ለዚህ እትም መግቢያ ያደረግነው ባለፈው እትም እንግዳችን የነበረችው የመራቢያ አካላት ካንሰር ሕክምና እስፔሻሊስት ኦንኮሎጂ ጋይኒኮሎጂ ዶ/ር ማርያማዊት አስፋው ተናግራው ከነበረው የወሰድነው ነው፡፡ ሰዎች በምንም ምክንያት ቢታመሙ ለመዳን ሲሉ የሚወስዱአቸው እርም ጃዎች ትክክለኛውን አቅጣጫ እንዳይስት ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ምርመራ ካደረጉ በሁዋላ ለኦፕራሲዮን እንዲዘጋጁ ሲነገራቸው አይ… ሰውነቴን ቢላ አይነ ካውም…በጸበል ወይም በባ ህላዊ ህክምና …ወዘተ በመሳሰሉት እድናለሁ ብሎ እራስን ከህክ ምናው ማራቅ አይገባም፡፡ ሐኪሙም ባገኘው እውቀት ተጠቅሞ ሰዎችን በሕክምና ሲረዳ እግ ዚአብሔር በሰጠው ጥበብ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ፡፡ ስለዚህ በየትኛው ነው የዳንኩት ለሚ ለው ጥያቄ መልስ ለማግኘት ሲባል ብቻ ሕክምናውን እርግፍ አድርጎ ወደእምቱና ወደጸበል ብቻ ከመሄድ ይልቅ እምነቱንም ህክምናውንም ጎን ለጎን አድርጎ መሞከርና በየትኛውም አቅ ጣጫ ቢዳን አዳኝ እግዚአብሔር መሆኑን መዘንጋት እንደማይገባ ተናግራ ነበር ኦንኮሎጂ ጋይኒኮሎጂስት ማርያማዊት አስፋው፡፡
ወደሕመሙ አይነት ስንዘልቅ የመራቢያ አካላት ካንሰር ማለት በየትኛው የሰውነት አካል ላይ የሚከሰት ነው ለሚለው ጥያቄአችን ዶ/ር ማርያማዊት የመከተለውን መልሳለች፡፡
የመራቢያ አካላት ካንሰር ሲባል በዋነኛነት የማህጸን ጫፍ ካንሰር ተጠቃሽ ነው፡፡
ከዚያም በመቀጠል የዘር ፍሬ ካንሰር የሚባል የካንሰር ሕመም አለ፡፡
የዘር ቱቦ ካንሰር ሌላው የካንሰር ታማሚ አካል ነው፡፡እራሱን ችሎ ወይንም ከዘር ፍሬ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ህመም ሊሆን ይችላል፡፡
የማህጸን ግድግዳ ካንሰር ሌላው የካንሰር ተጠቂ ሲሆን ይህም ከጊዜ ወዲህ እየጨመረ የመጣ ትኩረት የሚሻ ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ይህ የሰውነት አካል በካንሰር የሚጠቃበት ምክንያት ከአኑዋኑዋር ጋር በተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ ሰው ብዙ ጊዜ አካሉ ውፍረት ሲገጥመው ለዚያ ድግፍ የሚሰጡ የተለያዩ ሆርሞኖች ስለሚኖሩ እንዲሁም የደም ግፊት የመሳሰሉት ለህመሙ ሊያጋልጡ ይችላሉ፡፡
የማህጸን ጡንቻ ላይም ካንሰር ይከሰታል፡፡
የማህጸን ከንፈር ካንሰርም ሊኖር ይችላል፡፡
የቫጃይናል ካንሰርም (የሴት ብልት) ሌላው ህመም ነው፡፡
ስለዚህ የመራቢያ አካላት ካንሰር የሚባሉት ከላይ የተጠቀሱት ናቸው፡፡
እነዚህ የካንሰር ሕመሞች ቀድሞ የሚያሳዩት ምልክቶች እና የሚገጥሙ ሕመሞች እንደየአካሉ ይለያያል፡፡ ነገር ግን የማህጸን በር ካንሰር ከሌሎቹ የሚለይበት ሁኔታ አለ፡፡ በእርግጥ ቀድሞ የሚያሳየው ምልክት የለውም፡፡ የሚከሰተውም በቫይረስ ኢንፌክሽን ማለትም HPV በሚባለው ቫይረስ ኢንፌክሽን ስለሆነ አስቀድሞ በመመርመር ወደካንሰር ከመለወጡ በፊት እንዲድኑ ማድ ረግ ይቻላል፡፡ ስሜቶቹ ደም መፍሰስ ፤የዘንጋዳ ውሀ የመሰለ ፈሳሽ፤በግንኙነት ጊዜ ወይ ንም በመታጠብ ጊዜ የሚያጋጥም መድማት ሊሆን ይችላል፤ወይም በግንኙነት ጊዜ ያለ ህመም ሲሆን በጣም ትልቅ ደረጃ ከደረሰ ደግሞ የታፋ እግርን ጨምሮ ጀርባን እስከ እግር ድረስ ከነርቭ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የህመም አይነት ስሜት ይኖረዋል፡፡
የዘር ፍሬ ካንሰር በቀድሞ ጊዜ እንዲያውም ድምጽ አልባ ገዳይ በመባል ይታወቅ ነበር፡፡ ይህ የሆነው ግን ስሜቶች ስለሌሉት አይደለም፡፡ ብዙ ጊዜ ስሜቶቹ ከጨጉዋራ እና ከአንጀት ሕመም ጋር በተያያዘ የሚሰሙ ስሜቶች ጋር የመመሳሰል እድሉ በጣም ሰፋ ያለ ስለሆነ ነው፡፡ምግብ ቶሎ የመጥገብ፤ሆድ የመነፋት ስሜት ሁሉ አለው፡፡ በእር ግጥ ሁሉም እንደዚህ ያለ ህመም ያለው ሰው ጨጉዋራ አለበት ማለት እንደማይቻል ሁሉ የካንሰር ታማሚ ነው ለማለትም አስቸጋሪ ነው፡፡ ስለዚህ የዘር ፍሬ ካንሰር ህመም ስለሌለው እንደገናም ከሌሎች ሕመሞች ጋር የሚመሳሰል ስሜት ስላለው ለህክምናው ቶሎ የማይገኝ ነው፡፡ የካንሰር ሕመሞች ወደ ነርቭ አካባቢ የመሄድ ወይንም በጣም ተልቀው የመጫን ስሜት ያመጣሉ፡፡ እነዚህን ስሜቶች የሚያሳዩ ካልሆነ በስተቀር የህመም ስሜት የላቸውም፡፡ የዘር ፍሬ ካንሰር መከሰቱን የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው የሚባሉት ደግሞ ከሌሎች ሕመሞች ስሜቶች ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ ብዙ ጊዜ ለህክምናው አስቸጋሪ ይሆናል፡፡
ሌላው የማህጸን ግድግዳ ካንሰር ሲሆን በየወሩ ከሚመጣው የወር አበባ በተለየ ቶሎ ቶሎ ደም የመፍሰስ ሁኔታ ይስተዋልበታል፡፡የማህጸን ካንሰር ካንሰር የሚባለውም በውጭው በኩል የማሳከክ ባህርይ አለው፡፡ ሽፍታ፤የመጫጫር፤ትንሽ ቆጣ የማለት ነገር ሊኖር ይችላል፡፡ እብጠ ቶች ሊታዩ ይችላሉ፡፡ ህክናውን በሚመለከት ቅድመ ካንሰር ምርመራ ሲደረግ የማህጸን ጫፍ ሕመም ወደፊት ካንሰር ሊሆን ይችላል የሚባል ከሆነ ቀላል በሆነ የህክምና ዘዴ ታካሚዎቹ እንዲረዱ ይደረጋል፡፡
የማህጸን ግድግዳ ላይ ሲሆን ቅድመ ካንሰር የሚባሉት ላይ ሲገኝ ካንሰር ከመሆኑ በፊት መድሀ ኒት በመስጠት ህክምና ሊደረግ ይችላል፡፡ ካንሰር ከሆነ በሁዋላ ግን ኦፕራሲዮን ተደርጎ መው ጣት አለበት፡፡ የካንሰር ሴሉ በጣም ተሰረጫጭቶ ወደ ጉበት፤አንጀትን ወደሚሸፍነው ጮማ እና የተለያዩ ቦታዎች ሲሰራጭ እጢዎቹን ለቅሞ የማውጣት ሕክምና ይደረጋል፡፡ በዚህ ህክምና እስከ ኬሞቴራፒ እና የጨረር ሕክምና ድረስ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ሁኔታ አለ፡፡ የዘር ፍሬ ካንሰርን በሚመለከት በእርግጥ በግልጽ የሚያሳዩ ስሜቶች ወይንም ምልክቶች ባይኖሩም ግን በዘር ፍሬ ላይ በሚደረጉ ምርመራዎች የሚገኙ እብጠቶች ሲኖሩ ከእብጠቴ በመነሳት ምርመራ ሲደረግ ወደካንሰር የተቃረበ የሚመስል ነገር ካለ ወይንም ወደዚያው ሊያመራ እንደሚችል የሚጠቁም ነገር ካለ በመድሀኒት፤በኬሞቴራፒ እንዲሁም በኦፕራሲዮን በመሳሰሉት አስፈላጊ የህክምና ዘዴዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች አሉ፡፡ የማህጸን ከንፈር ላይ ያለ የካንሰር ሕመም ሲሆን እንደሁኔታው ማለትም ካንሰሩ ያለበትን ክፍል ከጫፍ ከመቁረጥ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በአካባቢው ያለውን በመቁረጥ እና በማውጣት የኬሞ እና ጨረር ሕክምና ይሰጣል፡፡
በእርግጥ የታካሚዎች ሁኔታ ይለያያል፡፡ አንዳንዶቹ በከተሞች ይኖራሉ፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ በገጠር ይኖራሉ፡፡ በከተሞች ይኖራሉ የሚባሉትም እንደከተማው ስፋትና እድገት ሁኔታዎች ሊለያዩ እንደሚችሉ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ባጠቃላይ ግን ሴቶቹ የካንሰር ሕመሙን ምል ክቶች ሲያዩ ወይንም ስሜቱ ሲከሰት በፍጥነት ወደህክምናው ይቀርባሉ ወይ ለሚለው ጥያቄ እንደአኑዋኑዋሩ፤እንደኢኮኖሚው ሁኔታ፤የህክምና ተቋማቱን ለማግኘት ቅርብ ወይንም እሩቅ ከመሆን ጋር ተያይዞ ፤በቤተሰብ ውስጥ ከሚኖራቸው እገዛ ወይንም ድጋፍ ከመሳሰለው ጋር ተያይዞ የሚለያዩ ነገሮች አሉ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የመማርና ያለመማር ሁኔታም ሌላው እንደምክንያት ሊወሰድ የሚችል ነው፡፡ በተለይም ከትምህርት ጋር ተያይዞ አሁን ካለው የኢን ተርኔት ድረገጾች ከመሳሰሉት የተለያዩ ጥናቶችን በመመልከት ስለሕመሙ አስቀድሞ የማወቂያ ዘዴው ወይንም እድሉ ሰፊ ስለሚሆን ህመሙ አስከፊ ደረጃ ሳይደረስ እርምጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡ የማይካደው ነገር ግን ባልተማሩ እና ከከተሞች ወይንም ከሆስፒታች በርቀት ላይ የሚኖሩ ሴቶች በጊዜ ቀርበው ያለመታከም ሁኔታ ስለሚኖራቸው በህመሙ የመጎዳት እጣ ፈንታቸው ከፍ ያለ ይሆናል ማለት ይቻላል፡፡ የካንሰር ህመሙ አንዳይከሰት ለመከላከል፡-
ቅድመ ካንሰር ምርመራ ማድረግ ፤ይህንን ምርመራ በእድሜአቸው ሰላሳ አመት ከሆና ቸው እናቶች ጀምሮ እንዲያደርጉት ይመከራል፡፡ ከምርመራው በሁዋላ በሚገኘው ውጤት መሰረትም ከስድስት ወር ጀምሮ በየሶስት አመቱ ወይንም በአንድ አመት አለ ዚያም በአምስት አመት ምርመራ መደረግ እንዳለበት በሕክምና ባለሙያዎች ይመ ከራል፡፡
ሌላው ክትባት ነው፡፡ ክትባት እንዲደረግ የሚመከረው ሴት ልጆች ከወንድ ጋር ግንኙነት ሳይጀምሩ በፊት ባላቸው እድሜ ነው፡፡ለዚህም ምክንያቱ (HPV) Human Papilloma Virus ኢንፌክሽን የሚመጣው ከግንኙነት ጋር ተያይዞ ስለሆነ ነው፡፡
ከዚህ በተረፈ ማንኛዋም ሴት ውፍረት ከመጠን ያለፈ እንዳይሆን መከታተል ወይንም የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ይጠበቅባታል፡፡እንደ ደም ግፊት ስኩዋር የመሳሰሉትን ሕመሞችም መከላከል ካንሰር እንዳይከሰት ይረዳል፡፡ እንደ ዶ/ር ማርያማዊት አገላለጽ ከካንሰር ሕመሙ ለመራቅ ሌሎች መፍትሔዎችም ስላሉ ሴቶች ጤንነታቸውን በንቁ እንዲከታተሉ እና ከህክምና ባለሙያዎች ምክር ለማግኘት መጣር ይጠቅማቸዋል፡፡
Saturday, 29 June 2024 20:06
አዳኝ እግዚአብሔር ነው፡፡
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ