ባለፈው እትም ስለአእምሮ ብዝሀነት ኒሮ ዳይቨርሲቲ ለንባብ ያልነው ሀሳብ ነበር፡፡ በአምዱ ላይ የህጻናትና ወጣቶች የአእምሮ ህክምና እስፔሻሊስትን ዶ/ር ትእግስት ዘሪሁንን እና ዶ/ር ቤተል ሔም አባይነህን ጨምሮ ወላጆችን ታዳጊዎችንም የጨመረ ምስክርነትን ለንባብ ማለታችን ይታወሳል፡፡ አንድ ህጻን ገና በእርግዝና ላይ እያለ በእናትየው በኩል በሚደርስ አንዳንድ ችግሮች የተነሳ አእምሮው ሊዛባ እንደሚችል ባለሙያዎቹ አብራ ርተዋል፡፡ የአእምሮ ብዝሀነት በሚለው አገላለጽም ሰዎች የተለያየ የአእምሮ እድገት ወይንም የነርቭ አወቃቀር እንደሚኖ ራቸው እና ከእነዚህም መካከል እንደ ችግር የሚቆጠሩ የነርቭ አወቃቀሮች የሚኖሩ ሲሆን ሁሉም በአጠቃላይ ግን እንደህመም የሚቆጠሩ አለመሆናቸውንና ከመካ ከላቸው በህክምና ሊረዱ የሚችሉ ነገሮች መኖራቸውን ይገልጻሉ፡፡ በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በመገኘት በተለይም ኦቲዝም አለባቸው የሚባሉትን ህጻናት ወላጆች በስልጠና በማገዝ ላይ ካሉት ባለሙያዎችና ከወላጆቻቸው ጋር ተወያይተን ነበር፡፡ ለአንባቢያን ግንዛቤ ያስጨብጣል ያልነውን እነሆ ብለናል፡፡ የምናስቀድመው ወላጆችን ይሆናል፡፡
‹‹…እኔ አሁን ልጄ አስራ ስድስት አመት ሆኖታል፡፡ ልጁ እስከ አራት አመት እድሜው በቂጡ መንፏቀቅ እንጂ ቆሞ አልሄደም ነበር፡፡ ሰዎችም ቀስ ብሎ ይሄዳል…አንዳንድ ልጆች እንደዚህ ናቸው እያሉ ሀሳብ ሲሰጡኝ እውነት መስሎኝ ዝም አልኩ፡፡ ከዚያም ገና በአራት አመቱ መቆምም መሄድም ጀመረ፡፡ ከዚያም ትምህርት ቤት ሳስገባው እስከሶስት አመት ድረስ ምንም ለውጥ አላመጣም፡፡ ከዚያም ለሶስት ወር ወደ ጸበል ወሰድኩ፡፡ ለውጥ የለውም፡፡ ወደሐኪም ቤት ብወስደውም ምንም ችግር የለውም አሉ፡፡ ከዚያም ወደ ፓውሎስ አመጣሁት፡፡ ችግሩም ታወቀ፡፡ …››
ዶ/ር ቤተሰልሔም አባይ የህጻናትና ወጣቶች የአእምሮ ህክምና ሶስተኛ አመት ተማሪ ሐኪም እንደገለጸችው በመረጃ የተደገፈ ነገር መናገር ባይቻልም ከልምድ እንደሚታየው ግን አሁን አሁን በተሻለ ሁኔታ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ሐኪም ቤት ያመጣሉ፡፡ ወላጆች በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን የሚተላለፉ መልእክቶችን በማየት እና ከልጆቻቸው ባህርይ ጋር በማስተያየት የእኔ ልጅ እንደዚህ አይነት ችግር ሊኖርበት ይችላል በማለት ወደ ሐኪም ቤት ያመጣሉ፡፡ ለስ ልጠናውም ፈቃደኛ ሆነው ይሰለጥናሉ፡፡ ልጆቻቸውን ሐኪም በሚነግራቸው መሰረት ይረዳሉ፡፡ ብላለች፡፡
የሌላ ወላጅ ምስክርነት፡-
‹‹…የእኔ ልጅ እስከ ሁለት አመቱ አላወራም ነበር፡፡ ሲጠራም አይዞርም፡፡ አንድ ነገር ከያዘ አይለቅም፡፡ ምግብም ላይ የተወሰነ የለመደውን እንጂ ሌላ አይመገብም ነበር፡፡ በህክምናውም በአፋጣኝ የተገኘ ነገር አልነበረም፡፡ መጨረሻ ላይ ግን ወደ አእምሮ ሕክምናው ስወስደው ኦቲዝም እንዳለበት ተነገረኝ፡፡ ከዚያም ስልጠና ወሰድኩ፡፡ ወደሆስፒታልም በቀጠሮው አመጣዋለሁ፡፡ የተቸገርኩት ግን ትምህርት ቤት ነው፡፡ ትምህርት ቤቱን ብለዋውጥለትም አልተሳካልኝም፡፡ …››
ሲስተር አይሻ አብዱልአዚዝ ሳይካትሪ ነርስ ናት፡፡ ልጆቻቸው ኦቲዝም ያለባቸው ወላጆች በደ ስታ እየመጡ ስልጠናውን ይወስዳሉ፡፡ ከህክምና ባለሙያዎች ከሚያገኙት ምክር በተጨማሪ እርስ በእርሳቸው የሚያ ደርጉት የልምድ ልለወለወጥ በጣም ያረካቸዋል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እንዲያውም ስልጠናው በማይኖርበት ጊዜ ጭምር በመገናኘት ቀናት ሳምንታት እንዴት እንዳለፉ የምንነጋገርበት የምንወያይበት ጊዜ አለ፡፡ የወላጆቹ የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ በተለይ አስፈላጊ የሚሆነው ልጆቻቸው ኦቲዝም እንዳለበት በአዲስ መልክ ያወቁ ወላጆች ልምዱ ስለሌላቸው ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች በሚሰጠው መልስ ነው ብላለች፡፡
በቀጣይ ያገኘናት ወላጅ እንደሚከተለው ሃሳብዋን ገልጻለች፡፡ ‹‹…ስሜ ማርታ ይባላል፡፡ ናርዶስ የምትባል ልጅ አለችኝ፡፡ እኔ መጀመሪያ ልጅ ከመውለዴ በፊት በበጎ ፈቃደኝነት አገለግል ነበር፡፡ በተለይም ልጆቹ ስለሚያሳዝኑኝና በተለይም ወላጆቻቸው አብረው ሲንገላቱ ስመለከት ጊዜዬንም ፤ጉልበቴንም፤እንዲሁም ሊያግዙ የሚችሉ ሌሎች ሰዎችን እያስተባበርኩ ዘኒ የኑስ በከፈተችው ኦቲዝም ማእከል የምችለውን ሁሉ አደርግ ነበር፡፡ በሁዋላም እኔ ናርዶስን ስወልድ እስከ ሁለት አመት ገደማ ደህና ነበረች፡፡ እየዋለ እያደር ግን በኦቲዝም ማእከል ካየሁት ልምድ አንጻር ልጄን ስመለከታት ጥርጣሬ አደረብኝ፡፡ ልጄ የማውራት አቅሟም ሆነ ፍላጎትዋ እየቀነሰ መጣ፡፡ የምትፈልጋቸው ሰዎችም ውስን ሆኑ፡፡ ሰው ሲያናግራትም መልስ መስጠትዋን ቀነ ሰች፡፡ ከዚያም ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል በመምጣት ሳሳያቸው በጊዜ ሂደት እንደሚፈታ እና ክትትል ማድረጉን ግን እንድቀጥል ተነገረኝ፡፡ ልጄ አታወራም ነበር፡፡ ልጄ መሄድም ትፈራ ነበር፡፡ እኔ ግን ልጄን ለመርዳት ስል የተለያዩ ቦታዎች ላይ እያገለገልኩ ልምድ እቀስም ነበር፡፡ አነባለሁ፡፡ የተለያዩ ነገሮችን አያለሁ፡፡ ከዚያም ሄጄ ልጄ ላይ እሞክራለሁ፡፡ ልጄ ማውራት ዋን፤መመገብዋን፤መጸዳዳትዋን በአግባቡ እንድታደርግ መርዳት ስላለብኝ የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ፡፡ ዛሬ ከቀድሞው በተለየ መልኩ መርጣ መልበስ ፤መመገብ፤እራስዋን ችላ መጸዳ ዳት ታደርጋለች፡፡ ትምህርት ቤትም በአግባቡ ትሄዳለች፡፡ በእርግጥ እኔ ተምራ የት ትደርሳለች የሚለውን ማሰብ አልፈልግም፡፡ እራስዋን አውቃ መኖር የምትችልበትን እውቀት ከቀሰመች ለእኔ በቂዬ ነው፡፡ እናም ብዙ መስዋእትነትን ከፍያለሁ፡፡ ስለዚህ ወላጆች አቅማቸው በሚፈቅ ደው መሰረት ተደጋግፈው ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆቻቸውን በተገቢው መርዳት አለባቸው የሚል እምነት አለኝ፡፡ብላለች፡፡
ለሲስተር አይሻ አብዱልአዚዝ ያነሳነው ቀጣይ ጥያቄ ስልጠናው እስከምን ድረስ ይሄዳል? ወደ ስነ ተዋልዶ ጤና ሁኔታ ስናመራ ሊደረግ የሚገባው ጥንቃቄ ምን መምሰል እንዳለበት ጭምር ወላጆች ይሰለጥናሉ?ብለን ነበር፡፡
‹‹…እኛ ስልጠናውን የምንሰጠው ለእናቶችና ለአባቶች ነው፡፡ የምንሰጣቸው ሀሳብም ስልጠና ውን አስቀድመው ቢጀምሩ ልጆቻቸውን ከልጅነት ጀምሮ እንዴት ማሳደግ እንዳለባቸው እውቀት እንደሚያገኙ እንነግራቸዋለን፡፡ ብዙ ጊዜ ግን የሚያጋጥመን ወላጆች ባሉበት ሁኔታ ጊዜያቸውን ገፍተው ልጆቻቸው እድሜአቸው ከፍ ካለ ማለትም ወደ አስር አመት ገደማ ከደረሱ በሁዋላ የሚመጡ ናቸው ፡፡ ስልጠናው አስራ ሁለት ሳምንት የሚፈጅ ሲሆን በየሳምንቱ ለአንድ ቀን እየተገኙ ስለልጆቻቸው ሁሉንም ነገር እናስተምራለን፡፡ የስነተዋልዶ ጤናን ጉዳይ በተመለከተ ግን የተለየ ስልጠና የለንም… ብላለች፡፡
ለእናት ማርታም ተመሳሳይ ጥያቄ አንስተንላት ነበር፡፡ ልጅሽ እራስዋን ከተለያዩ ጥቃቶች እንድትከላከል ምን ታደርጊያለሽ ?
‹‹…ልጄ ናርዶስ እድሜዋ 14 አመት ደርሶአል፡፡ ዛሬ የወር አበባ እያየች ነው፡፡ ስለዚህ በምንም መንገድ እንዳትጎዳ ለማድረግ የቻልኩትን ሁሉ እመክራታለሁ፡፡ ለምሳሌ ልብስዋን መለወጥ የምንችለው እኔና እናቴ ብቻ ነን፡፡ ሌላ ሰው ልብስዋን ከፍ አድርጎ ሰውነትዋን መመልከትም ሆነ መንካት እንዳይችል በሚገባት መልኩ አስረዳታለሁ፡፡ አብራ የምትቆያቸውን ሰዎች ማንነ ትም እከታተላለሁ፡፡ ዘመድም ሆነ ባእድ እንዳይጎዳት በማሰብ የቻልኩትን ሁሉ አደር ጋለሁ፡፡ በትምህርት ቤትም ያላትን ውሎና ግንኙነት በቅርብ እከታተላለሁ፡፡ አንድ ነገር ከሆነ በሁዋላ ከማዘን አስቀድሞ መጠንቀቅ እንደሚገባ አውቃለሁ፡፡ እኔ እጥራለሁ፡፡ በተረፈው ደግሞ እግዚ አብሔር ይጨመርበት…›› ብላለች፡፡
ሲስተር አይሻ አብዱልአዚዝ በስተመጨረሻው የተናገረችው እነዚህ Autistic የሆኑ ልጆች የመማር እና ጤናቸውም በአግባቡ የመጠበቅ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን ትምህርት ቤት በት ክክል አይገኝላቸውም፡፡ ወላጆች ወስደው ካስመዘገቡ በሁዋላ መልሳችሁ ውሰዱ ይሉአቸዋል፡፡ እነዚህን ማስተማር አንችልም ይሉአቸዋል፡፡ ወይንም ደግሞ ልዩ እረዳት ያስፈልጋቸዋል በማለት ገንዘብ ይጠይቁአቸዋል፡፡ ይህንን ማድረግ የማይችሉ ወላጆች ልጆቻቸው ከቤት ውስጥ እንዲውሉ ይሆናሉ፡፡ ህክምና ውንም በሚመለከት በትክክል መድሀኒታቸውን ማግኘት ስለማይቻል በተመሳሳይ መድሀኒት እና ለአዋቂዎች የሚሰጥ መድሀኒት እንዲወስዱ ይደረጋል፡፡ በውጭ ሀገር በጣም እርካሽ የሆነ መድሀኒት እዚህ በጣም ውድ ሆኖ ይሸጣል፡፡ Autism ላለባቸው ህጻናት ትምህርትና ሕክምና የሚመለከታቸው አካላት እርምጃ ሊወስዱ ይገባል ብላለች፡፡
Thursday, 08 August 2024 06:46
Autism፡ ህጻናት ተረግዘው ሳሉ ሊገጥማቸው ይችላል፡፡
Written by ፀሐይ ተፈረደኝ ከኢሶግ
Published in
ላንተና ላንቺ