Saturday, 22 June 2024 00:00

ካንሰር….በ20 እና 30 አመት እድሜ...

Written by  ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

በዚህ እትም እንግዳችን ያደረግናት ባለሙያ ዶ/ር ማርያማዊት አስፋው ትባላለች፡፡ ዶ/ር ማርያማዊት የማህጸን ካንሰር ህክምና እስፔሻሊስት ነች፡፡በሌላ አባባልም የሴቶች የመራቢያ አካላት ካንሰር ህክምና እስፔሻሊስት ማለት ነው፡፡ ዶ/ር ማርያማዊትን ያገኘናት በካዛንቺስ አካባቢ መቅረዝ ከሚባል ሆስፒታል ውስጥ በስራ ላይ እያለች ነው፡፡ ዶ/ር ማርያማዊት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤቱ ዲን በመሆንም እያገለገለች ትገኛለችት ዶ/ር ማርያማዊት ከአሁን ቀደምም የዚህ አምድ እንግዳ እንደነበረች አይዘነጋም፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጽንስና ማህጸን ህክምና እስፔሻሊስት ሆና በምትሰራበት ጊዜ ወደ ውጭ ሐገር ለተወሰኑ ጊዜያት በመሄድ የኦንኮሎጂ ጋይኒኮሎጂ ወይንም የመራቢያ አካላት ካንሰር ሕክምናውን ተመርቃ መጥታለች፡፡ ትምህርትዋን ጨርሳ ከመጣች በሁዋላ ነበር የዚህ አምድ እንግዳ ያደረግናት፡፡  በጊዜው በኢትዮጵያ በሀገር አቀፍ ደረጃ በዚህ ሕክምና ላይ ከነበሩ ውስን ወንድ ሐኪሞች በስተቀር ሴቶች በዘርፉ አልተሰማሩም ነበርና የመጀመሪያዋ የመራቢያ አካላት ካንሰር ህክምና ሴት እስፔሻሊስት መሆንዋም ጭምር አዲስ ስኬት ነበር፡፡
ለጥያቄአችን መነሻ ያደረግነው ዶ/ር ማርያማዊት ለኦንኮሎጂ ጋይኒኮሎጂ ሙያ በበቃችበት ወቅት የነበረውን የካንሰር ታካሚዎች ሁኔታ እና አሁን ያለውን እንድታነ ጻጽርልን ነበር፡፡  እንደሚከተለው ነበር መልስዋ፡፡
‹….እኔ ወደዚህ ትምህርት በገባሁበት ወቅት ሙያው በአገራችን ያልተስፋፋ እና ገና የተጀ መረበት ሁኔታ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ለካንሰር ህክምና እስፔሻሊስት ለመሆን ወደትም ህርት በገባሁበት ወቅት በእኛ ሐገር የካንሰር ሕክምና አገልግሎት እና የባለሙያ ቁጥር እንደዚህ እንደአሁኑ አልነበረም፡፡ በእርግጥ በሙያው በተለይ ባይሰለጥኑም የነበሩትን የካንሰር ሕመም ተኞች ሲያክሙ እና አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ ነባር የጽንስና ማህጸን ሐኪሞች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ከዚያ በተረፈ ግን ትምህርቱ ወይንም እስፔሻላይዜሽኑ በግልጽ ተለይቶ ስራ ላይ የዋለ አልነበረም፡፡ ነገር ግን ሕክምናው እየተሸሻለ አለም ከደረሰችበት ደረጃ በአጭር ጊዜ ሙሉ በሙሉ  መድረስ ባይቻልም እንኩዋን የተቻለውን ያህል ታካሚዎችን ማገልገል ስለሚያስፈልግ ከዚያ የተነሳ በተገኘው እድል ተጠቅሜ በመማሬ አገልግሎቱን እየሰጠሁ እገኛለሁ፡፡ የካንሰር ሕመም ትንሽ አስፈሪ ነው፡፡ ገና ስሙ ሲጠራ ብቻ ሰውን ተስፋ ወደ ማስቆረጥ የሚደርስ ሕመም ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ሕመም የተያዙ ሰዎችን በትንሹም ቢሆን መርዳት ከተቻለ ቀላል አይደለምና በዚህ ረገድ እኔ ደግሞ ምን አስተዋጽኦ አደርጋለሁ ከሚል የተሰማራሁበት  ነው፡፡ የማህጸን ካንሰር ሕመም መኖሩ ከተረጋገጠ ጀምሮ ታካሚዋን ከማሳመን ጀምሮ በየደረጃው የሚሰጡ ሕክምናዎችን አልፎ በተለይም ወደ ኦፕራሲዮን ሲመራ እና ሕክምናው ሲሰጥ ጥንቃቄ እና ዝግጅትን የሚጠይቅ ከመሆኑም በላይ ቀላል የሚባልም አይደለም፡፡ በመጠኑም ቢሆን አስቸጋሪ ነገርን መወጣት ስለሚያስፈልግ እኔ ደግሞ ብዚ ጊዜ በችግሮቹ ማለፍና ውጤታማ የሆነ ስራን መስራት ስለምወድ እወጣዋለሁ ብዬ  የተሰማራሁበት ሙያ ነው …..››ብላለች ዶ/ር ማርያማዊት፡፡
ዶ/ር ማርያማዊት ለኦንኮሎጂ ጋይኒኮሎጂ ትምህርት ወደውጭ ሀገር ስትሄድ በሀገራችን የነበረው የታካሚ ሁኔታ ከአሁኑ ወቅት ጋር እንዴት ይነጻጻራል የሚል ጥያቄም አስከትለናል፡፡
‹‹…...የኦንኮሎጂ ጋይኒኮሎጂ ትምህርቴን ጨርሼ የመጣሁት በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2018/ዓም ነው፡፡ እኔ የመጀመሪያውን ሁኔታ ሳስታውስ….እኔ የጽንስና ማህጸን ሕክምና እስፔሻላይዜሽኑን በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ነበር የተማርኩት፡፡ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የጨረር ሕክምናው ያለበት ብቸኛው ሆስፒታል ስለነበረ በመላው ሐገሪቱ ማለት በሚያስችል ሁኔታ በካንሰር ሕመም የተያዙ ለህክምናው የሚመጡበት ሆስፒታል ነበር፡፡ በተለይም የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር የያዛቸው ሴቶች ለህክምናው ሲመጡ ብዙዎቹ እጅግ በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ላይ እየደረሱ ነበር፡፡ ምክንያቱም ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡት ደረጃው ከመጨረሻ ደረጃ ከደረሰ በሁዋላ ስለነበር የጨረር ሕክምናው እራሱ የተወሰኑ እንደ ደም መድማት የመሳሰሉትን ለመቀነስ ካልሆነ በስተቀር ህክምና መስጠት ነው የማይባልበት ደረጃ ነበር፡፡ የሚመጡት ታካሚዎች ፈሳሽ በጣም ብዙ ይኖራቸዋል፡፡ ፈሳሹ እጅግ በጣም መጥፎ ሽታ አለው፡፡ ከበሽታውም ባሻገር እናቶቹ ከቤተሰብ ፤ከጎረቤት፤ባጠቃላይም ከማህበራዊ ሕይወት እራሳቸውን አግልለው የሚቀ መጡበት አሳዛኝ ነገሮች የሚስተዋልበት ነበር፡፡ በጊዜው ለእነዚህ ታካሚዎች የመዳኛ መንገድ ተደርጎ የሚሰጥ ሕክምናም ስላልነበረ ታካሚዎቹ ወደተ ኙበት ክፍል መግባት እስከሚጨንቀን ድረስ እንደርስ ነበር፡፡ ምክንያቱም ቀደም ባለው ጊዜ ካንሰሩ ደረጃውን አልፎ መዳን እስከማ ይችልበት ድረስ ታካሚዎች ለህክምናው ሳይቀርቡ ስለሚቆዩም ነበር፡፡ አሁን እንደማየው ከሆነ ግን  ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ቀደም ብሎ ወደህክምናው የመምጣት እንዲሁም ቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ የመሳሰሉት ልምዶች እየተስፋፉ ታካሚዎችም በጊዜ ወደ ባለሙያ እየቀረቡ መሆኑን መመልከት ችያለሁ፡፡ በእርግጥ አሁንም ቢሆን ችግሮቹ ሁሉም አንድ አይነት ባለመ ሆናቸው ሁሉንም በቅድሚያ አውቀን ህክምና እየሰጠን ነው ማለት አንችልም፡፡ ግን ቀድመው ወደህክምና ከቀረቡና ካንሰሩ ገና ከጅምሩ ከታወቀ ህክምናውን ለመስጠት ባለሙያ ውም አገል ግሎቱም ቀደም ካለው ጊዜ ይልቅ አሁን በተሻለ ሁኔታ ይገኛል ብዬ መመስከር እችላለሁ ብላ ለች ዶ/ር ማርያማዊት፡፡
ወደ መቅረዝ ሆስፒታል መለስ ብለን ዶ/ር ማርያማዊትን የጠየቅናት ጥያቄ ነበር፡፡ በሆስፒታሉ የእናቶችና ህጻናት ሕክምና በምን ደረጃ ይሰጣል የሚል ነበር፡፡ ዶ/ር ማርያማዊትም ስትመ ልስ ‹‹….በሆስፒታሉ ለተለያዩ ህመሞች ህክምናዎች ይሰጣሉ፡፡ ለምሳሌ እኔ የማህጸን ካንሰር ሐኪም በመ ሆኔ ሴቶች ለህክምናው ሲቀርቡ ከሌሎች የስነተዋልዶ ጤና ጉድለት ተነስቶ እስከ መራቢየ አካል ካን ሰር ድረስ ላለው ሕክምና በቀጥታ አገልግሎቱን እንሰጣቸዋለን፡፡ የእርግዝና ክትትል እንዲሁም ከወሊድ ጋር ተያይዘው የሚሰጡ ህክምናዎችም አብረው ይሰጣሉ፡፡ መው ለድ ያቃታቸው ወይንም የመሃንነት ሕክምናም በሆስፒታሉ አገልግሎት የተካተተ ነው፡፡ የማህ ጸን ወደ ውጭ መው ጣት፤ ከሽንት ጋር ተያይዞ መቆጣጠር አለመቻል፤ ኢንፌክሽን ጋር ተያ ይዞ የሚከሰቱ ህክም ናዎችም ይሰጣሉ፡፡ የህጻናት ክትትል፤ኦፕራስዮን…ወዘተ ህክምና ጭምር በሆስፒ ታሉ ይሰጣሉ በማለት  አብራርታልናለች፡፡
የካንሰር ሕክምናውን በሚመለከት እስከምን ድረስ በሆስፒታሉ መታከም ይቻላል የሚለውን ጥያቄ አንስተን ነበር፡፡ ዶ/ር እንዳለችውም ከጨረር ሕክምናው በስተቀር የተቀረው ሕክምና በመቅረዝ እንደሚሰጥ ነግራናለች፡፡ የጨረር ሕክምናው በሀገር አቀፍ ደረጃ ከጥቁር አንበሳ ውጭ አንደ ኛው ሐረማያ ሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን ሌላው ደግሞ በጅማ ሆስፒታል ይሰጣል፡፡ ወደፊት እንግዲሀ ቁጥሩ ይጨምራል ብለን ተስፋ የምናደርግ ሲሆን በተለይም በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የጨረር ሕክምናው መሳሪያ ይኖራል ተብሎ ተስፋ ይደረጋል ብላ ለች፡፡  
የካንሰር ሕመምን በሚመለከት ዶ/ር ማርያማዊት እንደገለጸችው…በፊት በነበረው ሁኔታ በእድ ሜአቸው ገፋ ያሉ ማለትም ከሀምሳ ከስድስ አመት ጀምሮ ባለው ሁኔታ የካንሰር ሕመሙ የሚ ከሰት ሲሆን አሁን አሁን ግን በእድሜአቸው ከወጣትነት ጊዜ ያላለፉ የሀያ እና ሳላሳ አመት እድሜ ባላቸው ሴቶች ላይም ሲከሰት ይስተዋላል፡፡ በእርግጥ በህጻንነት እድሜ አልፎ አልፎ የሚከሰት የካንሰር ሕመም መኖሩ ባይካድም አሁን ያለው ሁኔታ ግን አሳሳቢ ነው፡፡ ይህን ችግር ያመጣው ነገር ምንድነው …አኑዋኑዋሩ ነው ….አመጋገቡ ነው…የአየር ሁኔታው ነው….ምክንያቱ ምንድነው የሚለውን ጥናት በማድረግ መፈተሸ ያስፈልጋል፡፡
‹‹…ካንሰር ሲባል ሰዎች የሚደነግጡበት ሕመም ስለሆነ ከመጨነቅና ከመፍራት የተነሳ በአመዛኙ ወደ እምነት ቦታዎችና ወደባህል ህክምና አዋቂዎች መሄድን የሚመርጡ አሁንም አሉ፡፡ እምነትን ተጉዋዳኝ አድርጎ መፍትሔ የመፈለጉ ነገር የሚከለከል ባይሆንም ነገር ግን አዳኝ እግዚአብሔር መሆኑን አምኖ ለህመሙ ትክክለኛውን መፍትሔ መፈለግ ብልህነት ነው፡፡ በአለም ላይ እግዚአብሔር ካልፈቀደ ማንም ምንም ሊያ ደርግ አይ ችልም በሚል ሀሳባቸውን አረጋግተው እምነታቸውንም ህክምናቸ ውንም ጎን ለጎን ቢያስኬዱ ጥሩ ይሆናል፡፡ እዚህ ላይ በጸበሉም ሆነ በባህል ሕክምናው በቻሉት መንገድ ሁሉ ከሞከሩ በሁዋላ ማዳን ከማይቻልበት ደረጃ ደርሰው ወደሆስፒታሉ የሚመጡና ለህልፈት የሚ ዳረጉ መኖራቸውን ማስታወስ ያስ ፈልጋል፡፡ በየትኛውም አቅጣጫ ቢሆን አዳኝ እግዚአብሔር መሆኑን መርሳት አይገባም፡፡ ሐኪሙም ሰው የሚያድነው እግዚአብሔር በሰጠው ጥበብ እግዚአብሔር ስለ ፈቀደ ብቻ ነው፡፡   


Read 370 times