይ ይታያል፡፡ እናትየው ጥሩ ልምድና ስልጠና ወይንም እውቀት ከሌላት ልጅዋ ይጎዳል፡፡ እናትየው ከወለደች በሁዋላ ሳይሆን ከመውለድዋ በፊት እንዲያውም ሳታረግዝ አስቀድሞ ሁሉ በህክምና ተቅዋም ብሎም ስልጠናው በሚሰጥባቸው ቦታዎች እንድትገኝ ያስፈልጋል፡፡ እናትየው በውስጥ ደዌ ህመም የተያዘች ከሆነ ለምሳሌ እንደስኩዋር የደም ግፊት የመሳሰሉትን ለመከታተል ወይም በእርግዝናው ወቅት ችግር እንዳይከሰት ለመድረግ እንደሁም ሌሎች የአካል ብቃት ሁኔታዎችን ለማስተካከል እንዲረዳ አስቀድማ መታየት ይጠቅማታል፡፡ ከዚህም በላይ ትዳር ሲመሰረት ከማን ጋር መሆን አለበት የሚለውን በጤና ጉዳይም ይሁን በሌሎች ምክንያቶች እንድትዘጋጅ የሚያደርጋትን ስልጠና ከባለሙያዎች እንድታገኝ ይረዳታል፡፡ ስለዚህ ከማርገዝዋ አስቀድሞ፤በእርግዝና ላይ እያለች፤እንዲሁም ከወለደች በሁዋላ ስልጠናውን ማግኘት ከቻለች በጥሩ ሁኔታ ልጅዋን ማሳደግ ትችላለች፡፡ ህጻናቱ ጨቅላ ከሚባለው ጀምረው በየደረጃው የሚገጥማቸው ህመም በአብዛኛው ማለትም ወደ 80% የሚሆነው የሚከሰተው በኢንፊክሽን ወይንም በመመረዝ ስለሆነ ያንን ልጆቹ ሳይጎዱ በፊት ለመከላከል የሚቻለው ስልጠናው ወይንም እውቀቱ ሲኖር ነው፡፡ ኢንፌክሽንን በመከላከል ሊድኑ የሚችሉ ልጆች ሳይደረስላቸው በመቅረቱ በመሬት ላይ ሲንፉዋቀቁ ያየንበትን ጊዜ መርሳት አይቻልም፡፡ እንደዚህ የተጎዱ ልጆች ለራሳቸው፤ለቤተሰባቸው ብሎም ለሀገራቸው አሳዛኝ ውጤቶች ናቸው፡፡
አዲስ የተወለድ ልጅ ማለት የሰው ልጅ መጀመሪያው ነው፡፡ ያ ልጅ ነው አድጎ ተምሮ አገር የሚረከበው፡፡ ስለዚህ ልጁ በሚያድግበት ጊዜ እያንዳንዱ የሰውነት አካሉ በሚገባው ደረጃ በእንክብካቤ ካላደገ ለነገ ተረካቢ የምንለው ልጅ አጉል ሆኖ ሊያልፍ ይችላል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ እናትየው በተፈጥሮአዊ መንገድ አርግዛ፤ ወልዳ እንደፈለገው ሆኖ ይደግ ማለት ሳይሆን ስለጤንነቱ፤ ስለጽዳቱ፤ ስለአመጋገቡ፤ ስለትምርቱ ምን ማድረግ እንደሚገባት አስቀድማ ማወቅዋ እጅግ ጠቃሚ ነው፡፡ ብለዋል የጨቅላ ህጻናት እስፔሻሊስት ዶ.ር ሙሉአለም ገሰሰ፡፡
በ ሙሉጂ ሆስፒታል አማክኝነት በተከፈተው የእናቶች መክሊት ሰልጠና ተጠቃሚ የሆኑ ሁለት እናቶችን አስተያየት እናስነብባችሁ፡፡
ጽጌ ማርያም የሁዋላሸት ትባላለች፡፡ ልጆዋን በማሳደጉ ረገድ ከስድስት አመት በላይ አሁንም ድረስ በህክምናም ይሁን በምክር አገልግሎቱ የዶ/ር ሙሉአለም ገሰሰ ደንበኛ ነች፡፡ ጽጌ ማርያም እንደሚከተለው ነበር ልዩነቱን የገለጸችው፡፡ ‹‹‹…በእርግጥ ከመውለዴ በፊት ዶ/ርን አላወቅሁ ዋትም ነበር፡፡ በሌላ ሆስፒታል ወልጄ ለልጄ ስል ነበር ወደ ሙሉጂ የመጣ ሁት፡፡ በዚህም የሚሰጠውን የእናቶች ሰስልጠና ስመለከት ምነው ከመውለዴ በፊት መረጃው ቢኖረኝና ብጠቀምበት ኖሮ የሚል ቁጭት ነው ያደረብኝ፡፡ እኔ የወለድኩበት ሆስፒታል በእርግዝና ወቅት የሚሰጥ ስልጠና የሚባል ነገር አላየሁም፡፡ ምናልባት እናትየው ለምርመራ ስትቀርብ ሐኪምዋ ሊነግራት የሚገባው ነገር ካለ ይነግራታል እንጂ ከዚያ በተረፈ ግን በመክሊት ያየሁትን ስልጠና እኔ የወለድኩበት ሆስፒታል ሲሰጥ አላየሁም፡፡
እናት ጽጌ ማርያም በመቀጠልም የእናት መክሊት በሚል ቴሌግራም ላይ የተከፈተው ቻናል ላይ ከጤና ባለሙያዎች፤ከእናቶች ፤ከዶ/ር ሙሉአለም የሚገኙ ጠቃሚ ነገሮች ምንጊዜም ልጅን ለማሳደግ የሚያገለግሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ልጆች ከመረገዛቸው በፊት፤ከተረገዙም በሁዋላ ፤ከተወለዱም በሁዋላ ምን ማድረግ እንደሚገባ የሚሰጠው ምክር እና ስልጠና ሐኪም ቤት መሄድ ሳያስፈልግ ልጅን በተገቢው መንገድ ለማሳደግ ይጠቅማል ብዬ አምናለሁ፡፡ ልጅ ከተወለደ በሁዋላ አመጋገቡ ምን መምሰል አለበት፤የጽዳት አጠባበቁ ፤ቤታችንን እንዴት መያዝ እንዳለብን፤ኢንፌክሽንን እንዴት መከላል እንዳለብን የመሳሰሉትን ሁሉ ስለምትነግረን እንዲያው ብድግ ብሎ ወደሆስፒታል መሄድ ወይንም ለሚፈጠረው አጋጣሚ ሁሉ መድሀኒተን መስጠት አያስፈልገንም ብላለች፡፡
ሌላዋ እናት ሰላም ግርማ ትባላለች፡፡ የሁለት ልጆች እናት ናት፡፡ ሙሉጂ ስከታተል ወደ ሁለት አመት ይሆነኛል፡፡ ወደሆስፒታሉ የመጣሁበት አጋጣሚ ጥሩ አልነበረም፡፡ ነገር ግን በዶ/ር እርዳታ ልጄ ተሸሎአት ከሆስፒታል ወጥታልኛለች፡፡ ወደሆስፒታሉ ስመጣ ልጄ ኒሞኒያ ይዞአት በጣም መተንፈስ አቅቶአት ፤ደክማ፤ምግብ አቁማ በሚያስፈራ ሁኔታ ላይ ነበረች፡፡ ልጅትዋ የአንድ አመት ልጅ ነበረች፡፡ ገና ወደ ዶ/ር ጋ ስንገባ እየሳለች ስለነበር ምንም ሳትመረምራት ገና በማዳመጥ ነበር ያወቀችላት፡፡ በሌላ ሐኪም ታዞላት የነበረውን መድሀኒት አውጥተን ጉንፋን ተብላ ይሄ ታዞላት ነበር ስንል ዶ/ር አይደለም በማለት በሽታውን ነገረችን፡፡ እኔ ደግሞ በወቅቱ እርጉዝም ስለነበርኩ ሁኔታው እጅግ አስደንግጦኝ ሳለቅስ….የለም የለም ማልቀስማ የለብሽም በማለት ከህክምናው ጎን ለጎን ለእኔም የምክር አገልግሎት ስትሰጠኝ ነበር፡፡ ዛሬ ልጄ እጅግ በጣም ጤነኛ ናት፡፡ ከዚያ በሁዋላ የእናት መክሊትን አወቅሁ፡፡ ግን ቀድሜ ባውቀው ኖሮ ይህች ለሞት ደርሳ የነበረች ለጄ በዚያ ደረጃ ለህመም አትዳረግም ነበር፡፡ በጊዜው የተወለደችበት ሆስፒታል ከህጻናት ሐኪም ጋ አቅርቤአት የነበረ ሲሆን ከባለሙያው የተሰጠኝ መልስ ግን እጅግ አሳዝኖኛል፡፡የማያቋርጥ ትኩሳት የነበራት ሲሆን ከዚያ በላይ ከፍና ዝቅ ሊል ስለሚችል ሰፖዚተሪ ስጫት ብሎ ነው የመለሰኝ፡፡ ህመምዋ ምንድነው ስለውም ህጻናት ላይ ያጋጥማል ነበር ያለኝ፡፡ ስለዚህ እናቶች ለልጆቻቸው በጣም ሊያስቡ ይገባል፡፡ መጠራጠር ፤መጠየቅ፤ትክክለኛው ህክምና የት ይገኛል የምክር አገልግሎትስ የት ይገኛል የሚለውን መፈተሸ ይገባቸዋል፡፡ በተጨማሪም እንደ መክሊት ለእናቶች አይነት የስልጠና ማእከል ካለ መሳተፍ፤መካፈል ለሌሎችም ለመሰሎቻችን መረጃ መስጠት ከእኛ ይጠበቃል ነበር ያለችው እናት ሰላም ግርማ፡፡
ዶ/ር ሙሉአለም የስራ ውሎአቸውን ሲያስታውሱ በየካቲት ሆስፒታል ለአስራ አምስት አመት በጠቅላላ ሐኪምነት ለአስራ አምስት አመት ደግሞ በእስፔሻሊስትነት ህጻናቱን በማከም ስራ ሲሰሩ የሚያጋጥሙአቸው ብዙ ሰዎች ስለነበሩ የጎደለውን ነገር ለመታዘብ እንደረዳቸው ይገልጻሉ፡፡ ከሰዎች ሁኔታ የታዘቡአቸውን ነገሮች ለማስተካከል ስህተቶችን ላለመድገም መጀመሪያ ለባለሙያዎች፤በመቀጠልም ልጆች ክትትል ስለሚያስፈልጋቸው እናቶች ሰብሰብ ብለው እንዲገናኙ እና ስልጠና ወይንም ምክር እንዲያገኙ የሚቻልበት ቦታ መፍጠር ሌላው አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ አንዳንድ ጊዜ እናቶች ጨቅላ ህጻኖቻቸውን መተንፈስ ካቆሙ ወይንም ህይወታቸው ካለፈ በሁዋላ ወደሆስፒታል ይዘው የሚመጡበት ጊዜ ያጋጥማል፡፡ ይህም የሞት ምልክቱን እንኩዋን ካለማወቃቸው የተነሳ ጨቅላ ህጻን ዝም ማለት ደንቡ ነው ከሚል የመነጨ ነው ፡፡ በአገራችን የተማሩ፤ያልተማሩ፤ረዳት ያላቸው፤ረዳት የሌላቸው….ብዙ አይነት እናቶች አሉ፡፡ወደ ባለሙያዎቹ ስንሄድ ነርሶች፤ሐኪሞች ህጻናቱን ማትረፍ ወይም ለተወለዱት ድጋፍ የሚለው ነገር በትምህርታቸው ወቅት ያልተካተተላቸው ነበሩ፡፡ ይህ ዘርፍ ቀድሞ ያልታወቀና ምናልባትም ከአስራ አምስት አመት ወዲህ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴርና ከውጭም ድጋፍ ከሚያደርጉ ጋር በመተባበር ስልጠናው መሰጠት ተጀምሮአል፡፡ብለዋል፡፡
ዶ/ር ሙሉአለም በማስከተልም በኢትዮጵያ ብቻም ሳይሆን በመላው አለም ህጻናቱ የሚሞቱባቸው ሶስት ምክንያቶች አሉ፡፡ እነሱም አንዱ መታፈን፤ ልጁ ሲወለድ ታፍኖ ከወጣ ወዲያው ማስተንፈስ ያስፈልጋል፡፡ሁለተኛው ኢንፌክሽን ነው፡፡ ህጻናቱ መከላከያ ስለሌላቸው መመረዝ ወይንም ኢንፌክሽን ሊያጠቃቸው ይችላል፡፡ ሶስተኛው ጊዜያቸው ሳይደርስ የሚወለዱ ናቸው፡፡ ስለዚህ ህጻናቱን ለማዳን ሐኪሞችን፤ነርሶችን…ወዘተ ብቻ ሳይሆን እናቶችም ቢሰለጥኑ ልጆቻቸውን ከጉዳት ሊከላከሉ ይችላሉ በሚል እምነት የተጀመረ ነው የእናት መክሊት ስልጠና ብለዋል ዶ/ር፡፡
Saturday, 25 May 2024 00:00
የእናቶች መክሊት፡፡
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ