Monday, 22 July 2024 19:40

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ሃላፊዎች በሙስና ተጠርጥረው ተያዙ

Written by 
Rate this item
(2 votes)

የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው  በቁጥጥር ስር ዋሉ።
በቁጥጥር ስር ከዋሉት  ሃላፊዎች መካከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሀብታሙ አበበ እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ታምራት ታገሰ  ይገኙበታል።

የዋቸሞ ዩኒቨርስቲ ለአንድ የዩኒቨርስቲው የፋይናንስ ቡድን መሪ የ790 ቀናት አበል እንዲሁም ለሌላኛው የፋይናንስ የቡድን መሪ ደግሞ በስድስት ወራት ውስጥ ብቻ የ1,469 ቀናት (1,056,854 ብር) አበል እንደተከፈላቸው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በዩኒቨርሲቲው የሀብት ምዝበራ ላይ አተኩሮ በሰራው  የምርመራ ዘጋቢ ፊልም ላይ  ማቅረቡ ይታወሳል።

 በተጨማሪም  የዩኒቨርስቲው ፋይናንስ ሳያውቅ 1.4 ቢሊዮን ብር ለኦክስጅን ማምረቻ በሚል በህገወጥ መንገድ መንቀሳቀሱንና ፍቃድ የሌለው የኮንስትራክሽን ድርጅት ግንባታውን እንዲሰራ ያለ ጨረታ እንደተሰጠው በምርመራ ውጤቱ ተገልጿል። በዚህ የተነሳ ዛሬ አመራሮቹ በቁጥጥር ሥር ውለዋል::

Read 1606 times