Saturday, 06 July 2024 21:03

ቅድመ ወሊድ የህክምና አገልግሎት በመንግስት የህክምና ተቋማት...

Written by  ሃይማኖት ግርማይ ከኢሶግ
Rate this item
(0 votes)

የዓለም የጤና ድርጅት እንዳስቀመጠው በቅድመ ወሊድ የህክምና አገልግሎት ወቅት ለእናት እና ለተፀነሰው ልጅ ጠቃሚ የሆነ ክትባት፣ መድሃኒት እና የተለያዩ ምርመራዎች ይደረጋል። ከዚህም መካከል የደም ግፊት (ኢክላምሲያ እና ክላምሲያ) እንዲሁም የኤች አይ ቪ ኤድስ ህክምናዎች ተጠቃሽ ናቸው። ነፍሰጡር ሴቶች በእርግዝና ወቅት ስላሉ ጤናማ እና ጤናማ ስላልሆኑ ሁኔታዎች እንዲሁም በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ስለሚያጋጥሙ ችግሮች(ምልክቶች) ከህክምና ባለሙያ ትምህርት ያገኛሉ። ከዚህ በተጨማሪም ስለ እርግዝናው ሁኔታ በማወቅ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ይረዳል።  
በአዲስ አበባ ከተማ ኮ/ቀ ክ/ከ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት የጤና መኮንን ፍቅሬ አየለ እንደተናገሩት በጤና ጣቢያው ውስጥ ከቅድመ ወሊድ የእርግዝና ክትትል ጀምሮ እስከ ድህረ ወሊድ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል። “የሚሰጠው አገልግሎት ሙሉበሙሉ ያለ ክፍያ ነው። ተጠቃሚዎች የሚከፍሉት ምንም ነገር የለም። በመንግስት የሚሸፈን ነው” ብለዋል የጤና መኮንን የሆኑት ፍቅሬ አየለ። እንዲሁም በእርግዝና እና በወልድ ወቅት ከጤና ጣቢያው አቅም በላይ የሆነ ሁኔታ ሲያጋጥም ወደ መንግስት ሆስፒታል ታካሚዎች የሚላኩበት(ሪፈር የሚባሉበት) አሰራር መኖሩን ተናግረዋል።
መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዓለም አቀፍ ደረጃ ነፍሰ ጡር እናቶች በአማካይ 85 በመቶ የሚሆኑት 1 ጊዜ ቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል ያደርጋሉ። እንዲሁም ከ10 እናቶች 6 እናቶች ብቻ ናቸው በዓለም የጤና ድርጅት የተቀመጠውን ቢያንስ 4 ጊዜ በእርግዝና ወቅት ክትትል እንዲያደርጉ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ የሚያደርጉት። የጤና መኮንን የሆኑት ፍቅሬ አየለ “ከዚህ ቀደም ነፍሰጡር እናቶች 4 ጊዜ የቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል እንዲያደርጉ ይደረግ ነበር። አሁን ግን ቢያንስ 8 ጊዜ ወደ ህክምና ተቋም እንድትመጡ ይጠበቃል” ብለዋል። አከለውም ይህን አገልግሎት የሚከታተሉ ነፍሰ ጡር እናቶች መኖራቸውን ጠቅሰው ግን ቁጥራቸው አነስተኛ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም እንደ ችግር ያስቀመጡት ነፍሰ ጡር ሴቶች እርግዝናው ከገፋ በኋላ ወደ ህክምና ተቋም መሄዳቸውን ነው። ስለሆነም ችግሩን ለመቅረፍ እና አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት ያስፈልጋል። እናም በሂደት እንደሚስተካከል ነው ሜዲካል ዳይሬክተሩ የተናገሩት።
የወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ጨምሮ በአከባቢው የሚገኙ የመንግስት የህክምና ተቋማት (ጤና ጣቢያዎች) ለተጨማሪ የህክምና አገልግሎት ታካሚዎችን የሚልኩት (ሪፈር የሚሉት) ወደ አለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ነው። ነገር ግን እንደ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር ንግግር ጤና ጣቢያው፣ የጤና ቢሮ፣ አለርት እና ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በጋራ በመነጋገር የጤና ጣቢያው ታካሚዎች ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲላኩ ተደርጓል። “ወደ ጥቁር አንበሳ እና አለርት መሄድ ከትራንስፓርት አንፃር የተለያየ ነው። ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል መሄድ ርቀት አለው። እናም እናቶችን ወደ ጥቁር አንበሳ በምንወስድበት ሂደት ውስጥ ድንገተኛ ነገር ካጋጠመን ወደ አለርት እንወስዳለን” ብለዋል የጤና መኮንን የሆኑት ፍቅሬ አየለ።
“ሪፈር ተብላ የመጣች እናትን በሙሉ እንቀበላለን። እኛ ከምንሰጠው የህክምና አገልግሎት ከፍ ያለ ይኖራል ብለን አናስብም። ሁሉንም የህክምና አገልግሎት እንሰጣለን” ያሉት በአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፅንስ እና ማህፀን ህክምና ክፍል ሀላፊ የሆኑት የፅንስ እና ማህፀን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሺመክት ይልማ ናቸው። የፅንስ እና ማህፀን ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑት ዶ/ር ሺመክት ይልማ እንደተናገሩት ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ከ1 ዓመት በፊት ነው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲዘዋወር የተደረገው። ይህም ትስስር የተለወጥፕው አለርት ሆስፒታል ባለበት የስራ ጫና ምክንያት ነው።
አለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከአዲስ አበባ ከተማ ኮ/ቀ ክ/ከ እና ከኦሮሚያ ክልል ከ8 ጤና ጣቢያዎች እንዲሁም ከ2 ሆስፒታል ወላዶችን ይቀበላል። “በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ከሚገኙ ሆስፒታሎች ውስጥ የማዋለድ አቅማችን 2 ወይም 3ኛ ደረጃ ላይ ብንሆን ነው” በማለት ብዛት ያላቸውን እናቶች እንደሚያዋልዱ ዶ/ር ሺመክት ይልማ ተናግረዋል። ስለሆነም ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ከአለርት ሆስፒታል ቀድሞ ወደነበረው ትስስር ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል እንዲመለስ ተደርጓል። ነገር ግን ሜዲካል ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት ድንገተኛ ችግር ሲኖር አለርት እንደሚቀበል ዶ/ር ሺመክት ይልማ በተመሳሳይ ተናግረዋል።
ከጤና ጣቢያ ወደ ከፍተኛ የህክምና ተቋም (ሆስፒታል) የሚላኩ ነፍሰጡር እና ወላድ ሴቶች የጤና ሁኔታከዚህ ቀደም በቀዶ ጥገና የወለደች እናት
- ብዙ ልጆች የወለደች እናት
- በተደጋጋሚ ፅንስ መቋረጥ ያጋጠማት እናት
- በእርግዝና ወቅት የደም ግፊት ያጋጠማት
(ኢክላምሲያ እና ክላምሲያ)
- የስኳር በሽታ
- የማህፀን እጢ
- በወሊድ ወቅት ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥም
በአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የፅንስ እና ማህፀን ህክምና ክፍል ሀላፊ የሆኑት የፅንስ እና ማህፀን ህክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ሺመክት ይልማ እንደተናገሩት ትስስር ካላቸው ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች ውስጥ 2ቱ ቀዶ ጥገና ይሰጣሉ። እንዲሁም እነዚህ ቀዶጥገና የሚሰጡት የጤና ተቋማት ከአቅማቸው በላይ ከሆነ ማለትም የፅንስ እና ማህፀን ህክምና ስፔሻሊስት እገዛ ሲያስፈልግ ወደ አለርት ሆስፒታል ይልካሉ።
በአለርት ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ከተማ ኮ/ቀ ክ/ከ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ካነጋገርናቸው ነፍሰጡር እንዲሁም የወለዱ እናቶች መካከል ሰሚራ መሀመድ አንዷ ናት። ሰሚራ የ7 ወር ነፍሰ ጡር ስትሆን ቤተል ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኝ ጤና ጣቢያ የቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል ስታደርግ ቆይታለች። ነገር ግን የ5 ወር ነፍሰ ጡር እያለች ባጋጠማት የጤና እክል ምክንያት ወደ አለርት ሆስፒታል ተዘዋውራ ለ2ወራት በክትትል ላይ ትገኛለች።
ሌላኛዋ በአለርት ሆስፒታል ያገኘናት ነፍሰ ጡር በላይነሽ ትባላለች። ወደ አለርት ሆስፒታል ከመሄዷ በፊት ዘነበ ወርቅ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በሚገኝ ጤና ጣቢያ ክትትል ስታደርግ ቆይታለች። “የ9 ወር ነፍሰ ጡር ነኝ። የምወልድበት ቀን አልፏል ተብዬ ነው ወደ አለርት የመጣሁት” ብላለች በላይነሽ።
“4ቱንም ልጆቼን የወለድኩት በጤና ጣቢያ ውስጥ ነው” ያለችው በወረዳ 3 ጤና ጣብያ ልጇን ከተገላገለች ከ4 ሰአታት በኋላ ያገኘናት ሀያት ሸረፋ ናት። ሀያት የ5 ወር ነፍሰ ጡር እያለች ክትትል መጀመሯን ተናግራለች። እንደ ሀያት ንግግር በምጥ መውለድ የተሻለ ነው። “ከዚህ ቀደም በሆስፒታል ወልጄ አውቃለው። ግን ያለ ፍቃድ ቀዶ ጥገና አይደረግም። ምንም መፍራት አያስፈልግም ህክምናው ጥሩ ነው ብዬ ለሌሎችም እመክራለው” ብላለች ሀያት ሸረፋ። እንዲሁም ሀያት እንደተናገረችው አስፈላጊውን ቅድመ ወሊድ የህክምና ክትትል ማድረጓ በሰላም ለመገላገሏ አስተዋፅኦ አበርክቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ ኮ/ቀ ክ/ከ ወረዳ 3 ጤና ጣቢያ ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት የጤና መኮንን ፍቅሬ አየለ ነፍሰጡር ሴቶች ቢያንስ ከ16 ሳምንት(4ወር) የእርግዝና ወቅት ጀምሮ ቅድመ ወሊድ የህክምና አገልግሎት ማግኘት እንደሚገባቸው ተናግረዋል።

Read 278 times