Wednesday, 07 August 2024 07:45

ሞት ማስደንገጥ ሲያቅተው

Written by  (ከበደች ተክለአብ፤ እ.ኤ.አ. ጁላይ 2020
Rate this item
(2 votes)

ከተማም እንደ ሰው
ሲከፋው፤
ከተማም እንደ ሰው ልጅ መልክ
የታመቀ ህመም ግርዶሽ
በበሩ ድባብ ይጥላል
የተነከረ ከል ሸማ
የጠቆረ ማቅ ይለብሳል
ፅልመት ፀሐዩን ያደምቃል
ሲቃጠል ብርሃን አይሰጥም
ሲጋይ ሙቀት አይወልድም
እንደ በረዶ ክምር
አጥንት ያቀዘቅዛል
የደም ዝውውር አግዶ
የስትንፋስ ሂደት ይዘጋል
አንድ ባንድ የተካበው ካብ
በቅፅበት ግፊት ተንዶ
በበቀል ክብሪት ይጫራል።
ያልተቀመረ ብሶት ጎርፍ
አይኑን ጨፍኖ ይንዳል
የጊዜን ምልክት ሳያይ
የዘመኑን ስልት ሳያጤን
የመፍትሄ ክር ይበጥሳል።
ሃሳብን ከሰው የማይለይ
በእስትንፋስ የማይፀገይ
ችግኝ ይኮተኩታል።
(ከበደች ተክለአብ፤ እ.ኤ.አ. ጁላይ 2020)

Read 328 times