Thursday, 04 July 2024 12:16

( ስጋ እንጂ መልካምነት አይቀበርም )

Written by 
Rate this item
(0 votes)

 አንዳንድ ጊዜና ሁኔታዎች አሉ፤ መሀሉን ትታችሁ ውጤቱን ብቻ የምትናገሩበት። ብቻ ግን ከቻላችሁ ደግ ተግባር ስሩ ፤ ከቻላችሁ። እኔ ሁሌም መልካምነት የልብ መሻቴ ነው። በተግባር ግን እንደ ልቤ አይደለሁም። ክፉም ባልሆን ደግ ግን አይደለሁም።

መልካምነት የእውቀት ሳይሆን የመሰጠት ጉዳይ ነው። አሁን ይኸው ሁለቱም (አሰፋም ፣ ነቢይም) በሕይወት የሉም። አሰፋ ጎሳዬ ( የ"አዲስ አድማስ" ጋዜጣ ባለቤት ) የተባለ እጅግ የበዛ መልካም ሰው፣ በነቢይ ሕይወት ላይ ያለውን ድርሻ የምናውቅ እናውቀዋለን። ነፍስን መቁረጥ የፈጣሪ ድርሻም ቢሆን፣ በሰውኛ ስሌት የነቢይ ሕይወት እዚህ እንዲደርስ የአሰፋ ጎሳዬ ድርሻ የበዛ ነው። (" አሴዋ " ይለዋል ግሩም ዘነበ።)

አሴዋ ከተለየን ብዙ ዓመታት ተቆጥረዋል። በነቢይ ሕይወት ላይ ያለው የመልካምነት ድርሻ ግን እስከ ትናንትናዋ ዕለት የደረሰ ነው። አሴዋ፤ ስለ መልካምነትህ የምናውቅ እናስታውስሀለን።

          የሁለታችሁንም ነፍስ ይማር!

(ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ)

Read 757 times