Neuro Diversity ማለት የሁለት እንግሊዝኛ ጥምረት ነው፡፡ Neuro ማለት ነርቭ ማለት ሲሆን Diversity ማለት ደግሞ ብዝሀነት ማለት ነው፡፡ ይህ የሁለት ቃላት ጥምረት ወደ አማርኛ ሲመለስ የነርቭ ብዝሀነት የሚል ትርጉም ይሰጣል፡፡፡፡ አሁንም የነርቭ ብዝሀነት ማለት ምን ማለት ነው ሲባል በተለያዩ መንገዶች ሊነሳ የሚችል ሲሆን ማለትም የእጽዋት ብዝሀነት፤የባህል፤የእንስሳት …ወዘተ ብዝሀነት ይባላል፡፡ ወደ ነርቭ ስንመጣ የእያንዳንዱ ሰው የነርቭ ውቅር በተለያየ መልኩ የተቀናጀ ነው፡፡ ስለዚህም ከአለም ጋር በሚኖረው መስተጋብር እንደየነርቭ ውቅሩ የተለያየ ነው፡፡ ስለዚህም ብዝሀነት በዚህ ይገለጻል፡፡ የነርቭ ብዝሀነት ለአእምሮም ይሁን ለስነልቡና ህክምና አዲስ የመጣ አሰራር ሲሆን አካታችነትን የሚያበረታታ፤ አለመቻልን ወይም ስንኩልነትን የሚያስቀር አስተሳሰብ ነው፡፡
ይህንን ማብራሪያ ያገኘነው ከዶ/ር ትእግስት ዘሪሁን ነበር፡፡ ዶ/ር ትእግስት ዘሪሁን የህጻናትና ወጣቶች አእምሮ ጤና ሰብ እስፔሻሊስት ናት፡፡ ዶ/ር ትእግስት በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ አስተማሪና እንዲሁም Neuro Diversity Center Ethiopia የሚል የነርቭ ብዝሀነት ላይ የሚሰራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ተባባሪ መስራችና ስራ አስኪያጅ ናት፡፡ ከእስዋ ጋር በተነጋገርnው መሰረት በዚህ እትም ህጻናትንና የአእምሮ ብዝሀነትን የሚመለከተውን ቁምነገር ለንባብ ብለናል፡፡
የዚህን እትም መሰናዶ ለማቀናበር ያመራነው ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ነበር፡፡ ሁል ጊዜ ወር በገባ ሐሙስ ቀን ከአምስት ሰአት ጀምሮ ከአእምሮ ጋር በተያያዘ በተለይም ኦቲዝም ላለባቸው ህጻናት ወላጆች በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ስልጠና ይሰጣል፡፡ ይህ ስልጠና የሚ ሰጠውም በNeuro Diversity Center Ethiopia ሲሆን ስልጠናው ካለምንም ክፍያ በነጻ የሚሰጥ ነው፡፡ በዚያ ተገኝተን ስልጠናውንም ለመመልከትና ከአንዳንድ ወላጆች ጋር ለመነጋገር እድሉን ስላገኘን ለግንዛቤ እንዲረዳ ለንባብ ብለነዋል፡፡
በቅድሚያ ያነጋገርናት ዶ/ር ቤተልሔም አባይነህ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሶስተኛ አመት ሳይካትሪ ሰልጣኝ ሐኪም ናት፡፡ ዶ/ር ቤተልሔም እንዳለችው ህጻን ሲወለድ የአእምሮ ችግር ሊኖርበት ይችላል፡፡ ነገር ግን ልክ እንደአዋቂዎች የአእምሮ ሕመም አለበት ለማለት የሚያስች ለውን ምል ክት ገልጾ ለመናገር ሊከብድ ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን ብዙ ጊዜ ከሚያሳዩት ድርጊት ፤ባህርያት ፤እራሳቸውን ከሚገልጹበት መንገድ በመነሳት ሊታወቅ ስለሚችል በሚደረግ ምር መራም ሊገኝ ይችላል፡፡ ቤተሰብም ከሌሎች ህጻናት ሁኔታ ጋር በማስተያየት ወደ ባለሙያ ሊያመጣቸው ይችላል፡፡ የአእምሮ ሕመም መነሻው ብዙ ሲሆን አንደኛው ግን ከአፈጣጠር ጋር ተያይዞ ጀነቲክስ የሚባለው እንደምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ በተረፈ በዙሪያችን የሚገኙ ጭንቀ ትን የሚፈጥሩ ነገሮች፤ማህበራዊ ጉዳዮች …ወዘተ የአእምሮ መዛባትን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ ብላለች፡፡
በማስከተል ያነሳነው ሀሳብ ህጻናት ሲወለዱ ጀምሮ የአእምሮ ችግር ኖሮባቸው ሊወለዱ ይችላሉ ሲባል ከላይ ከተጠቀሱት ምክንያቶች ውጭ ሌሎች ተጠቃሽ ነገሮች ይኖሩ ይሆን የሚል ነበር፡፡ ዶ/ር ቤተልሔም ስትመልስ ከላይ እንደጠቀስኩት በአፈጣጠር ወይንም ጀነቲክስ የሚባለው ከቤ ተሰብም ሊወረስ የሚችልበት አጋጣሚ የሚኖር ሲሆን ሌላው በእርግዝና ጊዜ የሚፈጠሩ ችግ ሮች ይኖራሉ፡፡ በእርግዝና ጊዜ እናትየው ላይ የሚፈጠር ሕመም ካለ ፤ለተለያዩ ሱስ አምጪ ነገሮች የመጋለጥ ነገር ካለ፤በተለያዩ ምክንያቶች ለመድሀኒቶች መጋለጥ ካለ …ወዘተ በጽንሱ ላይ የተለያዩ የጤና ችግሮችን ሊያስከትል ይችላል፡፡ የተሟላ አካል ይዘው እንዳይወለዱ ከሚያ ደርጉአቸው ምክንያቶች በተጨማሪ አካሉ ተሟልቶ ቢፈጠርም የተሟላ ጤንነት እንዳይ ኖረው የሚያደርጉ ምክንያቶች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከእርግዝና ጊዜ ባለፈም በወሊድ ጊዜ የሚፈጠሩ ችግ ሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ Autism ከአእምሮ እድገት፤ ከትምህርት አቀባበል ጋር በተያያዘ ወይንም ደግሞ ያለመረጋጋት የመሳሰሉት ባህርያት የሚታይበት ሲሆን እነዚህ ችግሮች በተፈጥሮ ይመ ጣሉ ቢባልም ምክንያቶቻ ቸው ግን ከአእምሮ እድገት ወይንም ከነርቭ አወቃቀር ጋር ተያይዞ ብዙ መሆናቸው ይገለጻል ፡፡
እነዚህ የአእምሮ ችግሮች በህጻናቱ ላይ ከተፈጥሮ ጀምሮ የሚከሰቱ ሲሆን ለተመልካች ግን ግልጽ ሆነው የሚታዩበት እድሜ በእድገታቸው አንዳንድ ነገሮችን በሚያሳዩበት ወቅት ይሆ ናል፡፡ በእርግጥ በህጻንነት ማለትም ሰውን መለየት መሳቅ የመሳሰሉትን ነገሮች ከመጀመራቸው በፊት ያለው ሁኔታ ብዙም ግልጽ ላይሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን እድሜአቸው ከፍ እያለ ሲሄድ በየደረጃው ከሚኖራቸው ግንኙነት የሚማሩአቸው፤ነገሮችን ተቀብለው ምላሽ የሚሰጡባ ቸው፤ በእድገታቸው ጊዜ እንደየእድሜአቸው የሚያደርጉአቸው ነገሮች አሉ፡፡ እነዚህ ነገሮች በሚጠበ ቁበት እድሜ ሳይሆኑ ሲቀሩ ወይንም ደግሞ ወደሁዋላ በሚዘገዩበት ጊዜ ችግሩን ለመረዳት እንመጀመሪያ የሚ ታዩ ባህሪያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
አንድ ልጅ ተወልዶ ከተወሰኑ ጊዜያት በሁዋላ እራሱን ችሎ መቀመጥ አለበት፡፡
አንድ ልጅ በተወሰነ እድሜው እማማ፤አባባ ማለት አለበት፡፡
እቃ ይዞ መቆም፤ቆሞ መሄድ፤መሮጥ የሚጀምርበት እድሜ አለ፡፡ …ወዘተ
ከላይ የተጠቀሱት እና መሰል የእድገት ሁኔታዎች በሁሉም ልጆች ዘንድ ትንሽ ልዩነት ቢኖረ ውም እንኩዋን በአብዛኛው በተመሳሳይ እድሜ የሚታዩ የአእምሮ እድገቶች ናቸው፡፡ ነገር ግን የአእምሮ እድገት ችግር አለባቸው የሚባሉ ልጆች እነዚህን ተፈጥሮአዊ ሂደቶች በተጠበቀው ጊዜ ያለማከናወን ወይንም የመዘግየት ነገር ይኖራቸዋል፡፡ በእርግጥ ረዘም ያለ ጊዜ ወስደው ሊያደርጉት ይችሉ ይሆናል፡፡ በተለይም ከኦቲዝም ጋር በተያያዘ ቀድሞ እንደማስጠንቀቂያ የሚወሰዱ ነገሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ እናታቸውን ወይንም ሌላ ሰው በአይናቸው መከተል ፤አንዳ ንድ ነገሮች ሲደረጉላቸው ምላሽ መስጠት፤ፈገግታ ማሳየት፤ የተለያዩ ነገሮችን በፊታቸው መግለጥ፤የአይን ለአይን ግንኙነት የመሳሰሉትን ነገሮች መልሰው አለማ ድረግ እንዲሁም ነገሮችን በድግግሞሽ ማድረግ፤ እረፍት የሌለው የሰውነት እንቅስቃሴ ማድ ረግ፤በሌሎች አኩዮቻቸው ላይ የማይታዩ ለአንዳንድ ነገሮች ወጣ ያለ ትኩረት መስጠት፤ ፍላጎት ማሳየት አይነት ባህርይ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ በተለይም ኦቲዝም ከበድ ባለ ሁኔታ ከተከሰተ በአንድ አመት እድሜአቸውም ላይ በትልልቆቹ ላይ የሚታየው ባህርይ ሊታይ ይችላል፡፡ ነገር ግን ወደሁለት አመት ሲሆናቸው ባህርያቸው እየተገለጸ ስለሚመጣ በደንብ ማወቅ ይቻላል ብላለች ዶ/ር ቤተልሔም፡፡
በስልጠናው ላይ ያገኘናቸውን አንዲት እናትና ልጅን አነጋግረን ነበር፡፡ ምስክርነታቸው እንደሚከተለው ሰጥተዋል፡፡
‹‹…እኔ የስምንተኛ ክፍል ተማሪ ነኝ፡፡ በዘንድሮው ብሔራዊ ፈተናም (ሚኒስትሪ) ተፈት ኛለሁ፡፡ እኔ በትምህርቴ ምንም ችግር አልገጠመኝም፡፡ ነገር ግን የስምንተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መቀበል አትችይም ተብዬ ውጣ ውረዶችን አልፌአለሁ፡፡ ቤተሰቤ እና በቅዱስ ጳውሎስ ያሉት የህጻናትና ወጣቶች የአእምሮ እና ስነልቡና ሐኪሞችን ጨምሮ ወላጆችም ባደረጉት ክትትል ለፈተና ቀርቤአለሁ፡፡ ውጤቱን እንደማንኛውም ተማሪ እጠብቃለሁ፡፡ ነበር ያለችው፡፡ ስምንተኛ ክፍል ድረስ ስትማር ካለምንም ችግር ከመጣች ለብሔራዊው ፈተና ለምን አትበቂም እንደተባለች ባለሙያዎቹም ሆኑ ወላጆችም ሊያስረዱ አልቻሉም፡፡ እንደእነሱ እምነት ምንም የምትከ ለከልበት ምክንያት አልነበረም፡፡
በመቀጠል እናትየውን ነበር ያነጋገርናት፡፡ ለመሆኑ ልጅቷ Autistic መሆንዋን ከመቼ ጀምሮ ነው ያወቅሽው የሚል ነበር ጥያቄአችን፡፡
‹‹…..እኔ እንደእናትነቴ ሁኔታውን አስቀድሜ መረዳት ሲገባኝ ነገር ግን አላወቅሁም ነበር፡፡ በሁዋላ ግን ትምህርትዋ ላይ ወደ ሁዋላ ስትሔድብኝ ወደ ህክምናው መጣሁኝ ፡፡ እድሜዋ አምስት አመት ከሆናት በሁዋላ ከትምህርትዋ ጋር በተያያዘ የገጠመኝ ነገር ለብቻዋ ገለልተኛ መሆን፤ትምህርቱን ጥላ መውጣት ስታበዛ ቀስ ብላ ታስተካክላለች እያልኩ ስጠብቅ እየባሰ ስለመጣ ምንድነው ችግሩ በሚል ወደ ጳውሎስ አመጣሁአት፡፡ እስከአሁን እየተማረች ነው፡፡ የወደፊቱን እግዚአብሔር ያውቃል ብላለች፡፡
ዶ/ር ቤተሰልሔም አባይነህ እንዳለችው ኦቲዝም ማለት ሕመም አይደለም፡፡ የአእምሮ ብዝሀነት ለሚለው አንዱ መገለጫ ሲሆን እሱም ልዩነት እንደማለት ነው፡፡ ኦቲዝም ያለባቸው ልጆች ከአእምሮ እድገት ውቅረት ጋር ተያይዞ መለየት ስለሚኖራቸው የተለየ ባህርይ ያሳያሉ እንደ ማለት ነው እንጂ ህመም አይደለም፡፡ ስለሆነም ከሌሎች የተለየ እንክብካቤና ድጋፍ ሊደረግላቸ ውም ይገባል፡፡
Saturday, 27 July 2024 21:44
የአእምሮ ብዝሀነት (Neuro Diversity)
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ